• ዛሬ ለመላው ኢትዮጵያውያን እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምፈልገው እኛ እንቀጥላለን።በምንሰራው ሁሉ የሀገራችንን ብልጽግና በሚያረጋግጡ ነገሮች የዚህችን ሀገር ታላቅነት በሚመጥን መልኩ ታሪክን ከዛሬ ጋር ለነገ በሚበጅ መልኩ በማስተሳሰር የኢትዮጵያን ብልጽግና በሚቀጥሉት አስር አመታት መሰረት የሚጀምረው ዛሬ መሆኑን አምነን በብርታት የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን።
• የሚያግዘን ካገኘን የወሩን በሳምንት እንጨርሳለን። የሳምንቱን በዕለት እንጨርሳለን። የሚያግዘን ከጠፋም የሳምንቱን በወር፣የወሩንም በአመት እየሰራንም ቢሆን እንቀጥላለን፣ ፈጽሞ ግን አናቆምም። የጀመርነውን ጨርሰን ሪቫን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም።
• የቻሉ ያግዙናል፤ ያልቻሉ ይተውናል፤ ያልገባቸው ይተቹናል፤ ያልፈለጉን ይቃወሙ ናል። እኛ ግን ወገባችንን ጠበቅ አድርገን የጀመርነውን ጨርሰን ሪቫን እቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም።
• ሰላም የግጭት አለመኖር ብቻ አይደ ለም። ሰላም በመግባባት ላይ የተመሠረተ ፅኑ አንድነታችን ነው፣ ሰላም መተማመናችን ነው። ሰላም በሁላችንም ፈቃድ ዛሬም የቀጠለ የአብሮነት ጉዞአችን ነው። ሰላም አለመግባባትና ተቃርኖዎችን በሰለጠነ መንገድ መፍታት የሚያስችለን መንገድና ግባችን ነው።
• ሀገራችን ፍትህ፣ ነፃነትና ሰላም የሰፈኑባት፣ ዜጎችዋ በሰብዓዊነት የሚተሳ ሰቡባት፣ በእህት ወንድማማችነት የተሳሰ ሩባት እንድትሆን እንፈልጋለን። ይህ ህልማ ችን ዕውን የሚሆነው ከእንቅልፋችን ነቅተን ስንሰራ ነው።
• አመለካከታችንን ከጥላቻ፣ ከቂም በቀል ስሜትና ከዘረኝነት ማፅዳት ይገባናል። በብሄር፣ በፆታ፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በሃይማኖት ወዘተ ያሉንን ልዩነቶች እንደ በረከትነታቸው በፍቅር በማስተናገድ ከልዩነቶቹ የሚነሳ አለመግባባት ቢኖር እንኳ ከፍትህ እንጂ ከበደል ጋር ባለመተባበር ሞራላዊ ዕይታዎቻችንን ልናስተካክል ይገ ባል።
• እንደ ተለያየ አገር ዜጋ በባእድነት እና ባይተዋርነት ሳይሆን፣ ሁላችንም እንደ ባለቤቶች እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዝ ይጠበቅብናል። ይህ ሲሆን ስንወድቅም፣ ስንነሳም በጋራ ይሆናል።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012