አዲስ አበባ፡ የከተሞች ልማታዊ ሴፍ ትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ምልመላ ፍት ሃዊነት የሌለ መሆኑን፤ የክፍያ መዘግየትና ማነስ፤ የአቅርቦት ወይም የግብዓት እጥረት እና የጥራት መጓደል ችግሮች መኖራቸውን በስልታዊ ምርመራ ማረጋገጡን የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ።
ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው፤ በሴፍትኔት ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታዎች ሲቀርቡለት ቆይቷል። ከህብረተሰቡ ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተደርጓል። በተደረገው ውይይት ላይም የተጠቃሚዎች ምልመላ ፍትሃዊ አይደለም፤ የክፍያ ይዘገያል፤ ክፍያው አነስተኛ ነው፤ የጥራት መጓደል አለ የሚሉ ቅሬታዎች ተነስተዋል።
እነዚህን ቅሬታዎችን መነሻ በማድረግ የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም አጠ ቃቀም ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ ሀሳብ ለማመላከት በአዲስ አበባ፣ አዳማና ደሴ ከተሞች ስልታዊ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው ችግሮች እውነታ ያላቸው መሆናቸውን በም ርመራው ተረጋግጧል።
በአንዳንድ ቦታዎች የከተሞች የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎች መመልመያ መመሪያ ቁጥር 54/2008ን በሚጻረር መልኩ መስፈርቱን የማያሟሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፤ ይህ አግባብ አለመሆኑን ምርመራው አመላክቷል።
ተቋሙ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል ያላቸውን ምክረ ሀሳቦችንም አስ ቀምጧል። እንደ ተቋሙ ምክረ ሀሳብ መሰ ረት በምዝገባ ወቅት የሚሰጡ መረጃዎች ትክክለኛነታቸው ቢረጋገጥ፤ መስፈርቱን ሳያሟሉ የተካተቱ ግለሰቦችን በማስወጣት መስፈርቱን የሚያሟሉት ቢካተቱ፤ ክፍያው ወቅቱን ጠብቆ ቢፈጸምላቸው፤ የድጋፉ ተጠቃሚዎች አስፈላጊው የሰለጠነ የሰው ሀይል ቢሟላላቸው እንዲሁም ፕሮግራሙን እንዲያስፈጽሙ ኃላፊነት የተሰጣቸው ተቋ ማት በቂ የሰው ሃይልና ግብዓት ቢሟላላቸው ችግሩን ለመቅረፍ ያስችላል።
ፕሮግራሙን ለማስፈጸም ኃላፊነት የተሰ ጣቸው አካላት በፕሮግራሙ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ቢሰጣቸውና ባለድርሻ አካላት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ተቀናጅተው ቢሰሩ የከተማ ሴፍ ትኔት ፕሮግራም የታሰበለትን ዓላማ ያሳካል ብሏል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10/2011
በመላኩ ኤሮሴ