
በኡጋንዳ መስከረም ላይ የኢቮላ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ 109 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችና 30 ሞቶችን መዝገባቸውን የኡጋንዳ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስከ ሰኞ ዕለት ድረስ 15ቱ ሞቶች የተመዘገቡት በዋና መዲናዋ ካምፓላ ነው።በአገሪቱ ዋና መዲና ካምፓላ ውስጥ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ስድስት ሕጻናት በኢቦላ መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ስድስቱ ሕጻናት በቫይረሱ ሊያዙ የቻሉት በኋላ ላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ አንድ ዘመዳቸው በቫይረሱ ከተጠቁ አካባቢዎች መጥተው እነርሱ ጋር ካረፉ በኋላ እንደሆነ የጤና ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።የህክምና ባለሙያዎች ቫይረሱ ወደ ካምፓላ እንዳይዛመት ለመከላከል ለሳምንታት ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ቫይረሱ ሕዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች በፍጥነት የሚዛመት ሲሆን ይህ ‘ሱዳን ስትሬን’ ተብሎ የሚጠራው የኢቦላ ቫይረስ እስካሁን ክትባት አልተገኘለትም።በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የወረርሽኙ ማዕከል የሆኑት ሙቤንድ እና ካሳንዳ ወረዳዎች ከሌሎች አካባቢዎች ተለይተው እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር።በአገሪቷ መስከረም ላይ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ የኡጋንዳ የጤና ሚኒስቴር 109 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችና 30 ሞቶችን መዝግቧል። እስከ ሰኞ ዕለት ድረስ 15ቱ ሞቶች የተመዘገቡት በዋና መዲናዋ ካምፓላ ነው።
የአገሪቷ ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ከጤና ባለሙያዎች በቀላሉ ስለሚተላለፈው በሽታ ለሚሰጡት ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች እርምጃ ለመውሰድ ዘገምተኛ በመሆናቸው አንዳንዶች ስጋታቸውን ገልጸዋል።የጤና ሚኒስትር ጄን ሩት አሴንግ፣ ሕዝብ በስፋት በሚንቀሳቀስባቸው ከተሞች አካባቢ የቫይረሱ ስርጭት ስጋት እንዳሳደረባቸው ተናግረዋል።
በዋና መዲናዋ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ስድስቱ ሕጻናት ስምና እድሜ ማንነታቸውን ለመጠበቅ ሲባል አልተጠቀሰም።ይሁን እንጂ እነዚህ ሕጻናት የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች አለመዘጋታቸው ታውቋል።ሚኒስትሯ ዶክተር አሴንግ እንዳሉት በቅርቡ በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች መካከል ታማሚዎችን ሲያክሙ በቫይረሱ የተያዙ ስድስት የጤና ባለሙያዎች ይገኙበታል። ካምፓላ የአገሪቷ የንግድ ማዕከል ስትሆን የኢቦላ ቫይረስ በፍጥነት ከተዛመተ ወደ ሌሎች አገራት የመዛመት እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 18/2015