የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለተለያዩ የሚዲያ አካልት የተቋሙን ባለአንድ ገጽ እቅድ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ጋዜጣዊ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅና ፍትህ ስርዓቱ የሚታዩ ማነቆችን ለመፍታት ተቋሙ ከመቸውም በላቀ ሁኔታ አገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የህግ እና የፍትህ ማሻሻያ ሰራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የወንጅል ድርጊቶችን ትኩረት ሰጥቶ መከላከል ተቋሙ የተሰጠውን አገራዊ ኃላፊነት ለማሳካት የባለ አንድ ገጽ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመው የእቅዱ መነሸ ሃሳቦችም የሕግ የበላይነት አለመረጋገጥና ደካማ ፍትህ ሥርዓት፣ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከፍተኛ ጥሰት፣ደካማ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ እና ሕገ ወጥነትና ስርዓት አልበኝነት በመከላከል እና በመቆጣጠር የሕግ የበላይነትና ፍትህ ሥርዓትን ግንባታን ማጠናከር፣የፍትህ አግልግሎትን አሰጣጥ በማሻሻል እና የሰው ሃብትን አቅም በመገባት ሶስት ቁልፍተ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት በህዘብና በመንግሰት አመኔታን ያተረፈ ጠንካራ ተቋም ለመገባት በመሰራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የባለአንድ ገጽ እቅድ በአገራችን የተጀመረውን ለውጥ ዳር ለማድረስ የሰብአዊ መብት ጥሰት በፈፀሙ ሰዎች የሕግ ተጠያቂነት የማረጋገጥ፣የታራሚዎችን መብት አያያዝ ማሻሻል፣ የይቅርታና ምህረት አሰጣጥ ሥርዓቱን በተሟላ መልኩ ለመተግበር፣ በማህበራዊ ድረ-ገጽ የሚታዩ የጥላቻ ንግግር ወንጅል ሕግ ማውጣትና መተግበር እንዲሁም ሕገ ወጥነት፣ስርዓት አልበኝነትና የመንጋ ፍትህ ለመቆጣጠር ከአሁን በፊት ታይተው የማይታወቁ ህጎችን የማርቀቅና የማሻሸል ስራዎችን አቅድ ለውጤታማ ለመሆን የሕግና የፍትህ አማካሪ ምክር ቤት በማጠናከርና የሰው ሀይል በማደራጀት በመስራት ይገኛል፡፡
ዳይሬክተሩ በጋዜጠኞች ለተነሱላቸው የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ዙሪያ መልስ የሰጡ ሲሆን የወንጀል ፍትህ አስተዳደርን በማጠናከር ህዝብና በመንግስት ንብረት የመዝበራ ግለሰቦችን እና በመንግሰት ፕሮጀክቶች ላይ የሚደረገው ምርማራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ሲል መረጃውን ያደረሰን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ነው፡፡