በአፍሪካ የጀርመን ኮሚሽነር ጉንተር ኑክ፣ በአፍሪካ ዘመናዊ ቅኝ ግዛትን ለማስቀረትና አፍሪካ አገራት ወደ አውሮፓ የሚያደርጉትን ስደት ለማስቆም የአፍሪካን መሬቶች ለማልማት በአገራቸው ውስጥ መኖር እንዲችሉ እገዛ መደረግ እንዳለበት ሰሞኑን ባቀረቡት ጥናት ላይ ተናግረዋል:: እንደ ኑክ አባባል ከሆነ፣ “ነፃ ልማት” የአፍሪካን ኢኮኖሚ ለማፋጠን ስለሚያግዝና በአህጉሪቱ እድገትና ብልጽግና እንዲፈጠር ስለሚያደርግ አፍሪካውያን አውሮፓን የስደት መዳረሻ ከማድረግ ያቆማሉ፡፡
ጥናቱ የተቀላቀለ ገጽታ ቢኖረውም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ አንዳንዶቹ ጥናቱን በታሪክ የተሞላ ኢኮኖሚያዊ መግለጫ ሆኖ ውጥንቅጥ ለሆነ ፖለቲካ ማርገቢያ አድርገው አይተውታል:: በጥናቱ በአፍሪካ ልዩ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች እና የኢኮኖሚ ፕሮሰስ ዞን በመመስረት የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይ ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለበት ተቀምጧል:: ይህ ሁኔታ እድገትን ለማነሳሳት እና በጣም ጥሩው መንገድ የሚፈጥር ሲሆን ሰዎችን ከማህበረሰባዊ እውነታዎች እና ሰቆቃዎች በመከላከል ቢያንስ የሰው ጉልበት ማዳን ላይ ማተኮር እንደሚያስፈልግ ቀርቧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ ገዢ ሀሳብ ተገኝቷል:: ይሄም «ቅኝ ገዥዎች» የሚለው ቃል ላይ ሲሆን፤ ጀርመን በተለይም በናሚቢያ፣ በካሜሩን፣ ታንዛኒያ እና ቶጎ ውስጥ የከረረ ቅኝ ገዢነት እና የዘር ማጥፋት ዘመናት ታሪክ እንዲህ ያለውን ሀሳብ ለማውጣት የሞራል ስልጣን የለውም የሚል ሀሳብ ቀርቧል::
በአጠቃላይ በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ከአውሮፓ ቅኝ ግዛት ከደረሰባቸው ጉዳት ለማገገም እየታገሉ ነው:: በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የመሬት ይዞታ አሁንም ያልተለወጠ እና ለሀብታምና ለውጭ አገር ዜጎች ለሆኑ ሰዎች ከመስጠት በዘለለ የዘር መጠቀሚያ በመሆንም ኢኮኖሚያዊ ልዩነትን አምጥቷል፡፡ ብዙ የአፍሪካ አገሮች ከአውሮፓውያን የወረሱትን አገር የሰው ጉልበት በሚያባክን መንገድ በመጠቀማቸው አስቸጋሪ ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴዎችን ማለፍ አልቻሉም:: የቅኝ አገዛዝ ዘመን ካከተመ በኋላም አመጽ አሁንም በአፍሪካ ውስጥ አለ፡፡ በእርግጥ የአውሮፓ አገራት አሁንም በአፍሪካ አገራት አካባቢ ዘመናዊ የቅኝ ገዥነት ስሜቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡
በአፍሪካ ውስጥ በሚገኙት ችግረኞችን ልብ ለማግኘት ቀላሉ መንገድ መሰረታዊ የሆነውን የውሳኔ ሀሳብ በአግባቡ ማየት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ቅኝ ገዢነት ምን ማለት እንደሆነና የዚህ ጉዳቱም መታየት አለበት፡፡ መዝገበ ቃላቶች የቅኝ አገዛዝን ‹‹ፖሊሲ ወይም ሌሎች አገራት በመውረር የፖለቲካና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር የኢኮኖሚ ጥገኛ ማድረግ›› ብለው ያስቀምጡታል:: ይህም ማለት ሀይልን በመጠቀም እውቅና ያለውን ማህበረሰብ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ መንገዶች ጥገኛ ማድረግን ያካትታል፡፡ ይህ ደግሞ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለአንድ ማህበረሰብ መኖር ወሳኝ በመሆናቸው ነው፡፡
ስለዚህ ኑክ ያቀረቡት ሐሳብ በመሠረታዊ ደረጃ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ሲባል የቅኝ አገዛዝና ዘር ላይ ያተኮረ ቅኝ ግዛት ላይ ያለውን የኒዮ-ሊበራል አዝማሚያን ወይም ርዕዮተ-ዓለምን በመለወጥ ወደ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድርጅት እንዲመለስ ማበረታታት ነው፡፡ ይህንን ሀሳብ ለመደገፍ የሚናገሩ ብዙ ሰዎች የኢኮኖሚ አቅም እና ዕድገትን በማፋጠን እና በጣም አስፈላጊ የሚሆነው በተለይ የተጐዱትን በመተው ነው:: ማንኛውም ሰው በተለይ የአፍሪካ አገራት ነዋሪዎች እንደ ሰው የሚያስፈልጋቸው ነገር ተሟልቶላቸው የሚኖሩ አደሉም፡፡ ነገር ግን የተሻለ ሂወትና የኢኮኖሚ እድል ያስፈልጋቸዋል፡፡
የሰው ልጅ በጉልበት ሥራ ብቻ የሚኖር አይደለም፡፡ ሰው ውስብስብ፣ ማህበራዊ እና ተያያዥ ጉዳዮች ያሉት ነው፡፡ ሆኖም አጠቃላይ ያሉት ፍላጎቶች ወደ ገንዘብ ሊቀየሩ አይችሉም:: ማንኛውም ሰው የተለየ ፍላጎት እንዳለው የሚያጠያይቅ ጉዳይ አደለም፡፡ አፍሪካ የሚገኙ ነዋሪዎች በተወለዱበት ቦታ ላይ በድህነት እየማቀቁ የሚኖሩ ናቸው፡፡ በአፍሪካ የሚኖሩ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ በተለያዩ አጋጣሚዎች ብጥብጥ የማስነሳት አስተሳሰባቸውን ማስወጣት እንደሚያስፈልግና በአፓርታይድ ወቅት የተሳተፉና የጥቁር አፍሪካ ንቅናቄ መሪ ስቲቭ ቢኮ ይናገራሉ፡፡
ቢኮ በቅኝ አገዛዝ እና የአፓርታይድ ስርዓት ወቅት የነበሩ ግጭቶችን የተመለከቱ ሲሆን፤ ከዛ የተረዱትም ቅኝ ግዛት የአገራትን ኢኮኖሚ እንደሚያደቅ ነው፡፡ ቅኝ አገዛዝም በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጥቁር ህዝቦች ላይ ያደረሱባቸው የአእምሮ ብረዛ አለ፡፡ የአፓርታይድ አገዛዝ አላማው ጥቁር ህዝቦችን ማፍረስ ነበር፡፡ ይህም በቀላሉ ሊንፀባረቁ እና በፖለቲካው ስርዓት ውስጥ እንዲታዩ እና በራሳቸው እንዳይተማመኑ በማድረጉ አቅመ ቢስ እና በአለመቻል ውስጥ እንዲቆዩ አድርጓል፡፡ ቅኝ ግዛት ማለት አንዱን ማኅበረሰብ እንዳይሰራ በማድረግ የሌላ ጥገኛ ማድረግ ስለሆነ፡፡
በጣም አስቸኳይ የሆነው በዘመናዊ መንገድ የሚደረገው ቅኝ ገዥነት በጣም የሚስብ ሲሆን ታሪክንና እውነታን የደመሰሰ ነው፡፡ በአውሮፓ የሚደረገው ስደት በጣም አስቸጋሪ መሆኑ ቢታወቅም የአውሮፓ አገራት ስደተኞችን ለመቀበል ፍላጎት የላቸውም፡፡ ኑክ ወደ ማሕበረሰቡ እና ኢኮኖሚያዊ ማዕከል ጉዳዮች ውስጥ አይገቡም ነገር ግን ስደት ለወጣት አፍሪካዊያን ማራኪ መንገድ ነው ብለው አያምኑም፡፡ በጉልበታቸው ተበዝብዞና በባሕር ላይ የሚደርሰው ሞት ይበልጥ ወደ ቤት እንዲሄድ ያደርግ ይሆን?፡፡ በምዕራባዊ ኮርፖሬሽኖች እና መካከለኛው ምስራቅ መንግስታት ሰፊ መሬትን መያዝን በተመለከተ ኑክ ምንም የሚናገሩት ነገር የለም፡፡ በሳህል እና በአፍሪካ ምስራቃዊ የወደብ ባህር ዳርቻ ላይ የሚገኙትን ወጣቶች ወንጀል ለማስቆም ዓለም አቀፋ መንግስታት በአካባቢ መረጋጋት በሚል ሰበብ በቦታው እየሰፈሩ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ በቁጥሮች ላይ የተመሰረተ ጉዳይ አለ፡፡ አንዱና ዋነኛው ወደ አውሮፓ ለመሰደድ የሚሞክሩት አብዛኛዎቹ ሰዎች አፍሪካዊ ሳይሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ ዜጎች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 የአውሮፓ “የስደተኞች ቀውስ” በከፍተኛ ደረጃ ሲደርስባቸው ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩት ከአንድ ሚሊየን በላይ ከሚሆኑት ዜጎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት የመካከለኛው ምስራቅ እና በቅድሚያም ሶሪያውያን ነበሩ፡፡ ጀርመን በሶሪያ የመሳሪያ ሽያጭ በማድረግ የሶሪያ ሰዎች በማድረጉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነች፡፡ አውሮፓውያን ስደትን ለመቀነስ ጦርነት ማቆም ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ የአፍሪካ ከተሞች በኑክ የኢኮኖሚ አስተሳሰብ ውስጥ በመግባት ወደፊት ለሚሰሩት ስራዎች በርካታ ተግባራት እያከናወኑ ነው:: እውቅና ያላቸው ሰዎች ከሚኖሩበት አገር ከገጠር ወይም ከከተማ ነዋሪ የተሻለ መሰረተ ልማትና ቅድሚያ የማግኘት ዕድሎች አሏቸው:: ይህ ሁኔታ የስደተኞችን ቁጥር ጨምሮታል፡፡ በከተሞች አካባቢ የተማሩ ሰዎች እና ድሆች ላይ ልዩነት ፈጥሯል፡፡ በከተማ ድሀ ማህበረሰብ ላይ ደህንነታቸው ያለመጠበቅና የመብት ጥሰት ይደረግባቸዋል፡፡ የመብት ጥሰቱ የሚደረግባቸው እውቅና ያላቸውን ሰዎችን መብት ለመጠበቅ ተብሎ ነው፡፡
የአውሮፓ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ቅኝ ግዛት እንዲያደርጉ ያስቻሏቸውና በቅኝ ግዛት ምክንያት ማህበራዊ፣ ባህላዊ እና መዋቅራዊ ጉዳዮች ላይ የመጣውን ጉዳት ለተማሪዎቻቸው እንደማያስተምሩ ግልጽ ነው፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ ሴንቴልስ የተባለ ማህበረሰብ ከቅኝ ገዥዎች የተቃጣበትን ወረራ ለመከላከል የሌሎች አገራት ወጣቶችን መግደል ጀምሮ ነበር፡፡ የአውሮፓ የቅኝ ግዛት “ስልጣኔን የተላበሰ ተልእኮ” በሚል ያካሄደው ወረራ በመጨረሻም ምን ውጤት እንደነበረው ማስታወስ በቂ ነው፡፡ የቅኝ ግዛት መርዝ አሁንም ድረስ የሰው ልጅ ሰብዓዊነት እንዳይከበር፣ ኒዮ-ሊበራል እንዲስፋፋ እንዲሁም ዘመናዊ የቅኝ አገዛዝ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሰዎች መንቀሳቀስ በከፍተኛ ሁኔታ አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ ችግሩን ለመፍታት ጠንካራ እና የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን እውነታንና ታሪክን መካድ አይቻልም ምክንያቱም ባረጁ ፖሊሲዎች ከዘመኑ ጋር ለመዋሀድ መሞከር የተፈለገው ውጤት እንዳይመጣ አድርጎታል፡፡ በመጨረሻም ዘመናዊ ቅኝ ገዢነት እና የኑክ ሀሳብ ሌላው ነገር ደግሞ በፖሊሲ አውጭነት ውስጥ አስፈላጊ ሰዎችን ማስተባበር እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ ለእድገት የሚያስፈልገው ገንዘብን ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ መንገዱ የሚጠቁም የታሪክ መጽሐፍ ጭምር ነው፡፡
አዲስ ዘመን ህዳር 24/2011
በመርድ ክፍሉ
why should I be shy to show what chat with cam girls live wasnt ashamed to create?