የታይፎይድ ሕመም እያደጉ ባሉ ሀገሮች ውስጥ በተለይ በሕፃናት ላይ ከፍተኛ የጤና ጉዳት ሊያመጣ የሚችል የሕመም ዓይነት ነው። ሕመሙ የሚከሰተው ሳልሞኔላ ታይፊ በሚባል የባክቴሪያ ዓይነት ሲሆን ሕመሙ ከታማሚው ሰው ወደ ጤነኛው ሰው በተበከለ ውሃና ምግብ አማካይነት ይተላለፋል፡።
የሕመሙ ምልክቶች
•ሲጀምር መጠነኛ ሆኖ እያደር እየጨመረ የሚመጣ ትኩሳት
•የራስ ምታት
•መደካከምና የሰውነት መዛል
•የጡንቻ ላይ ሕመም
•ማላብ
•ደረቅ ሳል
•የምግብ ፍላጎት መቀነስና ክብደት መቀነስ
•የሆድ ሕመም
•ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት መከሰት
•የሆድ መነፋት የመሳሰሉት ናቸው።
ሕመሙ የሚተላለፍባቸው መንገዶች
የታይፎይድ ሕመምን የሚያመጣው ባክቴሪያ የሚተላ ለፈው በተበከለ ውሃ ወይም ምግብና አንዳንዴ ደግሞ ከታመ መው ሰው ጋር በሚኖረን ቀጥተኛ ግንኙነት አማካይነት ነው፡፡
ለሕመሙ የሚያጋልጡ ነገሮች
•የታይፎይድ በሽታ ሁሌ በሚታ ይባቸው አካባቢዎች መስራት ወይም መሄድ
- በታፎይድ ከተያዘ ሰው ጋር ቅርበት ያለው ግንኙነት (close contact) መኖር
- የተበከለ ውሃ መጠጣት (በተለይ ከተበከለ ቱቦ ጋር የሚገናኝ ከሆነ)
- የተበከሉ ምግቦችን መመገብ ናቸው፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ሕክምናዎች
ሕመሙን ለመፈወስ ብቸኛው መንገድ ፀረ-ባክቴሪያ መድኃ ኒቶችን መውሰድ ስለሚያስፈልግ የሕክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
የቤት ውስጥ ሕክምና
ፈሳሽ በበቂ መጠን መውሰድ/ መጠጣት፡- ይህ በትኩሳት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የሰውነት ፈሳሽ እጥረትን ሊያስቀር ስለሚችል ነው። ከመጠን በላይ የሆነ/ከመጠን ያለፈ የፈሳሽ እጥረት ካለዎ በደም ስር ፈሳሽ መውሰድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ስለሆነም ወደ ሕክምና ድርጅት መሄድ ያስፈልጋል፡፡
ታይፎይድን እንዴት መከላከል ይቻላል?
*የእጅ ንፅህናዎን መጠበቅ፡– ታይፎይድ ኢንፌክሽንን ለመከ ላከል አስተማማኙ መንገድእጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ ነው፡፡ ምግብ ከመመገብዎና ከማዘጋጀትዎ በፊት እንዲሁም መፀዳጃ ቤት ተጠቅመው ከወጡ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ ውሃ ማግኘት በማይ ችሉበት ወቅት አልኮሆል ያላቸው የእጅ ማፅጃዎች (ሃንድ ሳኒታዘሮች) መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
*ያልታከመ ውሃያለመጠጣት–
ታፎይድ የሚዛመተው በተ በከለ ውሃ ስለሆነ መጠጣት የሚ ያስፈልገው ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ አሊያም የታሸገ ውሃ ቢሆን ይመ ከራል፡፡
*ጥሬ የሆኑ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በደንብ በንፅ ህና አጥቦ መጠቀም፡– ይህን ማድረግ ካልቻሉና አትክልቱ ንፁህ በሆነ ውሃ ያልታጠበ ከሆነ አሊያም እርግጠኛ ካልሆኑ ጥሬ አትክልትና ፍራፍሬዎችን አለመጠቀም ይበጃል።
ምንጭ፡– ቴሌ ሜድ ሜዲካል ሰርቪስ
አዲስ ዘመን ሐምሌ 27/2011