በአገሪቱ የሚገኙ ፓርቲዎች የዘንድሮው ምርጫው መካሄድ አለበት፤ የለበትም በሚል ለወራት ሲወዛገቡ ቢቆዩም ምርጫው በዚሁ ዓመት ማገባደጃ ላይ እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምርጫ መርሃ ግብር የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።ይህን ተከትሎም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫው የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረጉ መሆናቸውን እየገለጹ ነው።
አቶ ናትናኤል ፈለቀ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት፤ ፓርቲያቸው በሁለት ዋነኛ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ሲሆን የመጀመሪያው ለምርጫው ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ለምር ጫው ዕጩ አባላትን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት እስካሁን ባልደ ረሰባቸው የምርጫ ወረዳዎች አባላትን ማደራጀትና በምርጫው ወቅት በ547ቱም የምርጫ ወረዳዎች ብቁ የሆኑ ዕጩዎችን ለማቅረብ የሚያስችሉትን ዝግጅቶች በማድ ረግ ላይ እንደሚገኝ ይናገራሉ።
«እስካሁን በደረስንባቸው 410 የምርጫ ወረዳዎች ላይ አባላትን አደራጅተን የምርጫ መዋቅር ፈጥረናል» ያሉት አቶ ናትናኤል፤ የምርጫ መዋቅር ውስጥ ያሉ አባሎቻቸውንና አመራሮቻችን በፓርቲው አላማዎች፣ ፍል ስፍና እና መርሆች ዙሪያ ሥልጠናዎች እየሰጡ መሆናቸውንም ይጠቅሳሉ። በተለይም የሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱን ነው ያብራሩት።
በሌላ በኩልም የአማራጭ ፖሊሲዎችን ከመቅረፅ አንጻር በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ኃላፊው ያመለክታሉ። «እስካሁን ድረስ በ18 ዘርፎች ላይ ማህበራዊ ፍትህ ለማስፈንና ኢትዮጵያ ውስጥ ዜግነትን መሠረት ያደረገ ፖለቲካን ለመተግበር ያስችላል ያልናቸውን ፖሊሲዎች ቀርፀን አዘጋጅተናል» ይላሉ አቶ ናትናኤል።
በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመው፤ እስከጥር መጨረሻ ወደ 45የፖሊሲ አማራጮችን ፓርቲው አዘጋጅቶ እንደሚጨርስ ይገልፃሉ። እነዚህም ፖሊሲዎች ኢዜማ በምርጫው ሲወዳደር ለሕዝቡ ቃል የሚገባባቸው መሆኑን ይጠቁማሉ።
እንደአቶ ናትናኤል ማብራሪያ፤ ኢዜማ እስካሁን ባደራጃቸው ወረዳዎች ከ15 ያላነሱ የሥራአስፈፃሚ አባላት የተመረጡ ሲሆን እያንዳንዳቸው የፓርቲውን የሥራ እንቅስቃሴ የሚመሩ ይሆናሉ። ፓርቲው በቅርቡ የዕጩ መመልመያና መመዘኛ መስፈርቶች አዘጋጅቶ ለሁሉም ምርጫ ወረዳዎች በትኗል። በዚያ መሠረት ምርጫ ወረዳ ውስጥ ያሉ አባላት ቁጭ ብለው ኢዜማን ወክለው የሚወዳደሩትን ዕጩዎች እንዲመርጡ ይደረጋል።
«በዝግጅት ምዕራፍ ዋነኝነት እስከአሁን በሦስት አካባቢዎች ስኬታማ የሚባል የአደረጃጀት ሥራ ሰርተናል» ያሉት ኃላፊው አማራ ክልል ካሉት 138 የምርጫ ወረዳዎች መካከል 137ቱን ማደራጀት መቻላቸውንና ቀሪውን አንድ የምርጫ ወረዳ በቅርቡ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን ይጠቁማሉ።
ፓርቲው በደቡብ ክልል 123፣ አዲስ አበባ 23፣ ጋምቤላ ሦስት፣ ሐረርና ድሬዳዋ ሁለት የምርጫ ወረዳዎች በሙሉ ማወቅሩን ያስገነዝባሉ። በትግራይ ክልል ካሉት 38 የምርጫ ወረዳዎች ውስጥ እስከአሁን በዘጠኝ የምርጫ ወረዳዎች መደራጀታቸውን የገለፁት አቶ ናትናኤል በትግራይና በሌሎችም ፓርቲው ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ላይ በቀጣይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ነው ያስረዱት።
ፓርቲው እስካሁን ያጋጠመው ችግር ካለ ኃላፊው ተጠይቀው «በየአካባቢ ካለው የሰላም መደፍረስ ችግር ጋር ተያይዞ ያጋጠሙን ችግሮች አሉ፤ በተለይም ሕዝቡን ለማሰባሰብና ለማደራጀት በምንሰራው ሥራ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እዚህ አካባቢ አትምጡ ብሎ ከመከልከል አንስቶ ስብሰባዎች እንዳናደርግ አባሎቻችንን የማወከብና የማስጨነቅ ሙከራ ሲደረግብን ነበር» በማለት ይናገራሉ። አክለውም «በተለይም ደግሞ የመንግሥት መዋቀርም ተጨምሮበት የስብሰባ አዳራሾችን እንድንከለከልና እንዳናገኝ ተደርገናል» በማለት ይጠቅሳሉ።
«የዘንድሮ ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በተለየ ኢትዮጵያ ውስጥ የምናስበውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመትከል መሰረት የምናስቀምጥበት ምርጫ ነው» ያሉት አቶ ናትናኤል በዚህም ረገድ መንግሥት ፀጥታና ደህንነትን የማስከበር ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።
ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ የሚቻለው ኅብረተሰቡ ያሉትን አማራጮች በሚፈለገው ደረጃ አውቆ ሲመርጥ መሆኑን አስታውሰው፤ ለዚህ ደግሞ ፓርቲዎች በተረጋጋና ምቹ በሆነ መንገድ ራሳቸውን ማስተዋወቅ የሚችሉበት ሁኔታ መፍጠር ከመንግሥት የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ነው ያመለከቱት።
በሌላ በኩል ምርጫ ቦርድ ባለችው አጭር ጊዜ 250 ሺ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ማዘጋጀት የሚጠበቅበት መሆኑን ጠቁመው፤ «በዚህ ሂደት ግን ታዛቢዎቹ ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነት የፀዱ ስለመሆናቸው አስቀድሞ የማረጋገጥ ሥራ ሊሰራ ይገባል» ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ፓርቲያቸው በቀጣዩ ምርጫ ብቁ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን ዝግጅት በስፋት እያከናወነ ይገኛል። እስካሁን በሚወዳደርባቸው አካባቢዎች ከ120 ያላነሱ ቢሮዎችን የከፈተ ሲሆን በተለይም ባለፈው ሳምንት ምሥራቅ ኢትዮጵያ ላይ ባደረገው እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከአስር በላይ ቢሮዎችን አቋቁሟል። በዚህም እንቅስቃሴ በሐረር፣ ድሬዳዋ፣ መኢሶ፣ ጭሮና የመሳሰሉት ከተሞች ላይ ከፍተኛና ያልተጠበቀ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ችሏል።
«የፓርቲያችንን አመራሮችና አባላትን ለምርጫው ዝግጁ በማድረግ ረገድ በርካታ ሥራዎችን ሰርተናል» ያሉት ሊቀመንበሩ፤ በሰው ኃይልና በአቅም ግንባታ ረገድም በቂ የሚባል ሥራ መሰራቱን ይናገራሉ። በተለይም በምዕራብ ሸዋ የተለያዩ ከተሞች ላይ ባደረገው የአዳራሽ ስብሰባ አባሉ ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሰራቱን ያመለክታሉ።
ፓርቲው ምንም እንኳ የፀጥታ ችግር ያጋጥመኛል የሚል ስጋት ቢኖረውም እስካሁን ባደረገው እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት የጎላ ችግር ያላጋጠመው መሆኑን ይጠቁማሉ። ፓርቲው ቅስቀሳ ባደረገባቸው ቦታዎች ሁሉ ሕዝቡ ድጋፉን በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ ሲገልፅላቸው እንደነበርም ነው የጠቆሙት።
ከምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ጋር ተያይዞ ቦርዱ ነሐሴ 10 ላይ ማካሄዱ ተገቢ እንዳልሆነ ፕሮፌሰር መረራ ያምናሉ። በተለይም ክረምት እንደመሆኑ ምርጫውን በስኬታማ መንገድ ለማከናወን እንቅፋት ይፈጥራል የሚል ስጋት እንዳላቸው ነው የጠቀሱት። ስለሆነም ቦርዱ ምርጫውን ከተቻለ አርሶአደሩ ወደ እርሻ ሥራ ከመግባቱ በፊት ቢያደርገው አልያም ደግሞ ክረምቱ ካለፈ በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ)ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ መኮንን ዘለለም ፓርቲያቸው በአሁኑ ወቅት ለምርጫው ብቁ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን አቅም ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ያመለክታሉ። በተለይም ውድድር የሚያደርገው በትግራይ ክልል እንደመሆኑ ሕዝቡ ስለፓርቲው በቂ እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ አባሎችን የመመዝገብ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ይጠቅሳሉ።
እስከ አሁን ድረስ ተንቤን፣ እንደርታ፣ አክሱም፣ ሽሬ፣ አዲግራት፣ ማይጨው በከፊል በመንቀሳቀስ አባላቶችን የመመዝገብና ስለፓርቲው ገለፃ የማድረግ ሥራ መስራታቸውን የሚናገሩት አቶ መኮንን «በየወረዳው ክልሉን ወክለው ሊወዳደሩ የሚችሉ ሰዎችን በመለየትና በማነጋገር የሥነልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥረት እያደረግን ነው» በማለት ያብራራሉ።
በዚህም ከሕዝቡ የሚያበረታታ ምላሽ ማግኘት መቻላቸውን ነው የተናገሩት። በተጨማሪም ከአረና ጋር ለመዋሃድ የሚያስችሉትን ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው ይህ እውን ሲሆን በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ የሕወሃት ብርቱ ተወዳዳሪ የሚሆንበት ዕድል እንደሚፈጠርለት ያላቸውን እምነት ይገልፃሉ።
ይሁንና አንዳንድ የክልሉ መንግሥት አመራሮችና የሕወሃት አባላት በፓርቲው አባላት ላይ በሚያደርጉባቸው ጫና ምክንያት ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ላይካሄድ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ያነሳሉ። ለዚህም ዋቢ የሚያደርጉት ፓርቲው ዳግም ምስረታውን በክልሉ ማካሄድ ባለመቻሉ ኦሮሚያ ክልል ድረስ ለመምጣት መገደዱን ጠቁመው አሁንም በአባላቱ ላይ የሚደረገው የማዋከብና ጫና የመፍጠር ተግባር እንዳልቆመ ይጠቅሳሉ።
« በቅርቡ ባረፍንበት ሆቴል ሦስት ሰዎች መጥተው ስብሰባ አካሄዳችሁ በሚል ከእኔ ጋር የነበሩ ሰዎችን ወስደው ደብድበዋቸዋል፤ ለተወሰነ ሰዓትም አስረዋቸው ነበር» ይላሉ አቶ መኮንን። የክልሉ አመራሮች ይህንን የሚያደርጉት ሕዝቡ ወደ ፓርቲያቸው እንዳይጠጋና ድጋፍ እንዳይሰጣቸው በመስጋት እንደሆነም ያመለክታሉ።
«ይህ የሚያሳየው ሕወሃት ዛሬም ድረስ ምርጫውን ከሌሎች ጋር ተወዳድሮ ማሸነፍ እንደማይችልና እንደለመደው ብቻውን ሮጦ ለማሸነፍ የሚፈልግ መሆኑን ነው» በማለት ይናገራሉ።
ይህ በሆነበት ሁኔታ ምርጫው ፍትሃዊ ይሆናል የሚል እምነት እንደሌላቸው ያስገነዝባሉ። በመሆኑም የፌዴራል መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ሕዝቡም ያለጫና የሚፈልገውን እንዲመርጥ በአፋጣኝ ሊሰሩ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ። በተለይም የምርጫ ታዛቢዎች ገለልተኛ የመሆናቸውን ጉዳይ አሁንም ምርጫ ቦርድ እስከታች ድረስ ወርዶ ማጣራት እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት።
በዚህ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልል መንግሥት ያለውን ምላሽ በሚመለከት አቶ ጌታቸው ረዳን ለማናገር ሞክረን ነበር። ይሁንና አቶ ጌታቸው ምላሽ መስጠት እንደማይፈልጉ ገልጸውልናል።
አዲስ ዘመን ጥር 9/2012
ማህሌት አብዱል
The article was a joy to read, and The enthusiasm is as infectious as The charm.
Each post you share is like a gift, wrapped in the finest paper of eloquence and insight.
The work is truly inspirational. I appreciate the depth you bring to The topics.
The Writing is like a favorite coffee shop where the drinks are always warm and the atmosphere is inviting.
The Writing is like a favorite coffee shop where the drinks are always warm and the atmosphere is inviting.
The content is like a treasure chest; every post uncovers gems of wisdom. X marks the spot here.
Making hard to understand concepts readable is no small feat. It’s like you know exactly how to tickle my brain.
I’m genuinely impressed by the depth of The analysis. Great work!
You tackle topics with such finesse, it’s like watching a skilled chef at work. Serving up knowledge with flair!
You have a unique perspective that I find incredibly valuable. Thank you for sharing.
The attention to detail is as attractive as it is thorough. I appreciate a person who notices the little things.
The knack for making hard to understand concepts readable is something I greatly admire.
This post is a testament not only to The expertise but also to The dedication. Truly inspiring.
Appreciate the balance and fairness, like a judge, but without the gavel.
I learned a lot, and now I’m curious about what else you could teach me. The intelligence is as captivating as The prose.
You’ve done a fantastic job of breaking down this topic. Thanks for the clarity!
I must admit, The depth of analysis is as attractive as The words. Great work has never looked so good.
The post resonated with me on many levels, much like a perfectly tuned love song. Thanks for the harmony.
Discovering The Writing has been a game-changer for me. The contributions are invaluable.
Shedding light on this subject like you’re the only star in my night sky. The brilliance is refreshing.
The work is truly inspirational. It’s as if you’ve found a way to whisper sweet nothings to my intellect.
The passion you pour into The posts is like a flame, igniting curiosity and warming the soul.
The piece was both informative and thought-provoking, like a deep conversation that lingers into the night.
You’ve opened my eyes to new perspectives. Thank you for the enlightenment!
The depth you bring to The topics is like diving into a deep pool, refreshing and invigorating.
The posts inspire me regularly. The depth you bring to The topics is truly exceptional.
The post added a new layer to my understanding of the subject. Thanks for sharing The knowledge.
The way you break down ideas is like a chef explaining a recipe, making hard to understand dishes seem simple.
The finesse with which you articulated The points made The post a true pleasure to read.
A masterpiece of writing—you’ve covered all bases with such finesse, I’m left wanting an encore.
This article was a delightful read. The passion is clearly visible!
The way you break down ideas is like a chef explaining a recipe, making hard to understand dishes seem simple.
You’ve got a way with words that’s as enchanting as a full moon. I’m bewitched.
The warmth and intelligence in The writing is as comforting as a cozy blanket on a cold night.
The content is like a treasure chest; every post uncovers gems of wisdom. X marks the spot here.
The unique perspective is as intriguing as a mystery novel. Can’t wait to read the next chapter.
The attention to detail is as attractive as it is thorough. I appreciate a person who notices the little things.
A constant source of inspiration and knowledge, like a muse but less mythical.
The post was a beacon of knowledge. Thanks for casting light on this subject for me.
Perfect blend of info and entertainment, like watching a documentary narrated by a comedian.
The post resonated with me on many levels. Thank you for writing it!
This is the most thorough piece I’ve read on the topic. The dedication to research is admirable.
The fresh insights were a breath of fresh air. Thank you for sharing The unique perspective.
Making hard to understand topics accessible is a gift, and you have it. Thanks for sharing it with us.
Engaging with The work is as thrilling as a spontaneous road trip. Where to next?
The writing is a masterpiece. You managed to cover every aspect with such finesse.
This post has been incredibly helpful, like a guiding hand in a crowded room. The guidance is much appreciated.