የጥቅምት 2011ዓ.ም አበይት ክንውኖች
•ጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ.ም፡- የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። በዚህ ወቅትም በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ ፕሮጀክቶችን በፋይናንስ በማጠናከር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማጠናከር ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
•ጥቅምት 4 ቀን 2011 ዓ.ም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአዲሱን ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መጀመር አስመልክተው ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የዘንድሮ ተመራቂዎች የምታዘጋጁአቸው የጥናት ወረቀቶችና ፕሮጀክቶች በጥረታችሁ አምጣችሁ የምትወልዱት እንጂ ሌሎች የለፉበትን የምትሰርቁበት ዓመት እንዳይሆን ከወዲሁ ራሳችሁን አዘጋጁ ብለዋል። “በተሰረቀ ምርምር ሲመረቁ የሚለብሱት ጥቁር ገዋን ይኮሰኩሳል እንጂ አይለሰልስም፤ የምስክር ወረቀቱ የውርደት እንጂ የኩራት ሊሆን አይችልም፤ ይህንን አውቃችሁ በእውነት ተማሩ፤ ተመራመሩ፤ ወገባችሁን አጥብቃችሁ ታጠቁ” ሲሉም መክረዋል።
•ጥቅምት 5 ቀን 2011ዓ.ም፡- የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሶስት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ በኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና በቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተመረቀ።
•ጥቅምት 5 ቀን 2011ዓ.ም፡- 11ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለዴሞክራሲዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተከብሮ ዋለ።
•ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም፡- የስሎቬንያው ፕሬዚዳንት ባሩት ፓሆር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ተገኙ። ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ጉዞ አድንቀዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2011
Super-Duper blog! I am loving it! Will come back again. I am taking your feeds also.