የቫይረሱን ስርጭትም ሆነ አዲስ በቫይረሱ የመያዝ መጠን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ህመሞች ምክንያት የሚከሰተውን የሞት መጠን ከመቀነስ ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና በጣም ሰፊና የማይተካ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህሞ መዘናጋቱ እየበረታ ሲመጣ በተለይ ወጣቶች ከኤች አይ ቪ ይልቅ እርግዝናን እንደሚፈሩ ይነገራል፡፡ በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ እና በጋምቤላ እንዲሁም በማደግ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የቫይረሱ የስርጭት መጠን በጣም እየተንሰራፋ ያለባቸው አካባቢዎች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ዛሬም እንደከዚህ በፊቱ ኤች.አይ.ቪ.ኤድስ የሃገራችን ስጋት የመሆን ሁኔታ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም ሀገሪቷ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ሰፊ ሚና የነበራቸው ባለድርሻ አካላት፣ እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች አገራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ውስጥ በማድረግ አሁንም ተመሳሳይ የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡
የተቋሙ መረጃዎች እነደሚያሳዩት በአዲስ አበባ ያለው የቫይረሱ አጋላጭ ሁኔታዎች በርካታ ናቸው፤ ከነዚህም መካከል በአነስተኛ ስራዎች ላይ ተሰማርተው ያሉ እና ከመደበኛ ስራቸው ውጭ አጋላጭ በሆነው ተግባር ውስጥ የገቡ ሴቶች መኖራቸው ይጠቀሳል፡ ፡ በየኮንደሚንየሙ ለሴተኛ አዳሪነት ስራ ተከራይተው የሚኖሩ ሴቶች መበራከታቸው፣ የግለሰብ ቤቶች በመከራየት የተለያዩ የህበረተሰብ ክፍሎችን የሚያስተናግዱ ሴተኛ አዳሪዎች፣ በማሳጅ ቤቶች የሴተኛ አዳሪነት ስራ የሚያከናውኑ መኖራው፣ ከትምህርተ ገበታ ጎን ለጎንም የሚሰማሩ ተማሪዎች መኖር ከአጋላጭ ምክንያቶች ውስጥ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የቫይረሱን ስርጭትም ሆነ አዲስ በቫይረሱ የመያዝ መጠን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ህመሞች ምክንያት የሚከሰተውን የሞት መጠን ከመቀነስ ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና በጣም ሰፊና የማይተካ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህሞ መዘናጋቱ እየበረታ ሲመጣ በተለይ ወጣቶች ከኤች አይ ቪ ይልቅ እርግዝናን እንደሚፈሩ ይነገራል፡፡ በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ እና በጋምቤላ እንዲሁም በማደግ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የቫይረሱ የስርጭት መጠን በጣም እየተንሰራፋ ያለባቸው አካባቢዎች እየተስተዋሉ ነው፡፡ ዛሬም እንደከዚህ በፊቱ ኤች.አይ.ቪ.ኤድስ የሃገራችን ስጋት የመሆን ሁኔታ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም ሀገሪቷ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ሰፊ ሚና የነበራቸው ባለድርሻ አካላት፣ እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች አገራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ውስጥ በማድረግ አሁንም ተመሳሳይ የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡
ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባልነታችን ሚና መወጣት አለብን፤ ተቋማትም የመከላከሉንና የመቆጣጠሩን ስራ የስራቸው አካል አድረገው ህዝቡን ተጠቃሚ በማድረግ በጋራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ አክለውም ቫይረሱን ስርጭት የመከላከልና የመቆጣጠር ስራም የአዲስ አበባ ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽ/ቤት ኃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ የትኛውም ዘርፍ በተለይ ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ ስራ ላይ የሚሰሩ ማህበራት ራሳቸውም ግንዛቤው ኖሯቸው በስፋት እንዲሰሩ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ግንዛቤ ከማሳደግና ተመርምሮ እራስን ከማወቅ ጀምሮ የመከላከሉ ስራ ላይ እያንዳንዱ የየዘርፉ መስረያ ቤትም ሚናውን እንዲጫወት ምክር ቤቱ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
በተያያዘም በተላይ በፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች አካባቢ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በስፋት መስራት አስፈላጊ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለተማሪ አገልግሎት ክሊኒኮች የምርመራ አገልግሎትና ለምርመራ አስፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶችን ማሟላትና ለባለሙያዎች ተገቢውን ስልጠና ከመስጠት ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች ይነሳሉ፡፡ ዩኒቨርስቲዎች ተጋላጭ ከሚባሉና የቫይረሱን ስርጭት የመከላከል ስራ ሊሰራባቸው ከሚገባ አካባቢዎች በመሆናቸው በምክር ቤቱ ያለው የድጋፍ ሁኔታ መጠናከር ይኖርበታል፡፡ በተላይ አፍላ እድሜ ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ላይ የስርጭቱ ግንዛቤ በስፋት ካልተሰራ ከላይ እንደተገለጸው ወጣቱ ከቫይረሱ ይልቅ እርግዝናን ስለሚፈራ በከተማዋ ላለው የስርጭት መጠን መጨመር አንዱ ምክንያት ሊሆንም ይችላል፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም በአቅራቢያው ካሉ የአስተዳደር እርከኖች ጋር በጋራ በመስራት ድጋፍና ክትትልም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ኤች.አይ.ቪ/ኤድሰ ከሴቶች ቀጥሎ ከፍተኛ ሁኔታ እያጠቃ ያለው ወጣቱን ስለሆነ ወጣቱ ላይ በስፋት መሰራቱ ተገቢ ነው፡፡ በተለይ በአፍላ እድሜ ላይ ያሉ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ተማሪዎች የምርመራ አቅርቦት ምቹ መሆን አለበት፡፡ መድሃኒትና የህክምና መሳርያዎች አስመጪ ድርጅት ጋር በመሆንም አቅርቦቱን በማሻሻል ሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምከር ቤቱ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለበት ፡፡ የምክር ቤት አባሉም ችግሩ እንዲፈታ ግፊት በማድረግ መጎትጎትና መጠየቅ ይኖርበታል፤ እንደ አንድ የሕዝብ ተወካይም ከቤተሰብ በመነሳት ማህበረሰቡን እንዲሁም በስራ ቦታዎች አካባቢ መዘናጋት እንዳይኖር ስለ ቫይረሱ መነጋገር ያስፈልጋል፡ ፡ ህብረተሰባችንም ወቅታዊውን መረጃ አውቆ ለአፍታም ቢሆን ሳይዘናጋ በየተሰማራበት እና በሚያገለግልበት ማህበራዊ አገልግሎት ላይ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
ቫይረሱ በደም ውስጥ ቢኖርም የቫይረሱ ቁጥር አነስተኛ በሚሆንበት ጊዜ በደም ምርመራ ላይገኝ ስለሚችል፤ ይህም ህብረተሰቡን እያዘናጋው ጠፍቷል ወደ ሚል ድምዳሜ እየሄደ ነው በተቃራኒው ግን ችግሩ ውስጥ ውስጡን እየተስፋፋ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ስለዚህ በሁሉም ማህበረሰብ ከቤተሰቡ ጀምሮ በግልጽ በመነጋገር እና ውይይት በማድረግ ቤተሰብን እና ልጆችን ከቫይረሱ መጠበቅ ያስፈልጋል፡ ፡ ከዚህም ውጪ ይበልጥ ተጋላጭ የሚባለው የህብረተሰብ ክፍል በተላይ የሴተኛ አዳሪ፣ የመጠጥ ቤቶች እና የአረቄ ቤት ሰራተኞች፣ ለሺሻ ጫትና ለተለያዩ ሱሶች የተጋለጡ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም በተለይ በዚህ ዙርያ ያሉ እና ቫይረሱ በደም የተገኘባቸው ወገኖች ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ተገቢውን ምርመራ አድርገው ቫይረሱ ካለም ተገቢውን የጸረ ኤች አይ ቪ ህክምና በማድረግ እራስንም ሌሎችንም መጠበቅ ይገባል ፡፡
የጤና አገልግሎትም በተገቢው ማግኘት መቻል አለባቸው፡፡ እንዲሁም በኮንደሚኒየም ቤቶች አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየታዩ ያሉትን አባባሽ የሆኑ ተግባሮች በመንግሥት በኩል ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል፡፡ ተማሪዎችም መዘናጋት መቻል የለባቸውም፤ መምህራን ደግሞ በይበልጥ ሰፊውን የወጣት ክፍል እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍል የሚያገኙ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ የማይተካ ሚና መጫወት ይችላሉ ከፍተኛ ኃላፊነትም አለባቸው፡፡ በማጠቃለያም በየመድረኩ እና በየሚዲያው ይሄንን የዘመቻ ስራ ብቻ ሳይሆን የዘወትር ስራቸው አድረገው በትኩረት ማህበራዊ ግዴታን መወጣት መብታቸውን ማስከበር እና አዎንታዊ ጫና መፍጠር፤ እንዲሁም ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው እንዲነጋገሩ የማድረግ ሁኔታም መኖር አለበት፡፡ ከተቋማትም ጋር በቅርበት እና በቅንጅት መስራት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
በተቋም ደረጃም በእያንዳንዱ ስራቸው ውስጥ ኤች.አይ.ቪ መከላከልን ማካተት እንዲሁም በጀት በመመደብ መከላከል ድጋፍና እንክብካቤ ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡ በተመሳሳይም በግለሰብ ደረጃ ራስን ማወቅ ለሌሎች መኖር መማርና ማወቅ ያስፈልጋል፤ በቤተሰብ ደረጃም ልጆችን ማስተማር እና መወያየት መልካም ስብዕና ያለው ዜጋ ማፍራት እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃም በየሃይማኖት ተቋማቱ በየትምህርት ቤቱ ዜጎችን የማነጽ መልካም ዜጋ የማፍራት እና ህብረተሰቡን በባለቤትነት ማስያዝ ተገቢ ነው፡፡ በአመራር ደረጃም ትኩረት ሰጥቶ መምራት የአገር ውስጥ ሃብት መመደብ እና ተጠያቂነት ማስፈን ለቫይረሱ ስርጭትና አጋላጭ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 10/2011
በኃይሉ አበራ