በስሜን ብሄራዊ ፓርክ አምባ አካባቢ የተነሳው ሰደድ እሳት በቁጥጥር ስር ውሏል
አዲስ አበባ፡- በስሜን ብሔራዊ ፓርክ ዳግም የተነሳውን ሰደድ እሳት ለማጥፋትና ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ስድስት እሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖች ከደቡብ አፍሪካ ለማስመጣት ውይይት መደረጉን እና ሊመጡ ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ ቃጠሎን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በስሜን ብሔራዊ ፓርክ ዳግም የተነሳው ሰደድ
ዳይሬክተሩ አውስተው፤ በኬንያ ተራራማ አካባቢዎች እሳት ቃጠሎ በመከሰቱ ምክንያት በወቅቱ ሊደርሱ እንደማይችሉ ተናግረዋል።
ደቡብ አፍሪካና ፈረንሳይ የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ለመላክ ይሁንታቸውን በመግለ ጻቸው ለጊዜው ከደቡብ አፍሪካ ስድስት እሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖች እንደሚመጡና እሳቱ ሙሉ ለሙሉ መጠፋቱ እስከሚረጋገጥ ድረስም እንደሚቆዩ አመልክተዋል።
የፓርኩን የሰደድ እሳት ቃጠሎ በተመለከትም አቶ ኩመራ እንዳብራሩት፤ በተራራው አምባ የተነሳው ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ውሏል። ወደ ገደሉ የገባው እሳት ግን ማጥፋት አልተቻለም። ወደ ቆላው እና ወደ ጫካው እንዳይስፋፋ በአዳርቃይ ወረዳ በኩል የእሳት መከላከያ መስመር በአካባቢው ህብረተሰብ ተሳትፎ እየተቆፈረ ነው ብለዋል።
የፌዴራል መንግስቱ በፓርኩ ዳግም የተ ነሳውን እሳት ለማጥፋት እሳት ማጥፊያ አው ሮፕላን ለማስመጣት ጥረት ከማድረጉ በተጨማሪ በማስተባበር፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ እሳቱን በማጥፋትም ከሰባት ሺ በላይ የአካባቢውና በአቅራቢያ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ርብርብ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
እስካሁን በፓርክ ባለሙያዎች መረጃ መሰረት በፓርኩ አስከፊ ጉዳት አለመድረሱን ጠቁመው፤ በአጥቢ እንስሳት ማለትም የዋሊያ፣ የቀይ ቀበሮና የጭላዳ የሞት አደጋ አለማጋጥሙን አብራርተዋል።
ባለፈው መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በስሜን ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው እሳት ለሳምንት ያህል ቆይቶ መጥፋቱ አይዘነጋም። በወቅቱም 342 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት የፓርኩ ክፍል ተቃጥሏል። እንደገና ያገረሸው የእሳት ቃጠሎ ምን ያህል ውድመት እንዳደረሰ እስካሁን አልታ ወቀም። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እ.ኤ.እ በ1978 በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበ ነው።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2011
በጌትነት ምህረቴ