ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ወዲህ ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጠነ ሰፊ የማሻሻያ እርምጃዎችን በመውሰድ በህዝብ ቅቡል ያልነበረውን የመንግስት መዋቅር ከመቀየር አንስቶ ኢትዮጵያ በአካባቢው ከሚገኙ አገራት ጋር የነበራትን ግንኙነት በማሻሻላቸው ከፍተኛ አለም አቀፍ እውቅና ተችሯቸዋል።ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች በተጫማሪ የ2019 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል ። ለመሆኑ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የነበሯቸው የሰላም ጉዞዎች ምን ይመስሉ ነበር።
በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ፣ በአንዳንድ ተጻራሪ አመለካከት ባላቸው አካላት ጭምር፣ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎትን የቀሰቀሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጉዞ ከታሰበው በተቃራኒ መልካም አስተዳደርም ሆነ ሰላምን ሳያመጣ እንዳይከሽፍ ቢሰጉም እስካሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬቶች ዓለም ዓቀፍ ዕውቅናዎችን ማግኘት ጀም ረዋል።
ከእነዚህም መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፍተኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ስኬት ከኤርትራ ጋር የተፈጠረው ሰላም ነው። በዚህም የተነሳ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ በሁለቱ ችግር ምክንያት ደፍርሶ የነበረው ሰላም እንዲመለስና የሰፈነው የባላንጣነት ስሜት እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ሐምሌ20/2010ዓ.ም በአሥመራ ከተደረገው የሁለቱ ሃገራት መሪዎች የመጀመሪያ የፊት ለፊት ግንኙነት ወዲህ መሰረታዊ የሚባሉና ተቋርጠው የነበሩ የመገናኛ ግንኙነቶች በሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደገና ተጀምረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረውና ከኤርት ራና ሶማሊያ ጋር በመዳበል የሶስትዮሽ ግንኙነት የክፍለ አህጉራዊውን የጸጥታ ችግር በመቅረፍና ትብብርን በማስፈን ረገድ መልካም ጅምር የሚባልና ሊበረታታ የሚገባው ነው። የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲቀዳጅ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለተጫወቱት ሚና አለም አቀፍ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል። መሰረታዊ ለውጥ እን ዲመጣም ከተፈለገ ከሁለትዮሽ ግንኙነት በተ ጨማሪ ክልላዊና አህጉራዊ ተቋማት አይነተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ይታመ ናል።
ባለፈው አንድ አመት ኢትዮጵያ ከአረብ – ገልፍ ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል። የቀጣናው ሃያላን ሃገራት ማለትም ሳኡዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በሸምጋይነት ከመሳተፋቸውም በላይ ሁለቱ ሃገራት በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚና የወታደራዊ ትብብር አይነተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ብሎም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ዶላር መዋእለ ንዋይ እንድታፈስ ማድረግ ተችሏል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ስርአት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ለውጥ ተስተውሎበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት ሃገሪቱ የመፍረስና የመበታተን ከፍተኛ ስጋት አንዣቦባት እንደነበር ይታወሳል::
ዶክተር አብይ አህመድ በቀውስ የተናጠ ሃገር ነው የተረከቡት። ብሄርን መሰረት አድርጎ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ባለፈው አመት ብቻ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከሶሪያ በላቀ ሁኔታ የሃገር ውስጥ ከፍተኛ መፈናቀል የተስተዋለባት ሃገር አድርጓታል። በተጨማሪም በክልሎች መካከልና በክልሎች ውስጥ ያሉት ግጭቶች ተባብሰው በነበሩበት ሁኔታ ውስጥ ነበር ወደ ስልጣን ጉዟቸውን የጀመሩት።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ጥቂት ወራት በኋላ በርካታ ቀውሶች ስውር በሆኑ እጆች አማካኝነት እዚህም እዚያም ተቀጣጥለዋል።
እጅግ የከፋው ቀውስ በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልሎች ድንበር አካባቢ በሚገኙ ነዋሪዎች ዘንድ የተከሰተው ግጭትና መፈናቀል እንዲሁም በጉጂና ጌዲኦ አካባቢዎች የተከሰቱት ግጭቶች በርካታ ዜጎች ሲፈናቀሉ የብዙ ዜጎች ሃብትና ንብረት ከመውደሙ በተጨማሪ እርዳታ በአግባቡ እንዳይደርስ ጭምር ሲደረጉ ተስተውለዋል። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወሰዷቸው በሳል አመራሮችና ወደ ህዝቡም ቀረብ ብለው በሰሯቸው ተጨባጭ ስራዎች በአካባቢዎቹ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል። በሀገር ውስጥ ተፈናቅለው ከነበሩ ዜጎች ከ90 በመቶ በላይ ወደ ቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ህይወታቸውን በመምራት ላይ ይገኛሉ።
በአንጻሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሮችን ከስር መሰረታቸው ለመፍታት ከመጣር የብሄራዊ እርቅና ሰላም እንዲሁም የአስተዳደርና የድንበር ኮሚሽኖች የመሳሰሉትን የትርፍ ጊዜ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል። ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ከተፈለገ መንግስት ከጊዜያዊ መፍትሄ ባለፈ ተቋማትን ማጠናከርና በተለይም በቅርብ ጊዜ የተቋቋመውን የሰላም ሚኒስቴር በከፍተኛ ሁኔታ በማዋቀር ሁሉን አካታች የሆነ ሃገር በቀል እውነተኛ እርቅ በማህበረሰብ መካከል እንዲፈጠር የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012