የወራቤ ከተማ ጎዳናዎች በህዝብ ጎርፍ ተሞልተዋል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በወራቤ ከተማ ጎዳናዎች የሚተመውን ህዝብ ያስተዋለ እንግዳ ሰው፤በእንግዴ ስሜት መዋጡ አይቀሬ ነው። ከአራቱም አቅጣጫ የሚተመው ህዝብ በአንድ ልብ መዳረሻውን ወራቤ ስታዲየም ያደረገ ነበር። በወራቤ ጎዳና የሚተመውን ህዝብ ተከትለን ስናቀና መዳረሻችን ያደረግነው የወራቤ ስታዲየም ነበር። በስታዲየሙ ዙሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸው ባነሮች ተሰቅለዋል ።የተለያዩ መልዕክቶች በተከሸሙት ባነሮች ሞገስ የተጎናጸፉ የዶክተር ዐብይ አህመድ በርካታ ፎቶዎች ይስተዋላሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን በከተማቸው መገኘት ተከትሎ የወራቤን ጎዳና ካጥለቀለቀው ታሪካዊው ሁነት በስታዲየም ተገኝተው ለመታደም ከሚጣደፉት ብዙ ሺ ወጣቶች መካከል በስልጤ ብሄረሰብ አልባስ የተዋበው ወጣት ከሪም ሬድዋን ህዝቡ ከመሪው ጎን የመቆሙን ምስክርነት ታላቅ ወኔ በተሞላ ድምጸት እንዲህ ሲል ገልጾልናል።
“የስልጤ ህዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንደሚቆም «መደመር መንገዳችን ብልጽግና መዳረሻችን» በሚል አጋርነቱን አረጋግጧል።” ወጣቱ ሙህዲን በበኩሉ «መንግሥት ሀገርን ከብልጽግና ማማ ላይ ለማድረስ በሚያደርገው ጉዞ በስልጤ ዞን የሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ አንዱ አካል መሆኑን ያምናል። ሀገርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በሚደረግ የለውጥ ጉዞ ውስጥ የህዝብን ጥያቄ ማድመጥና ምላሽም መስጠቱ ደግሞ በእጅጉ አስፈላጊ ነው ሲል ሀሳቡን ቀጠለ።
“በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትራችን እየሄዱበት ያሉት መንገድ ዛሬ አጋርነቴን ለመግለጽ ማልጄ ለመድረሴ ምክንያት ሆኖኛል። በተጀመሩት በጎ ለውጦች ውስጥ ደግሞ መሻሻልና መመለስ የሚገባቸው በርካታ የልማት ጥያቄዎች የመኖራቸው ሀቅ የሚሸሸግ አለመሆኑንም በዚሁ ድምጸት አንስቷል።
በከተማችን ወራቤና አካባቢዋ ያለውን የመሰረተ ልማት ችግር በአብነት ብናነሳ ፤ጠቅላይ ሚኒስትራችን ለተለሙት የብልጽግና ጉዞ የችግር ጋሬጣ የሚፈጥሩ ናቸውና ምላሽ መስጠት ይገባል» ሲል የፊቱን ገጽታ ቅጭም በማድረግ ነበር የገለፀው።
የስልጤን ህዝብ የልማት ረሃብ በልቡ አንግቦ በመሪያቸው ላይ ያላቸውን ተስፋና ፍቅር ለመግለጽ በወራቤ ስታዲየም ከተገኙት የስልጤ እናቶች መካከል አንዷ ወይዘሮ ሰዓዳ ረዲ የዶክተር አብይ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ከሚሹት የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች መካከል መሰረተ ልማት ግንባር ቀደም ስለመሆኑ ሀሳባቸውን አጋርተውናል።
በወራቤና አካባቢዋ ሳንካ ከፈጠሩ የመሰረተ ልማት ችግሮች መካከል በተለይ ከመብራት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር በመንቀስ የተጽእኖው አድማስ ከፍተኛ ስለመሆኑ ምሬት በተሞላበት ሁኔታ ገልጸውልናል። ከመብራት ጋር ተያይዞ ያለው ችግር ልማቱን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል።
ወይዘሮ ሰዓዳ ንግግራቸውን በመቀጠልም በከተማችን ወራቤም ሆነ በዞናችን መፍትሄ ያጡ የመሰረተ ልማት ችግሮች በመኖራቸው የባለሀብቶቹ ልባዊ የለውጥ ፍላጎት መሬት ላይ እንዳይወርድ አድርጓል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። «በወራቤ ከተማና አካባቢዋ የብሄረሰቡ ተወላጆች በርካታ ቁጥር ያላቸው ፋብሪካዎችን መገንባት ችለው ነበር። ከኃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ አንዳንዶቹ ለኪሳራ ተዳርገው ሲዘጉ ፤ሌሎቹ ደግሞ ችግሩን ተሸክመው እየሰሩ ይገኛሉ። ይህ ችግር ከተማዋን ለማልማት ፍላጎት ያላቸውን አዳዲስ ባለሀብቶች ብቻ ሳይሆን የነበሩትን እያሸሸ ይገኛል» በሚል ነበር ወይዘሮ ሰዓዳ የችግሩን ጥልቀት ያስረዱን ።
በስልጤ ህዝብ ፍጹም በሆነና በሚደንቅ መልኩ ፍቅርና አክብሮት የተቸራቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ህዝቡ የልማት ረሃብ ሳያሸንፈው የሰጣቸውን ፍቅርና ድጋፍ በመረዳት «በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ እንደሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች ሁሉ የስልጤ ህዝብ ዛሬም ድረስ ያልተመለሱ የልማትና የመልካም አሰተዳደር ጥያቄዎች እንዳሉት መንግስት በትክክል ይገነዘባል። የስልጤ ህዝብ ከጎናችሁ ነን ሲል ሰልፍ የወጣውም የልማት ጥያቄ የለብንም ለማለት ሳይሆን የእድገት ጥያቄ የሚመለሰው በተደመረ ሀሳብ፣ በመተጋገዝና እንቅፋት ባለመሆን መሆኑን በማመን ነው» ሲሉ ለህዝቡ ያላቸውን አክብሮት ገለጸዋል።
ዶክተር ዐብይ የስልጤ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን በማመን «የተለያዩ መልኮች፣
አዲስ ዘመን የካቲት 13/2012
ዳንኤል ዘነበ