ኢትዮጵያውያን ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች የተገኙበት የጅቡቲ ዓለም አቀፍ የንግድ አውደ ርዕይ ትናንት (ህዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም) በይፋ ተከፍቷል፡፡
የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ክቡር እስማኤል ኦማር ጉሌ የንግድ ትርዒቱ በይፋ ከፍተዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡማር ጉሌህ በመክፈቻው ባሳሙት ንግግር መንግስታቸው ኢትዮጵያ ጨምሮ ከቀጠናው ሀገራት ጋር ያለውን የንግድና የቢዝነስ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ገልፀው የአከባቢው ሆነ ዓለም አቀፉ የቢዝነስ ማህበረሰብ በሀገሪቱ የሚገኘውን የቢዝነስ ዕድል እንዲጠቀም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ከአስራ እንድ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ምርቶችን የሚያስተዋውቁ ሀገር በቀል ተቋማት በቆዳ ምርቶች፣ በሀገር ባህል አልባሳት፣ በባልትና ውጤቶች፣ በቡና፣ በጥራጥሬና ቅመም ምርቶች፣ ምርቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የጪጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው በተጨማሪም ለትርዒቱ ወደ ጅቡቲ ሄደው የብሔራዊ ቲያትር የባህል ቡድን በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያን ድንቅ ባህላዊ ውዝዋዜዎችን በማቅረብ አድናቆትን አትርፏል፡፡
በንግድ ትርዒቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት በጅቡቲ የኢፌዴሪ አምባሳደር ክቡር ሻሜቦ ፊታሞ ከመክፈቻው አንድ ቀን ቀደም ብለው ኢትዮጵያውያኑን ተሳታፊዎች ለማበረታት ባዘጋጁት የእራት ግብዣ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ አምራቾች በጅቡቲ ያለውን የቢዝነስ ዕድል የበለጠ እንዲያውቁና እንዲጠቀሙበት እንዲህ አይነቱ የንግድ ትርዒቱ ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን አስረድተዋል፡፡