ከዓለም የንግድ አባልነት ተጠቃሚ ለመሆን

አሜሪካ ስታስነጥስ የተቀረው ዓለም ጉንፋን ይይዘዋል እንዲሉ፤ የትራምፕ አስተዳደር ሰሞኑን ቀረጥን ወይም ታሪፍን ሲያስነጥስ ፓሲፊክንና አትላንቲክን ተሻግሮ እነ ቻይና፣ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ አውሮፓ እና ሌሎች ሀገራትን የቀረጥ ጉንፋን እየያዛቸው ነው። በዚህ የተነሳ ዓለማችን ወደለየለት የንግድ ጦርነት ልትገባ አንድ ሐሙስ ነው የቀራት።

ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎች እየተጣሱ፤ የዓለም ንግድ ድርጅትም በብርቱ እየተፈተነ ይገኛል። ሀገራችን ሰሞኑን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየተደራደረች ባለችበት እድሜ ለትራምፕ የድርጅቱ ህልውና ላይ ግን አደጋ ተደቅኗል። ከወደ አሜሪካ እየመጣ ያለው አደጋ ዓለም አቀፍ ዳፋ ስለሚኖረው ሀገራችን ሳትዘናጋ አበክራ ልትዘጋጅ ይገባል።

በፕሬዚዳንት ትራምፕ የታሪፍ ናዳ የተነሳ ዓለም አቀፉ ገበያ እየታወከና እየታመሰ ይገኛል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ውስጥ “ታሪፍ” እንደሚለው ቃል ደስ የሚል ቃል የለም በማለት ለታሪፍ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ። ለዚህ ይመስላል የታሪፍ ሰው tariff guy የሚል ቅጽል የተሰጣቸው።

ለመሆኑ የንግድ ጦርነት ምን ማለት ነው፤ የንግድ ጦርነት ማለት ሀገራት በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አለመግባባቶች ምክንያት ቀረጥ/ታሪፍ ወይም ሌላ የንግድ እንቅፋት የሚጥሉበት ሁኔታ ነው። የንግድ ጦርነቶች ለዘመናት ዓለም አቀፋዊ ንግድን በማዛባት ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዘዞችን አስከትለዋል። ሆኖም የንግድ ጦርነት ዛሬ የተጀመረ አይደለም። ጥንትም የነበረ እንጂ።

የመርካንቲሊስት ግጭቶች በመባል ከ16ኛው እስከ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተከሰተውን የንግድ ጦርነት በአብነት ማንሳት ይቻላል። የጊዜው የአውሮፓ ኃያላን ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቱጋል እና ኔዘርላንድስ በቅኝ ግዛት እና በንግድ የበላይነት ተወዳድረዋል። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን የሚገድቡ ፖሊሲ እንዲከተሉ አድርጓል። ከ1652 እስከ 1784 የተካሄዱ የአንግሎ-ደች ወይም በእንግሊዝ እና በኔዘርላንድ መካከል የባሕር ንግድ በበላይነት ለመቆጣጠር የተደረጉ ጦርነቶች መሆናቸውን የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ።

ከ1651 እስከ 1849 ሥራ ላይ ውሎ የነበረው የብሪቲሽ የአሰሳ ወይም የናቪጌሽን ሕግ የውጭ መርከቦችን ከቅኝ ግዛቶቿ ጋር እንዳይገበያዩ ይገድብ ነበር። በዚህ የተነሳ ከሌሎች የአውሮፓ ኃይሎች ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። ከሁሉም የንግድ ታሪፎች ግን ዛሬ ድረስ በግዝፈቱ የሚወሳው የ1930ዎቹ የስሞት-ሃውሊ ታሪፍ እና ታላቁ የኢኮኖሚ ቀውስ ነው።

ከ1929 የአክሲዮን ገበያ ውድቀት በኋላ በጣም ጉልህ ከሆኑት የንግድ ጦርነቶች ቀዳሚ ሆኖ ይጠቀሳል።አሜሪካ እኤአ በ1930 ኢንዱስትሪዎቿን ለመጠበቅ ከ20ሺህ በላይ በሆኑ ገቢ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ የጣለውን የስሞት-ሃውሊ ታሪፍ ሕግን አፀደቀች። ይሄን የአሜሪካ ድርጊት ተከትሎ ሌሎች ሀገሮች የአጸፋ ታሪፍ ጣሉ። በዚህ የተነሳ የዓለም ንግድ ከ60 በመቶ በላይ ቀነሰ።

ታላቁ የኢኮኖሚ ውድቀትም The Great Economic Depression ተባባሰ። ይህ ጦሰኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትን በመጎንቆሉ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ሊያዋልድ ችሏል። ከዚያ በኋላ የዓለም ንግድ ድርጅት በመቋቋሙ ላለፉት 80 ዓመታት የንግድ መቆራቆሶች እዚህም እዚያም ቢያገረሹም የከፋ ቀውስ ሳያስከትሉ ሊፈቱ ችለዋል። የትራምፕ አስተዳደር ይሄን የንግድ ሥርዓት ነው እያዛባና ዓለማችንን ወደ አልተፈለገ ኢኮኖሚያዊ ግብግብ እየወሰደ ያለው።

የአሜሪካ-ጃፓን የንግድ ውጥረት(1980-1990ዎቹ)፤ የአሜሪካ-ቻይና የንግድ ጦርነት (2018–አሁን)፤ የአሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት የንግድ ውዝግቦች መነሻ መካከል በተለይ ለቦይንግ እና ኤርባስ የሚደረጉ ድጎማዎች፣ በብረት ንግድ ላይ የተጣሉ ታሪፎች እና ዲጂታል ታክሶች ይገኙበታል።

ሩሲያ 2014 ላይ ክሬሚያን በወረራ ከተቆጣጠረች እና በዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች በኋላ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳና በሌሎች ኃያላን ሀገራት 26ሺህ ማዕቀብ ተጥሎባታል። እሷም የአጸፋ ርምጃ ወስዳለች። የዩናይትድ ኪንግደም ከአውሮፓ ሕብረት መነጠል በታሪፍ፣ በአሳ ማጥመድ መብት እና በንግድ እንቅፋት ላይ አለመግባባቶችን አስከትሎ እንደነበር አይዘነጋም።

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የንግድ ታሪፍ ሌሎች ሀገራትን ለአጸፋ ርምጃ በመጋበዝ የንግድ ጦርነትን ለኩሰዋል። በዚህ የተነሳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ውጥረት ተከስቷል። የሀገራት ግንኙነት ሻክሯል። የሽርክና ገበያው መረጋጋት ተስኖታል። ሸማቹ ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል። በዜጎች የሥራ ዕድል ላይ የስጋት ዳመና አንዣቧል።

ትራምፕ የታሪፉ ሰው እስከ መባል የደረሱት ታሪፍን እንደ መደራደሪያ መሳሪያ የማየት አባዜ ስለተጠናወታቸው ነው። በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው እንዲሁ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ የአልሙኒየምና የብረት ምርቶች ላይ ታሪፍ ጥለው ነበር። 100 ቢሊየን ዶላር በሚገመቱ የቻይና የቴክኖሎጂ፣ የግብርና፣ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ታሪፍ ጥለው ቻይናም በአጸፋው በአሜሪካ የግብርና ምርቶችና መኪናዎች ታሪፍ መጣሏ አይዘነጋም።

በሀገራት መካከል የሚደረግ የታሪፍ አጸፋዊ ምላሽ ነጮች ቲት-ፎር-ታት ይሉታል። በሸማቾች ላይ የዋጋ ጭማሪ እና የዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶች እንዲስተጓጎል አድርጓል። ከውጭ በሚገቡ ግብዓቶች ወይም ጥሬ ዕቃዎች የሚያመረቱ የአሜሪካ ፋብሪካዎች ለተጨማሪ ወጪ ከመዳረጋቸው ባሻገር ምርቶቻቸው ወደ ገበያ ሲገቡ ውድ ስለሚሆኑ ገዥ አያገኙም።

በዚህ የተነሳ ፋብሪካዎች ለኪሳራ ይዳረጋሉ። ሠራተኛ ይበትናሉ። ከሁሉም የከፋው የታሪፍ መዘዝ በገበያ ላይ ርግጠኛ አለመሆን፣ የሽርክና ገበያ መዋዠቅን እና ኢንቨስተሮች በገበያው ላይ እምነት ስለማይኖራቸው ተጨማሪ ሀብት እንዳያፈሱ ከማድረጉ ባሻገር ያፈሰሱትን ሀብት ለመሰብሰብ ይገደዳሉ። በዚህ ጊዜ የኢኮኖሚያዊ እድገት ማሽቆልቆል ይከሰታል።

በፕሬዚዳንት ትራምፕ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው በአሜሪካና በቻይና መካከል በቀሰቀሱት የንግድ ጦርነት የዓለማችን የሀገር ውስጥ ምርት በአንድ በመቶ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል። ለአሜሪካ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ከለላ ለመስጠት በሚል በትራምፕ የሚጣሉ ታሪፎች የንግድ ጦርነት ከመቀስቀሳቸው ባሻገር የዓለም ኢኮኖሚ እንዲቀዛቀዝ፣ ዜጎች ሥራ እንዲያጡና የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት እያደረገ ይገኛል።

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የንግድ ታሪፍ ሌሎች ሀገራትን ለአጸፋ ርምጃ በመጋበዝ የንግድ ጦርነትን ለኩሰዋል። በዚህ የተነሳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ውጥረት ተከስቷል። የሀገራት ግንኙነት ሻክሯል። የሽርክና ገበያው መረጋጋት ተስኖታል። ሸማቹ ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል። በዜጎች የሥራ ዕድል ላይ የስጋት ዳመና አንዣቧል።

ትራምፕ የታሪፉ ሰው እስከ መባል የደረሱት ታሪፍን እንደ መደራደሪያ መሳሪያ የማየት አባዜ ስለተጠናወታቸው ነው። በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው እንዲሁ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ የአልሙኒየምና የብረት ምርቶች ላይ ታሪፍ ጥለው ነበር። 100 ቢሊየን ዶላር በሚገመቱ የቻይና የቴክኖሎጂ፣ የግብርና፣ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ታሪፍ ጥለው ቻይናም በአጸፋው በአሜሪካ የግብርና ምርቶችና መኪናዎች ታሪፍ መጣሏ አይዘነጋም።

በሀገራት መካከል የሚደረግ የታሪፍ አጸፋዊ ምላሽ ነጮች ቲት-ፎር-ታት ይሉታል። በሸማቾች ላይ የዋጋ ጭማሪ እና የዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶች እንዲስተጓጎል አድርጓል። ከውጭ በሚገቡ ግብዓቶች ወይም ጥሬ ዕቃዎች የሚያመረቱ የአሜሪካ ፋብሪካዎች ለተጨማሪ ወጪ ከመዳረጋቸው ባሻገር ምርቶቻቸው ወደ ገበያ ሲገቡ ውድ ስለሚሆኑ ገዥ አያገኙም። በዚህ የተነሳ ፋብሪካዎች ለኪሳራ ይዳረጋሉ። ሠራተኛ ይበትናሉ።

ከሁሉም የከፋው የታሪፍ መዘዝ በገበያ ላይ ርግጠኛ አለመሆን፣ የሽርክና ገበያ መዋዠቅን እና ኢንቨስተሮች በገበያው ላይ እምነት ስለማይኖራቸው ተጨማሪ ሀብት እንዳያፈሱ ከማድረጉ ባሻገር ያፈሰሱትን ሀብት ለመሰብሰብ ይገደዳሉ። በዚህ ጊዜ የኢኮኖሚያዊ እድገት ማሽቆልቆል ይከሰታል። በፕሬዚዳንት ትራምፕ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው በአሜሪካና በቻይና መካከል በቀሰቀሱት የንግድ ጦርነት የዓለማችን የሀገር ውስጥ ምርት በአንድ በመቶ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል።

ለአሜሪካ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ከለላ ለመስጠት በሚል በትራምፕ የሚጣሉ ታሪፎች የንግድ ጦርነት ከመቀስቀሳቸው ባሻገር የዓለም ኢኮኖሚ እንዲቀዛቀዝ፣ ዜጎች ሥራ እንዲያጡና የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት እያደረገ ይገኛል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ከተመለሱ በኋላ ዓለም እየተመሰቃቀለች ነው። የመረጧቸው አሜሪካውያን ሳይቀር ከሥራ እየተቀነሱ ይገኛል።

ወዳጅ ሀገራትን በታሪፍና በአፍ እላፊ ባላንጣ እያደረጓቸው ነው። በጎረቤትና በአሜሪካ ወዳጅ ካናዳና ሜክሲኮ ላይ በከፊል ታሪፍ የጣሉ ሲሆን፤ በአውሮፓ ላይ ደግሞ 200 ፐርሰንት ታሪፍ እንደሚጥሉ እያንገራገሩ ነው።

ይህ አልበቃ ብሏቸው ካናዳ የአሜሪካ 51ኛ ግዛት እንደሚያደርጓት ሲናገሩ መደመጣቸው በካናዳ ቁጣ ቀስቅሷል። ታይቶም ሆነ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የካናዳን ብሔርተኝነት እንደ አዲስ ለመቀጣጠሉ መግፍኤ ሆኗል። በዚህ የተበሳጩ ካናዳውያን በአሜሪካ ምርቶች ላይ አድማ እየመቱ ይገኛል። በአሜሪካ ምርቶች ላይ አጸፋዊ ታሪፍ እየጣሉ ነው። በዚህ የተነሳ የሽርክና ገበያው ወርዶ ተፈጥፍጧል። የዋጋ ግሽበቱና የኑሮ ውድነቱ አሜሪካውያንን እያስጨነቀ ይገኛል። ካሁኑ የትራምፕ ደጋፊዎቹና መራጮቹ ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።

የታላላቅ ኩባንያዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች አበክረው የፕሬዚዳንት ትራምፕን ታሪፍ ጭማሬን አጥብቀው እየተቹትና እየተቃወሙት ይገኛል። ከኑግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ፣ አብሮ ይወቀጥ፤ እንዲሉ የፕሬዚዳንቱ ቀንደኛ ደጋፊ የሆነውና የመንግሥት ወጪ ቅነሳ ላይ የተሾመው በዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤለን መስክ ንብረት የሆነው የቴስላ የሽርክና ዋጋ እያሽቆለቆለ ነው።

በዚህ የተደናገጡት ፕሬዚዳንት ትራምፕ በአሜሪካ የፕሬዚዳንቶች ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ የቴስላ መኪና አሻሻጭ ሆነው ተከስተዋል። ከተለያዩ የቴስላ ሞዴል መኪኖች ፊት ቆመው ኤለን መስክን ከማድነቅ አልፈው አንድ ቴስላ መኪና መግዛታቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን መኪናዋ ውስጥ ሲገቡም ታይተዋል። ይሄ የጥቅም ግጭት የconflict of interest ጥያቄ አስነስቷል። ሥልጣናቸውን እና ነጩን ቤተ መንግሥት ቴስላን ለማስተዋወቅ እየተጠቀሙበት ነው። ይህ ደግሞ የለየለት የሕግ ጥሰት ነው በሚል ሚዲያው እያብጠለጠላቸው ይገኛል።

የንግድ ጦርነቱ እየተጧጧፈ ባለበት ነው እንግዲህ ትራምፕ በአውሮፓ ውስኪና ሻምፓኝ ምርቶች ላይ 200 ፐርሰንት ታሪፍ እጥላለሁ ያሉት። በአሜሪካና በአውሮፓ ሕብረት እንዲሁም ኔቶ አባል ሀገራት መካከል ንፋስ በገባበት ሰሞን ሌላ ግንኙነትን የሚያሻክርና ዓለማችንን ወደለየለት የንግድ ጦርነት ውስጥ የሚዘፍቅ ነገር ውስጥ ነው የገቡት ሲል የአሜሪካው ተነባቢ ጋዜጣ ፓለቲኮ ትራምፕን ይተቻል። የአውሮፓ ሕብረት ገና በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ በአሜሪካ የውስኪ መጠጥ ላይ የ50 ፐርሰንት ታሪፍ እጥላለሁ ስላለ ነው ትራምፕ 200 ፐርሰንት አጸፋዊ ታሪፍ እጥላለሁ ያሉት።

ትራምፕ ካናዳን ጨምሮ ከአውሮፓ ወደ ሀገራቸው በሚገባ አልሙኒየምና ብረት ምርቶች ላይ የ25 ፐርሰንት ታሪፍ ጥለው አውሮፓውያን አጸፋዊ ታሪፍ ይጥላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ሳለ ነው የአውሮፓንና የአሜሪካን ወይም ትራንስ አትላንቲክን የንግድ ጦርነት የሚያቀጣጥል የትራምፕ ታሪፍ ይፋ የሆነው። ትራምፕ ትሩዝ በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው የአውሮፓ ሕብረት በአሜሪካ ውስኪ ላይ የጣሉትን ታሪፍ ካላነሱ 200 ፐርሰንት ታሪፍ ይጠብቃቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በነገራችን ላይ በዚህ ታሪፍ ክፉኛ የሚጎዱት ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ስፔን ናቸው። ለዚህ ነው የፈረንሳይ የግብርና ሚኒስትር አኔ ጌንቫርድ ዓለም አቀፉን የንግድ ሕግ የሚጻረረው የትራምፕ ታሪፍ እውን የሚሆን ከሆነ አውሮፓ የአጸፋ መልስ ትሰጣለች ሲሉ ለፓለቲኮ የተናገሩት። የአውሮፓ ወይን አምራቾች ሊቀ መንበር ሳንቼዝ ሬካርቴ ደግሞ ይህ የትራምፕ ታሪፍ ሌላ ምንም ማለት አይደለም የአውሮፓ ምርት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ማገድ ነው።

አሜሪካ ለአውሮፓ ትልቁ ገበያ ነው። በብዛትም ሆነ በገቢ ሌላ የሚስተካከለው ገበያ የለም። ይሄ ዘርፍ የአሜሪካና የአውሮፓ የታሪፍ ጉልበት መፈታተሻ መሆን የለበትም ይላሉ ሊቀ መንበሩ። ማንም የማያተርፍበትን የንግድ ታሪፍ ትራምፕ ከመረጡ እኛም በአሜሪካ ብረትና አልሙኒየም ላይ ተመሳሳይ ታሪፍ እንጥላለን።

የአሜሪካ የንግድ ሚኒስትር ሀዋርድ ሉትኒክ የአውሮፓ ሕብረት የአጸፋ ታሪፍ የአሜሪካን ክብር የሚነካ ሲሉ ተችተዋል። ከብሉምበርግ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ትራምፕን ማስቀየም አጸፋው የከፋ ነው ሲሉ የአውሮፓን ሕብረት ያስጠነቅቃሉ። በማከልም ካናዳና አውሮፓ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ አክብሮት የላቸውም። አሜሪካ የራሷን የአልሙኒየምና የብረት ኢንዱስትሪ አሳድጋ ራሷን እንደምትችል እንኳ አያስቡም ሲሉ ሀዋርድ ይተቻሉ። በአንጻሩ ሜክሲኮንና እንግሊዝን እዩ ከአሜሪካ ጋር ተቀራርቦና ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለተገነዘቡ ከሀገራቱ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነው ያላቸው።

የቤልጂየም የምክር ቤት ካትሌን ቫን ብሬምፕት የተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግዴለዎትም አይጨነቁ የራሳችንን ወይን እንጠጣለን ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ተሳልቀዋል። አዲሱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር የትራምፕን ታሪፍ እንደሚፋለሙ ቃል ገቡ። የካናዳ ገዥው ሊበራል ፓርቲ መሪ ለመሆን በተደረገው ውድድር ያሸነፉት የቀድሞው የማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ ማርክ ካርኒ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ቆፍጠን ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ኢኮኖሚያችንን ለማዳከም የሚሞክር አንድ ሰው አለ፤ የካናዳ ሠራተኞችን፣ ቤተሰቦችንና የንግድ ድርጅቶችን እያጠቃ ነው፣ እንዲሳካለት ልንፈቅድለት አይገባም” ሲሉ ዶናልድ ትራምፕን ነቅፈዋል፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ትራምፕ እያደረሱ የሚገኙትን ተጽዕኖ ለመቋቋም ከተለመደው የተለየ አካሄድን መከተል እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ትራምፕ በካናዳ ላይ ለጣሉት የ25 በመቶ ታሪፍ፣ የጀስቲን ትሩዶ አስተዳደር 30 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር ዋጋ ባላቸው የአሜሪካ ምርቶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ በማድረግ ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።

ሻሎም ! አሜን።

በቁምላቸው አበበ ይማም (ሞሼ ዳያን) fenote1971@gmail.com

አዲስ ዘመን መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You