የግንባታው የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት እለት – መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም፤
• የግንባታው ስፍራ፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉባ ወረዳ፤
• የዋናው ግድብ ከፍታ – 145 ሜትር
• የዋናው ግድብ ርዝመት – 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር
• የዋናው ግድብ ውፍረት – የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር
• ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን – 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር
• ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት – 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር
• ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር
• የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ከፍታ- 50 ሜትር
• የኮርቻ ግድብ /Saddle Dam/ ርዝመት 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር
• ግድቡ16 የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች አሉት፤
• እያንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የኃይል መጠን ከ375 እስከ 400 ሜጋ ዋት፤
• ጠቅላላ ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚያመነጨው ኃይል መጠን፡-6 ሽህ 450 ሜጋ ዋት
• ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላል፤
• ከ10 ቶን በላይ ዓሳን ማምረት ያስችላል፤
• 74 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለው፤
• ከ40 በላይ ደሴቶች ይኖሩታል።
• ከግድቡ የውሃ ላይ የትራንስፖርት፣ የአሳ ልማትና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ አገልግሎት ይውላል።
• ታዳሽ ኃይል በመሆን የከባቢ ብክለትን ይከላከላል።
• የከተሞችን ተሞክሮ በመቀመር በአዲሱ የህዳሴ ሐይቅ ዙሪያ ዘመናዊ ከተማ ለመመስረት ያስችላል።
• አጠቃላይ ግንባታው የደረሰበት ደረጃ- 66.26%፤
• ግድቡ በትልቅነቱ በአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዟል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2011