አዲስ አበባ፡- ለኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር መጠናከር ከሚያግዙ ውይይቶች ይልቅ ብሄር ተኮር አጀንዳ በሚናፈሱባቸው ጉባኤዎች ላይ የሚገኙ ታዳሚዎች ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ እንደሚስተዋልና ይህም መስተካከል እንደሚገባው ተጠየቀ፡፡
እናት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ማህበር ያዘጋጀውና ስለ አገር ሰላም የሚመክረው ጉባኤ ትናንት በኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደበት ወቅት የተገኙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና የሰብዓዊ መብት መምህር ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ፣ ‹‹ሰላም የሁሉ መሰረት ነው፣ ስለ ሰላም ተገናኝቶ መወያየትም የሚደገፍ የሚበረታታ መሆኑ ነጋሪ አያሻውም፡፡
ይሁንና በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላም፣አንድነትና ፍቅር መጠናከር ከሚያግዙ ውይይቶች ይልቅ ብሄር አሊያም መንደር ተኮር አጀንዳዎች በሚናፈሱባቸው ጉባኤዎች ላይ የሚገኙ ታዳሚዎች አዳራሽ ይጠባቸዋል›› ብለዋል፡፡
ይህ ፈፅሞ የተሣሣተ ምርጫ በመሆኑ ሳይውል ሳያድር መስተካከል እንዳለበት ያስገነዘቡት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ለአገር ሰላም መሆን ሁሉም የድርሻውን ማበርከት እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተውበታል፡፡ በተለይ ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን በሚደረግ ጥረት ግንባር ቀደም ተዋናይ የሆኑ የፀጥታ አካላትና መገናኛ ብዙሃን ኃላፊነታቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ መከወን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) መሪ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው፣ ስለ ሰላም ተቀራርቦ ከመወያየት ይልቅ ዳር ተመልካች በመሆን ሰላምን ማምጣት እንደማይቻል አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ሰላም በመወያየት ብቻ የሚረጋገጥ ብሎም የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ አይደለም›› ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ ዘላቂ ሰላም የሁሉንም ኃላፊነትና አጋርነት እንደሚሻ፣ ለዚህም እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ሚና ማበርከት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
አርቲስት አስቴር በዳኔ በበኩሏ፤ ስለ ሰላም አንድነትና ፍቅር መወያየት የሁሉም ኃላፊነት መሆን እንዳለበት በመጠቆም፣ ‹‹ይህን በማድረግም ሰላም ለማምጣት ከመትጋት ይልቅ ሰላም ሲደፈርስ ግጭቶች ሲቀሰቀሱ የሚያተርፉትን የሚያሰሉና ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙት ሕሊና አልባዎች ማሳፈር ያስፈልጋልም›› ብላለች፡፡
የማህበሩ መስራች ወይዘሮ አስቴር ስዩም በበኩላቸው፤መሰል መድረኮች ማዘጋጀት ያስፈለገው ዘላቂ ሰላምን በጋራ ለመፍጠር ብሎም ቂምና ቁርሾን ይቅር ተባብሎ አዲስ እርምጃን ለመራመድ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ስለ ሰላም ተገናኝቶ ለመወያየትም ሁሉም በሩን ክፍት ማድረግ እንደሚገባው አስምረውበታል፡፡
ማህበሩ በሰላም ጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ ለበርካታ ግለሰቦች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የመንግስታዊ ተቃማትና አመራሮች እንዲሁም ሀይማኖታዊ ተቋማት ጥሪ ቢያደርግም የተገኙት ግን በጣም ጥቂት ሆነው ተስተውለዋል፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 5/2012
ታምራት ተስፋዬ
prix du médicaments au Canada Fannin Thun acquista farmaci
medicamentos precio en Uruguay Pharmakern Cagnes-sur-Mer Medikamente von Ärzten in den Niederlanden empfohlen
medicamentos en venta libre en España AAA-Pharma Colmar médicaments sans ordonnance, livraison rapide
compra de medicamentos en Perú Arena Belp Opzioni di pagamento sicure per l’acquisto di farmaci
до чого сняться красиві гори з будинками до чого сниться дитячий велосипед
кататися
молитва щоб надати сили снилося що бився
Acheter de la médicaments en ligne : Conseils pratiques
Viofar Eferding Acheter de la médicaments de qualité certifiée
бүгін тіркеусіз тегін гороскоп арал теңізінің физикалық географиялық сипаттамасы, арал теңізі
флорасы күміс алқа қанша бала 2022, алтын
алқа күміс алқа 2022 оливейра – махачев бой смотреть полный бой, бой ислама махачева
полный бой смотреть онлайн
өлкетану бойынша ғылыми жобалар, ғылыми жоба тарих пәнінен 8..
назовите способы движения растений., сор по биологии 7 класс 3 четверть тема движение сыни пікірдің түрлері, сыни пікір
мақсаты философия мен философтың адам және қоғам өміріндегі рөлі., адам
және қоғам философиясы