በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና እና ህዝብች ክልል በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ህገመንግሰታዊ መብታችን ይከበርልን በሚል የተካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁ ታውቋል።
በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ባደረሰን መረጃ መሰረትም፤ በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት፣ የዞኑ አስተዳደር፣ የከተማዋ ከንቲባና የወጣቶች ተወካዮች ንግግር ካደረጉ በኋላ ሰልፈኞቹ ወደየመጡበት በሰላም ተመልሰዋል።
ሰልፍ ላይ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫውቻ፤ የሲዳማ ህዝብ በክልል ተዋቅሮ ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ማውቅረብ ከጀመረ 130 ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረ መሆኑን አንስተው፤ በህገመንግስቱ መሰረት ምላሽ መሰጠት እንዳለበትም ነው የተናገሩት።
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፤ የሲዳማ ህዝብ ከወንድም እና እህት ህዝብ ጋር መኖርን መቼም የማይዘነጋ ህዝብ ነው ብለዋል። ሰልፉ በህገመንግስቱ መሰረት ክልል የመሆን ጥያቄን ለማቅረብ የተካሄደ መሆኑን ገልጸው፤ ጥያቄው በአፋጣኝ መልስ ማግኘት እንዳለበት አሳስበዋል።
የሲዳማ ወጣቶችን(ኤጀቶ ) በመወከል ንግግር ያደረገው ወጣት ታሪኩ ለማ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ህዝቡ እያቀረበ ያለው ጥያቄ በአግባቡና በፍጥነት ሊመለስ ይገባል ሲል ተናግሯል።
ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች መካከልም “ለውጡን እንደግፋለን፤ ጥያቄዎችን እናቀርባለን!”፤ “የህግ በላይነት ህገመንግስታዊ መብታችን እውን ይሁን”፤ “ህገመንግስታዊ መብታችን በህገመንግስቱ ብቻ ይመለስ”፤ “የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ለማንም ስጋት ሊሆን አይገባም” የሚሉት ይገኙበታል።
ክፍለዮሀንስ አንበርብር – ሀዋሳ
ህገመንግሰታዊ መብታችን ይከበርልን በሚል በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ