አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን ሠራተኞች ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ያሰባሰቡትን የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በመርካቶ ቁጥር አንድ ጽህፈት ቤት አስረከቡ፡፡
በገቢዎች ባለሥልጣን የመርካቶ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የድጋፍ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ተስፋጽዮን ሽኮ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች የተሰበሰበው ድጋፍ ውስጥ 750 ሺህ ብር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን ሥር ከሚገኙ 15 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች የተሰበሰበ ሲሆን፣ ቀሪውን በበጎ ተግባሩ ከተሳተፉ ባለሃብቶች የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
‹‹ሠራተኞቹ ለተፈናቃዮች አለኝታነታችንን መግለጽ አለብን›› በሚል ወኔ ተነሳስተው ያለ አንዳች ልዩነት ከደመወዛቸው በማዋጣት በችግሩ ለረሃብ ተጋለጭ ለሆኑ ሕጻናትና እናቶች ያላቸውን
ሰብዓዊነትና ርህራሄ ያሳዩበት መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ በቀጣይም አቅም በፈቀደ መጠን የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ከየቅርንጫፉ ተውጣጥተው ድጋፉን ያስተ ባበሩት የኮሚቴው አባላት በዓይነት የተዘጋጀውን ድጋፍ በአምስት አይሱዙ ኤፍ ኤስ አር መኪና ጭነው በመጓዝ ለተፈናቃዮቹ የሚያስረክቡ መሆኑን አቶ ተስፋጽዮን አክለው ገልጸ ዋል። በዓይነት ከቀረቡት ቁሳቁሶች መካከል አንከር የሕጻናት ወተት፣ ዘይት፣ዱቄት እና ፈሳሽ ሳሙና ይገኙበታል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ባለሥልጣን የመርካቶ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሕግ ማስከበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ይልማ እንደተናገሩት፣ ድጋፉ በሰብዓዊነት የተደረገ ሲሆን፣ ተጠና ክሮ የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል፡፡ አንድነ ታችን፣ መከባበራችን፣ እንዲሁም
የእያንዳንዳችን ቀለም፣ቋንቋ ወዘተ ልዩነት ውበት እንጂ ለችግር የሚያጋልጡን ሆነው አያውቁም፤ መሆንም የለባቸውም ብለዋል። ዜጎች አንድነታቸውን ካጠናከሩ በመካ ከላቸው ምንም እንከን ሊፈጠር አይችልም፤ ሌላ ዓላማ ያለው አካል ካለም ምቹ ሁኔታ አግኝቶ በዜጎች ህይወት ጉዳት አይደርስም። ስለዚህ እህት ወንድምን ማፈናቀል ማብቃት አለበት፤ሊቆም ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላ ልፈዋል፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2011
መሐመድ ሁሴን