አዲስ አበባ:- አብዛኛዎቹ ኢንዱስት ሪዎች ከሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተቋማት ጋር ከመሥራት ይልቅ በውጭ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን የማስጠናትና በውጭ ሰዎች ብቻ የማመን ችግራቸው አሁንም አብሯቸው እንዳለ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
የትምህርትና ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ኃላፊዎችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ ትናንት ሲካሄድ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ እንደገለጹት፤ በርካታ ተቋማት ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ይልቅ የውጭ አገር ተቋማትን የኢንዱ ስትሪዎቻቸው አጋር በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሥራት ይመርጣሉ።
የማማከር እና የትብብር ሥራዎች ሲፈልጉ በአገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊከናወን የሚችል ቢሆንም እንኳን የውጭውን የማማተር ችግር አለባቸው። የሚኒስቴሩ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ቴክኖሎጂ ሽግግር የዩኒቨርሲቲ ትስስር ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸው እ ን ደ ገ ለ ጹ ት ፤ ኢ ን ዱ ስ ት ሪ ዎ ቹ ከኢትዮጵያውያን ምሁሮች ጋር አብሮ የመሥራት ልምዳቸው ውስን ከመሆኑ ባሻገር አንዳንዶቹም ላይ ደግሞ ጨርሶ የለም።
በመሆኑም ልምዱ እንዲጎለብት ከኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ተማሪ በማሰልጠን እና ልምድ በመስጠት የሚሠሩትን የሚያበረታታ አሠራር ያስፈልጋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው፤ አብሮ ያለመሥራቱ ምክንያት ከሁለቱም ወገኖች ማለትም ከኢንዱስተሪዎችም ሆነ ከዩኒቨርሲቲዎች የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢንዱስትሪዎቹ በሀገር ውስጥ ዕውቀት ያለመተማመን እና የውጭ ዜጎች ላይ እምነት የመጣል የቆየ ችግር እንዳለባቸው ገልጸዋል። እንደ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ገለጻ ከሆነ፤ የዩኒቨርሲቲ ምሁሮች በበኩላቸው የኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት እንደሚችሉ የሚያሳይ ምርምር በማከናወን ረገድ ውስንነት አለባቸው።
በመሆኑም የዩኒቨርሲቲ ምሁራንም በውጭ ዜጎች የሚከወኑ ተግባራትን በራሳቸው አቅም እንደሚፈጽሙ ሠር ተው ማሳየት አለባቸው። የካንጋሮ ጫማ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እዮብ አርጋው እንደገ ለጹት ደግሞ፤ ኢንዱስትሪው ላይ የሚያስፈልገው ቴክኖሎጂ እና ክህሎት አገር ውስጥ የማይገኝ ከሆነ ወደ ውጪ መማተሩ አይቀርም። ለአብነት የጫማ ኢንዱስትሪው ላይ ያለው የዩኒቨርሲቲ ዕውቀት በቂ ባለመሆኑ የውጭ አገራት ባለሙያዎች ጋር መሥራቱ አዋጭ ሆኖ ተገኝቷል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 5/2011
ጌትነት ተስፋማርያም