አዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ ከተማ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎች ቢከናወኑም በቅን ጅት ጉድለት የተፈለገው ውጤት አለመም ጣቱን የአዲስ አበባ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞላልኝ ባዩ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደተ ናገሩት፤ ባለፉት ሰባት ወራት በአዲስ አበባ የሚገኙ ወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቅረፍ ሥራዎች ቢከናወኑም በሴክተር መስሪያቤቶችና በክፍለከተሞቸ ቅንጅት ችግር የተፈለገው ውጤት አልመጣም።
በክፍለከተሞች አካባቢ ሥራ ዕድል የተፈጠረላ ቸውን ወጣቶች በቅርበት አለመከታተል፣ የሥራ ዕድል ሳይፈጠር እንደተፈጠረ አድርጎ ሪፖርት ማድረግ በተለይ በየካና አራዳ ክፍለከተሞችና በከተማው ሴክተር መስሪያቤቶች ተፈጠረ የተባ ለው የሥራ ዕድል ላይ የጠራ መረጃ አለመኖር መስተዋሉን አመልክተዋል።
የቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ኢንቨስ ትመንት ቢሮና ሠራተኛና ማህበ ራዊ ጉዳይ ቢሮዎች በኩል ሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች የከተማዋ ነዋሪ ስለመሆናቸው አለመታወቅ፣ ስም ዝርዝራቸው አለመኖር እና የሥራ ዕድሉ የዚህ ዓመት ስለመሆኑ አለመረጋገጡ ችግር መፍጠሩን አስረድተ ዋል።
አብዛኛው የሥራ ዕድል ፈጠራው በአገልግ ሎትና በንግድ ዘርፍ ላይ በመሆኑ በማፋክቸሪንግ ዘርፍ ወጣቶችን የማደራጀት ሥራው መረሳቱን ገልጸዋል። በቀጣይ በተለያየ ጊዜ ሰልጥነው ተደራጅተው ወደ ሥራ የገቡ ወጣቶችን ችግር መፍታት፣ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ መስሪያቤቶች በእቅዳቸው መሠረት እንዲመሩ ማድረግ እና ተገንብተው የተጠናቀቁ የመስሪያ ቦታዎች መሠረተ ልማት የማሟላት ሥራ እንደሚከናወን አብራርተዋል። ባለፉት ሰባት ወራት የተሰጠ ተዘዋዋሪ ብድር 227 ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር ሲሆን ከተሰጠው ብድር ውስጥ 123 ሚሊዮን 595 ሺ 199 ብር መመለሱን ጠቁመዋል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 7/2011
መርድ ክፍሉ