አዲስ አበባ፡-‹‹የፌዴራሊስት ኃይል›› የሚለው የህወሓት ፕሮፖጋንዳ ትላንትና ራሱ የፈጠረውን ችግር በማረሳሳትና በማዘናጋት እንደገና የአራት ኪሎን ወንበር እያሰበ መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉ አቶ ትግስቱ አወሉ ገለጹ።ጫፍ ከያዘውና ዋልታ ረገጥ ከሆነው የፌዴራሊስት ሀይሎች ፎረም ምክትል ሰብሳቢነት ራሳቸውን ማግለላቸውንም ተናግረዋል።
የአንድነት ለዴሞክራሲና የፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበርና በቅርቡ በመቐለ በተቋቋመው የፌዴራሊስት ኃይሎች ፎረም ምክትል ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፤ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ አስመልክተው ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የገዢው ፓርቲ አባል የነበረው ህወሓት ለፌዴራሊስት ኃይሎች ባዘጋጀው ስብሰባ ጥሪ ሲደርሳቸው ድርጅታቸውን ወክለው መሳተፋቸውንና የፎረሙ ምክትል ሰብሳቢ ተደርገው መመረጣቸውን አስታውሰዋል።
ነገር ግን በስብሰባው ሂደት ህወሓት ትላንትና የነበረውን ችግር በማስረሳት፤ አገዛዙን በሌላ የአደረጃጀት መንገድ ለማምጣትና እንደገና የአራት ኪሎን ወንበር በማሰብ እየሰራ መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም የህወሓት ዓላማ ከአገር ሠላም ጋር የማይሄድ በመሆኑ ራሳቸውን ከፎረሙ ማግለላቸውን አስታውቀዋል።
እንደ
አቶ
ትግስቱ
ማብራሪያ፤
የፌዴራሊስት
ሀይሎች
ፎረሙ
መድረክ
የሚያጠነጥነው
ብሄራዊ
ፌዴራሊዝምና
ህገ
መንግስቱን
ማዳን
የሚል
ሀሳብን
ሲሆን
የአደረጃጀቱ
ዓላማም
‹‹በፌዴራሊዝሙ
ማንነትህ
እየተነጠቀ
ነው››
በሚል
ሀሳብ
በደካማ
ጎን
ለመግባት
የሚደረግ
እንቅስቃሴ
ነው።ምንም
እንኳን
ህወሓት
የፌዴራሊዝም
ጉዳይ
አሳስቦኛል
ቢልም፤
ከዚህ
ቀደም
የነበረው
የራሱ
አካሄድ
ጸረ
ፌዴራሊዝም
የነበረና
አሁንም
ቢሆን
ይህ
ፕሮፖጋንዳ
የሚጠቀመው
ትላንትና
የነበረውን
ችግር
በማረሳሳትና በማዘናጋት እንደገና የአራት ኪሎን ወንበር በማሰብ ነው።በለውጥ ሂደት ውስጥ ህገ መንግስቱና የፌዴራል ሥርዓቱ ተንዷል የሚለው ህወሓት ቀድሞም ቢሆን ህገ መንግስቱን ሲተገብር አልነበረም።
አቶ ትግስቱ፤ ‹‹ህወሓት የትላንትና አገዛዙን በሌላ የአደረጃጀት መንገድ ለማምጣት በበረሀ በነበረበት ጊዜ የተለያዩ ድርጅቶችን በመሰብሰብ ግንባር እንደፈጠረ ሁሉ አሁንም ባማረ ከተማ ውስጥ ምልመላ እያደረገ ነው።ይህ የፎረሙ አደረጃጀት ከጥግ ወደ መሀል ለመግባት የቀየሱት ሌላ ስትራቴጂና የትላንቱን አስተሳሰብ መልሶ ለማምጣት የሚጠቀምበት ሥልት ነው። ‹‹መስመራችን ኃይላችን ነው›› ይላሉ።ይህ ማለት የሚከተሉት የአብዮታዊ ዴሞክራሲን መስመር እንደሆነ የሚገልጽ ነው።በመሆኑም ይህንን ሊደግፉ የሚችሉ ሌሎች ሀይሎችን ለመፍጠር ነው እየሰሩ ነው ያሉት›› ሲሉም አክለው ገልጸዋል።
‹‹ህገ መንግስቱን እናድን›› የሚለው የስብሰባው መሪ ሀሳብ በህወሓት የተነደፈ እንጂ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ተስማምተውበት ያወጡት አይደለም ያሉት አቶ ትግስቱ፤ በስብሰባው ህወሓት ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን ማለቱንና ይህ ማለት ደግሞ ከዴሞክራሲያዊ አማራጭ ውጭ ሌላ የሀይል አማራጭ እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
አካሄዱ ጫፍ የያዘና ዋልታ ረገጥ በመሆኑ ዴሞክራሲያዊ መንገድን የተከተለ አለመሆኑን አስታውቀዋል።ድርጅቱ አሁንም ቢሆን እኩልነት በሚል ስብስብ ውስጥ የበላይነት አስተሳሰቡን ለመጫን እየሞከረ መሆኑንም አስረድተዋል።
አቶ ትግስቱ፤ ስብስቡን በበላይነት የሚመራው ህወሓት የብልጽግና ፓርቲ አሃዳዊ ነው የሚለውም የብሄር ብሄረሰቦችን ቀልብ ለመሳብና የሀሳቡ አጋር ለማድረግ አዋጭ የመታገያ መንገድ ነው ብሎ በማሰብ መሆኑን አስታውቀዋል።
የፌዴራሊስት ኃይሉ ‹‹ጋብቻ ለመመስረት›› እየተንደረደረ እንጂ ፎረሙ እስካሁን ህጋዊ መሠረት እንደሌለው የጠቆሙት አቶ ትግስቱ በፎረሙ ውስጥ ያለው ስብስብ የተደበላለቀ አቋም ያለው በመሆኑ ቆም ብሎ ሊታይ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።ህዝቡም ቢሆን ከሚነገረው ትርክት ባሻገር የፖለቲካውን አንድምታ ማወቅ እንደሚያስፈልገው አስረድተዋል።
በፌዴራሊስት ሀይሎች ስብስብ ውስጥ የተካተቱት ፓርቲዎች በማንነት ፖለቲካና በመልክዓምድር ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ እሳቤ ያላቸው ሲሆኑ፤ አሁንም ቢሆን በብሔር የተደራጁ ድርጅቶችንና ሌሎች አገር አቀፍ ድርጅቶችን ለያይቶ የማየት ሁኔታዎች መኖራቸውን አቶ ትግስቱ ገልጸዋል።
በስብሰባዎች ሠላማዊ የሚመስል ነገር እንደማይታይ፤ በተለይ የሚጠቀሙባቸው ኃይለ ቃሎች ዴሞክራሲን የሚገልጹ አለመሆናቸው፤ ለምሳሌ ‹‹ተነስ ዝመት›› የሚል ቃል እንደሚጠቀሙና ይህ ቃል በአብዛኛው የአምባገነኖች ቃል መሆኑንም ጠቁመው፤ ህወሓት የትግራይን ህዝብ ባህሪ የማይወክል ነገር ግን የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑ ተዘንግቶ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ስጋት ነው ብሎ እንዲያስብ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የስብስቡ ዓላማ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና ከርሳቸው ድርጅት ተልዕኮ አንጻር የማይሄድ በመሆኑ የነበራቸውን የምክትል ሰብሳቢነት ኃላፊነትም ሆነ ድርጅታቸው በፎረሙ ውስጥ የነበረውን ተሳትፎ ማቋረጣቸውን ጠቅሰው፤ የፌዴራሊስት ፎረሙ ሀሳብ የሚስተናገድበት አግባብም ድርጅታዊ መስመርም እንደሌለው አጽንኦት ሰጥተዋል።የኢትዮጵያን ሰላም የሚያሳጡ መሰል ድርጊቶችን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመሆን እንደሚታገሉትም ገልጸዋል።
አዲስዘመን ጥር 1/2012
አዲሱ ገረመው