አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በእህት እና በአጋር ድርጅትነት የነበሩት ሰባት ድርጅቶች የብልጽግና ፓርቲን መቀላቀላቸውን በአወጡት መግ ለጫ አረጋገጡ።
እስካሁን ፓርቲውን የተቀላቀሉት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)፣ የኦሮሞ ዴሞክ ራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)፣ የአፋር ብሔራዊ ዴሞክ ራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)፣ የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ)፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) እና የጋምቤላ
ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) በጉባኤዎ ቻቸው ፓርቲውን ለመቀላቀል የወሰኑ ሲሆን የሶማሌ ዴሞክ ራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) ደግሞ በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ተወያይቶ ለመቀላቀል ወስኗል።
ድርጅቶቹ ሰሞኑን ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባዔ በብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብና ፕሮግራም ላይ በመወያየት ፓርቲውን ለመቀላቀል ወስነዋል። የኢህአዴግ እህት ድርጅት የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ውህደቱን በተመለከተ ዛሬ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።
ሌላው የግንባሩ እህት ድርጅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ደግሞ ጉዳዩን በሥራ አስፈጻሚና በማእከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ከመከረ በኋላ የወሰደውን የብልጽግና ፓርቲን ያለመቀላቀል አቋም በቅርቡ አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባዔ በመጥራት ጉባዔው የሚወስነውን የመጨረሻ አቋሙን እንደሚያሳውቅ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገልጸዋል።
አዲስ ዘመን ህዳር 18/2012
በጋዜጣው ሪፖርተር