በአልጄሪያ እ.ኤ.አ 2019 ሐምሌ 4 ቀን አጠቃላይ ምርጫ እንደሚደረግ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር የተገለፀው፡፡ ምርጫው እንዲካሄድ የተወሰነው ለወራት ያክል ሲደረግ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ነው፡፡ እ.ኤ.አ 2019 የካቲት ወር ላይ የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ለአምስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለው ማለታቸው ውጥረት ፈጥሮ ነበር፡ ፡ ከዚህ በኋላ በአገሪቱ ተቃውሞ በመነሳቱ ፖሊስ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና እሥራት ቀጥሏል፡፡ የአልጄራዊያን ዋና ፍላጎት ግልፅነት ያለው የፖለቲካ ለውጥና በሥልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች እንዲወርዱ ነው፡፡
ህዝቡ የአብዱላዚዝ ቡተፍሊካን የፕሬዚዳንትነት ቆይታ የማይፈልጉ ሲሆን በተጨማሪም የአገሪቱ መከላከያ እያደረገ ያለውን ጣልቃ ገብነት ይቃወማሉ፡፡ የአገሪቱ መከላከያ ኃይል አባልና ምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ አህመድ ጋዲ ሳላህ እያሳዩት ያለው የመንግሥት ድጋፍ በህዝቡ እንዲጠሉ አስደርጓቸዋል፡፡ ቀደም ብሎ ቡተፍሊካ የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ አባል የነበሩ ሲሆን እ.ኤ.አ 1950 እና 1960 ነፃነት ለማግኘት ከፈረንሳይ ጋር በተደረገው ጦርነት ተሳትፈዋል፡፡ ቡተፍሊካ እራሳቸውን በአገሪቱ የሥልጣን ቁንጮና ወሳኝ ሰው አድርገው የሚያዩ ሲሆን አጠቃላይ የፖለቲካ ስልጣኖችን በእጃቸው ያስገቡ ናቸው ተብሎ በህዝብ ይታመናል፡፡
ጋኢድ ሳላህ ደግሞ በአገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት አለው የሚል ሀሳብ ያራምዳሉ፡፡ እንደ ጋኢድ ሳላህ ገለፃ፤ አገሪቱ መንግሥት ባለጋራ የሆኑ አገራት በተፈጠረው ተቃውሞ ፍላጎት አላሳዩም፡፡ ነገር ግን በሰሜን አፍሪካ አካባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ግን አሳስቧቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሚደረጉ ተቃውሞዎች ላይ የፈረንሳይ፣ የሩስያና የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም፡፡ እንደዚህ አይነት ክሶችና ተቃውሞዎች የሚያሳዩት የአልጄሪያ መከላከያ ኃይል ሥልጣን ለመያዝ ፍላጎት እንዳለው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በቅርብ ሳምንታት በተደረጉ ተቃውሞዎች ላይ አልጄራዊያን በሕገ መንግሥታቸው አንቀፅ 7 ላይ የተቀመጠውን ‹‹ጥግ ድረስ ነፃነት የሚፈቀደው ለህዝቡ ነው፡፡
ህዝቡም የሚወከለው ነፃ በሆኑ ሰዎች ብቻ ነው›› የሚለውን አንቀፅ ጽፈው ይዘው አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የአገሪቱ መከላከያ ኃይል እውቅና ለማግኘት የአልጄሪያን ህዝብ እየደገፈ ይገኛል፡፡ ከሁሉም ሂደት በኋላ የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ ወታርደር ክንፍ ከህዝቡ ለማሸሽ ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡ ነገር ግን በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ እስካሁን ያልተፈታ በወታደራዊ ሥልጣንና የሲቪል ኃይል መካከል ቁርሾ አለ፡፡ በነፃነት ትግል ወቅት ወደነበረው ሁኔታ ቢታይ የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ ውስጥ መከፋፈል ተፈጥሮ ነበር፡፡
በነፃነት ትግል ወቅት በብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ትግል ነበር፡፡ በትግሉም መከፋፈሎች ተፈጥረዋል፡ ፡ በወቅቱ በየነበሩ ሽኩቻዎች አሁንም ድረስ ባለው የህዝብ ተቃውሞ ላይ በመንግሥት ባለሥልጣናት ውስጥ ታይቷል፡፡ በቅርብ ሳምንታት የተፈጠረው ነገር ቢታይ አልጄራዊያን ጊዜያዊ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ቤን ሳላህን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ናውረዲን ቤዶኡ እና የሕገ መንግሥት ካውንስል ሊቀመንበር የነበሩትን ጣይብ ብላዚ ከሽግግር መንግሥቱ እንዲወጡ ተጠይቀዋል፡፡ እነዚህን ሦስት ባለሥልጣናት ከዚህ በፊት ከነበሩ ከሪም ባልካሲም፣ አብዱልሀፊድ ቦሱፍ እና ላክሀዳር ቤንቶባ ጋር በፖለቲካ አመለካከታቸው ያመሳስሏቸዋል፡፡ በነፃነት ጦርነት ወቅት እነዚህ ሦስት ባለሥልጣናት ቁልፍ ሰዎች ነበሩ፡፡
ባለሥልጣናቱ የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የወታራዊ ኃይሉ ፖለቲካው ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥር አድርገዋል፡፡ በተመሳሳይ እነዚህ ሦስት ባለሥልጣናተ በአቤን ረመዳኔ ግድያ የሚጠረጠሩ ናቸው፡፡ አቤን ረመዳኔ የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ተከታይና አባል የነበረ ሲሆን በሚያራምዳቸው የለውጥ ሀሳቦች እስካሁን ድረስ የሚታወስ አክትቪስት ነው፡፡ እሱ ሲያራምዳቸው የነበሩ ሀሳቦች በሠላማዊ ሰልፈኞች ተይዘው አደባባይ ወጥተዋል፡፡ ረመዳኔ ቀደም ብሎ የአገሪቱ ፖለቲካ በአልጄራዊያን መመራት አለበት በሚል አቋም ከፈረንሳይ ነፃ ለመውጣት ከፍተኛ ትግል ያደረገ ሰው ነው፡፡ እ.ኤ.አ 1956 ሀሳቡን ለማሳወቅ የሶማም ኮንግረስ እንዲደራጅ አድርጓል፡፡ በወቅቱ የነበሩት የፖለቲካ ሀሳቦች አሁንም ድረስ በአልጄሪያ እየተንፀባረቁ ይገኛሉ፡፡
ኮንግረሱ ሁለት መመሪያዎች የነበሩት ሲሆን የመጀመሪያው የፓርቲው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከመከላያው በላይ መሆን አለበት የሚልነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በፖለቲካው ቅድሚያ የሚሰጠው በተደረገው የነፃነት ትግል ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ለታገሉ ሰዎች መሆን እንዳበት ይጠቅሳል፡፡ የረመዳኔን ሀሳብ የሚከተለው የለውጥ አራማጅ ላሪብ ቤን ምሀዲ በወታደራዊ ኃይሉ ሃሳብ ተጠልፎ የነበረ ቢሆንም በአልጄሪያ ነፃነት ትግል ወቅት ከአገር ውጭ ሆነው የሚታገሉ ሰዎች ፖለቲካው ላይ መምጣት የለባቸውም የሚል አቋም ነበረው፡ ፡ በዚህም በፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ የተከፋፈለና ለሲቪል ባለሥልጣና ነፃነት በሚሰጥ መልኩ መሠራት ተጀመረ፡፡ ከተወሰነ ዓመታት በኋላ ይህ መመሪያ ችላ የተባለ ሲሆን በተለይ ለቀጣይ አልጄሪያ ዕጣ ፈንታ ተፅዕኖ እንዳይኖረው መደረጉ ይታወሳል፡ ፡
የመጀመሪያው የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት አህመድ ቤንቤላ የጎንግረሱ አባል ሳይሆኑ ሥልጣን የጨበጡ ሲሆን የታጠቁ ኃይሎች ደጋፊ በመሆናቸው ሲቪል ባለሥልጣናን በማግለል በተለይ በወቅቱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ፈርሃት አባስ የቁም እስረኛ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ የቤንቤላ የሥልጣን መንገድ አብዛኛውን የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ አባላት ያሳተፈ ቢሆንም በወቅቱ የነበሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሀውሀሪ ባውሜድኒ መፈንቅለ መንግሥት በማድረግ ሥልጣን ያዙ፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱ ወታደራዊ ኃይሉ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ ያለውን ወሳኝነት ያሳየ ነበር፡፡ የአልጄሪያ ሦስተኛና አራተኛ ፕሬዚዳንቶች ማለትም ቻድሊ ቤንድጃዲ እና ሊምኔ ዞርዋል የወታደራዊ ክንፍ ነበሩ፡፡ በኋላ ላይ እነዚህን ክስተቶች አባስ እ.ኤ.አ በ1962 የተጀመረውን ትግል እና ለውጥ “የተቀበረ ነፃነት” በሚል በስዕላዊ መጽሐፍ አቅርበውታል፡፡ ቀደሞ በወታደራዊ ኃይሉና በሲቪል ባለሥልጣናት መካከል በነበረው ታሪካዊ ሽኩቻ በአልጄሪያ የሚገኘው ወታደር በህዝቡ ሥር ያለ ቅጥያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ እ.ኤ.አ 1988 ላይ ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ ይህንን አባባል ያፈርሰዋል፡፡
በወቅቱ በነበረው የኢኮኖሚ መውደቅና በሙስና የተበሳጨው ወጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ወታደራዊ ኃይሉ ሰብዓዊ መብትን በሚጥስ መንገድ 500 ንፁሀንን ገድሏል፡ ፡ እ.ኤ.አ 1991 ላይ በነበረው ምርጫ የአልጄሪያ መንግሥት ከህዝቡ የሚመጣበት ጫና በመብዛቱ ጥምር ፓርቲ ለመመስረት የሚያስችለውን እርምጃ ወሰደ፡፡ የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ ባስገራሚ ሁኔታ በኢስላሚክ ሳሊቬሽን ግንባር ፓርቲ ተሸነፈ፡፡ የአገሪቱ ወታራዊ ኃይል የምርጫውን ውጤት እንዲሰረዝ በማድረግ እና ሊፈጠር የነበረውን ውጥረት ለማርገብ ሲል የብሔራዊ ነፃነት ግንባር ፓርቲ መስራች የነበሩትን መሀመድ ባውዳፊን ወደ ሥልጣን አምጥቷል፡፡
መሀመድ ባውንዳፊ ታዋቂ ሰው ሲሆኑ የቤንቤላንና የባውሜድኒን አስተዳደሮች ይቃወሙ ነበር፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ 1992 ባውዳፊ ሚስጥራዊ በመሆነ መንገድ እንዲገደሉ መደረጉ አልጄሪያ ወደ ርስበርስ ጦርነት ከመግባቷ በተጨማሪ ወታደራዊው ኃይል ሥልጣኑን ተቆጣጥሮታል፡፡ የባውዳፊን መገደል የሚያሳየው ወታደራዊ ኃይሉ አልጄሪያን እስር ድረስ ለመቆጣጠር እንዲያስችለው የፈጠረው ሴራ መሆኑ ብዙዎች ይስማሙበታል፡ ፡ የባውዳፊ መንግሥት አገሪቱ ከገችበት ቀውስ እንድትወጣ ታማኝነት ያለውና በአገር ወዳድ መንፈስ ሲሠራ የነበረ ነው፡፡ እንዲሁም የኢስላሚክ አክቲቪስት ቡድን እንዲፈራስና የአገሪቱ መከላከያ ኃይሉ ላይ የራሱን ሰው በመሾም የአገሪቱን ደህንነት ቁጥጥር ያደርግ ነበር፡፡ ባውዳፊ እንደ ረመዳኔ፣ ቤን መሀዲና እንደሌሎቹ ቀደም ብሎ የነበረውን የሲቪል ባለሥልጣናትን ቁጥር ለመጨመር ሠርቷል፡፡ አሁን የአልጄሪያ ዜጎች በተቃውሟቸው እንደሚገልፁት በአገሪቱ ግልፅ የሆነ የሥልጣን ሽግግር ተደርጎ የሲቪል ኢንስትቲዩሽን እንዲፈጠር ይፈልጋሉ፡፡
ቡተፍሊካ ከሥልጣን ከወረዱ ከሦስት ቀናት በኋላ የባውዳፊ ወንድ ልጅ ናስር እና የቤን መሀዲ እህት ድሪፋ ህዝባዊ ተቃውሞውን የተቀላቀሉ ሲሆን ድምፃቸውንም አሰምተዋል፡፡ ዳሪፋ እንዳለችው፤ ሦስቱ ባለሥልጣናት ብቻ ሳይሆን ሁሉም እንዲወርዱ ይፈለጋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላም የባውዳፊ ቤተሰቦች በሰጡት መግለጫ፣ በቀጣይ ትክክለኛው የአልጄሪያ የለውጥ መርህ መምጣት እንዳበት በመጥቀስ፤ አልጄሪያ ሪፐብሊክ እንጂ ወታደራዊ መንግሥት መመስረት እንደሌለበት ይናገራሉ፡፡ የአልጄሪያውያንም ፍላጎት ከሁልም በላይ መሆን ነው ሲሉ ይጠቅሳሉ፡፡ ታሪካዊ ዳራዎች እንደሚያሳዩት እንደ ባውዳፊ፣ ረመዳኔ እና ቤን መሀዲ እንዲሁም የሳውማም ኮንግረስ መርህ በመከተል የአልጄሪያ ህዝቦች ቀድሞ የነበረውን ወታራዊ ሥልጣን ሳይሆን የለውጥ አራማጅ ፓርቲ በድጋሚ እንደሚፈልጉ በተቃውሟቸው አሳይተዋል፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2011
መርድ ክፍሉ