•ከፍተኛ ነጥብ ላመጡ ሴት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ይሰጣል
አዲስ አበባ፡- “ምሁራን ተዋዳችሁ ካልተማ ረው፣ ካልተዘጋጀው፣ ብዙዎች ከሚንቁትና ታሪክ ከሚሰራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ከማንም በላይ ከእናንተ የሚጠበቅ ይሆናል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡ ከፍተኛ ነጥብ ላመጡ ሴት ተማሪዎች በሙሉ የውጭ ሀገር ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በሚሊኒየም አዳራሽ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 9ሺ637 ተማሪዎችን በመረቁበት ወቅት እንዳሉት፣ ትልቅ ሃሳብ ትልቅ ሆኖ ትልልቆቹን የሚያሳምነው ሲተገበር ነው፡ ፡አራት ቢሊዮን ብለን አራት ቢሊዮን ማድረግ የምንችል፣ ትላልቅ ማሰብና መከወን የምንችል ህዝቦች መሆናችንን ለዓለም ስናሳይ እንዲሁም ድህነትን አሸንፈን ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ መሆናችንን ዳግም እናረጋግጣለን ብለዋል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በቅርቡ አራት ቢሊዮን ዛፍ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥረት ለመትከል ሥራ ተጀምሯል፡፡ አራት ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ስንወስን ይህንን ቅዱስ ሃሳብ ለመላው ሕዝብ ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት እስከ ዛሬ ድረስ ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን በላይ ዛፍ መትከል ተችሏል፡፡
ኃያላን ከሚባሉ የአውሮፓ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መካከልም አንዱ ስልክ ደውሎ ‹‹በእኔ አገር አራት ቢሊዮን ዛፍ የለም፡፡ አንተ በአንድ ክረምት አራት ቢሊዮን ዛፍ እተክላለሁ ምቹ በአረንጓዴ ተክሎች ያማረ ከማድረግም በተጨማሪ ሕፃናት እና ወጣቶች የሚያነቡበት ምቹ የማንበቢያ ቦታ ጭምር እንደሚሰራ ይናገራሉ። ይሄ ደግሞ ልጆች አልባሌ ቦታ ላይ እንዳይውሉ ፊታቸውንም ወደ ንባብ እንዲያዞሩ ያደርጋል። ስለዚህ በአካባቢ ሕዝብ እንዲለማና የአካባቢው ሕዝብ እንዲጠቀምበት ነው ያደረግነው። ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችም ይውላል።
በአሁኑ ሰዓት እየለማ ያለው አረንጓዴ ስፍራ ሦስት ሺ850 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ነው። ካለፉት ዓመታት ጀምሮ እንደ ግራር፣ ወይራ፣ዝግባ … የመሳሰሉትን ሀገር በቀል ዛፎችን ጨምሮ በርካታ ችግኞችን ተክለናል። ቦታውን በብሎኬት በማሳመርና በሳር በመሸፈን ንጹህና ማራኪ አረንጓዴ ስፍራ ለማድረግ እየተሰራ ነው። ለዚህ ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች ከ500 እስከ 5000 አዋጥተዋል የቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 9 ችግኝ እና ሳር በመስጠት ከፍተኛ ትብብር አድርጎልናል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ቦታውን በአካል በመመልከት እንድናለማ ፈቃድ ሰጥቶናል፤ ውል ወስደናል ሲሉ ነው የተናገሩት።
የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ እንዳሉት በአዲስ አበባ የሚገኙ የአረንጓዴ ቦታዎችን በደን ከመሸፈን አንፃር በርካታ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ይናገራሉ።
ከተማዋን አረንጓዴ የማልበስ ዕቅድ መንግሥት ብቻውን ውጤት የሚያመጣበት ባለመሆኑ ኅብረተሰቡ በተለያዩ አደረጃጀቶች በማህበራት መሳተፍ አለባቸው። በዚሁ መሠረት ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የመኖሪያቤት ማህበራት የመሳሰሉት አረንጓዴ ስፍራዎችን ማልማት ላይ ሲሳተፉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይበልጥ ተበረታትተው ወደ ሥራው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።
በክረምቱ ወቅት በችግኝ ተከላ ወደ ሥራ ለሚገቡ ማህበራትም ሆነ ተቋማት አስፈላጊውን ችግኞች እና በጉድጓድ ቁፋሮ እገዛ ይደረጋል። አሁን ከ500ሺ በላይ ችግኞች መኖራቸውን ይገልጻሉ።
«የደን ተከላ በአንድ ጊዜ ብቻ የሚሰራ ሥራ አይደለም፤ ዓመቱን በሙሉ የሚሰራ ነው። በመሆኑም ችግኝ ማፍላት፣ ጉድጓድ መቆፈር፣ ከዚያም ችግኝ መትከል ይከተላል። በዚሁ መሠረት ባለፉት አስራ አንድ ወራት ችግኝ የማፍላት ሥራ ተሰርቷል። በተለያዩ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች 780 ሺ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል። ይሄ በራሳችን የተሰሩ ናቸው። እስካሁንም 250ሺ ችግኝ የተተከለ ሲሆን በዚህም ሥራ 19 ሺ ዜጎች ተሳታፊ ሆነዋል» ይላሉ አቶ ዋለልኝ። በቀጣይ እንደ ሀገር አቀፍ ለሚሰራው ሥራም የጉድጓድ ማስቆፈር ሥራ እየተሰራ ነው።
አቶ ዋለልኝ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ በዓመቱ መጀመሪያ የተያዘው ዕቅድ አንድ ሚሊዮን ችግኝ እንተክላለን የሚል ነበር። ሆኖም ግን አሁን ለአረንጓዴ ልማት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የተነሳ ዕቅዱን ወደ ሦስት ሚሊዮን ከፍ በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት። ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ አራት ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ተገብቷል። ሐምሌ 22 ደግሞ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታስቧል።
ብለህ ማሰብህ ትልቅ ነገር እንደምታስብ ያሳያልና ምን ላድርግልህ›› ብሎ እንደጠየቃቸው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ፕሮግራሙን ለማስፈፀም አንዳንድ ነገር ያስፈልጋል›› በማለታቸው 130 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
“ትልቅ ሃሳብ ትልቅ ሆኖ ትልልቆቹን የሚያሳምነው ሲተገበር ነው“ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አራት ቢሊዮን አቅደን አራት ቢሊዮን ማድረግ የምንችል ሕዝቦች መሆናችንን ፣ትላልቅ ማሰብና መከወን የምንችል መሆናችንን ለዓለም ስናሳይ ድህነትንም እንደዚሁ የምናሸንፍ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል ፡፡
ስንኖር ኢትዮጵያዊ ከሆንን ኢትዮጵያችን አረንጓዴ መሆን አለባት፡፡ ስንሞት ኢትዮጵያ ከሆንን ቢያንስ መቃብራችን በዛፍ ጥላ ስር መሆን አለበት፡፡ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ከሆንን ደግሞ ቢያንስ ልጆቻችን ድህነትን ዳግም የማያስተናግዱ፤ የበጀት እጥረት ችግር የማያዳምጡ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ጉልበታችንን ፣እውቀታችንን፣ ጊዜያችንን ሳንሰጥ የምንመኛትን ኢትዮጵያን መፍጠር እንደማይቻል የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የወሰነ በየትኛውም ስፍራ ያለ ዜጋ ገንዘቡን ዱባይ ፣ለንደን፣ ቻይና ከሚያስቀምጥ ይልቅ በተባበረ፣ በህጋዊና ስርዓት ባለው መንገድ ኢንቨስት በማድረግ ባጠረ ጊዜ ኢኮኖሚያችንን ማሳደግና ተመርቀው ሥራ የሚያጡ ልጆችን ሥራ ለማስያዝ መስራት አለበት ብለዋል።
የዛሬ ሰባ አምስት ዓመት ገደማ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በሁለት በሬና በሞፈር ያርሱ እንደነበር ያስታወሱት ዶክተር አብይ ፣ ዛሬም ከሰባ አምስት ዓመት በኋላ አባትና እናቱን ከሞፈርና ቀንበር መገላገል ያልቻለ ትውልድ መሆኑን አንስተዋል። አሁንም ሌላ ሰባ አምስት ዓመት እንዳንቆይ በተባበረ ክንድ አርሶ አደሩን ከሞፈር፣ ከቀንበር፣ ከበሬ ተላቆ በዘመነ መንገድ አርሶ በልቶ የሚያበላን እንዲሆንና ለማኝነት ከኢትዮጵያ እንዲወገድ በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
“ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መዳረሻ ብልጽግና መሆኑን አምነን በአንድ አቅጣጫ መጓዝ ካልቻልን ያኮረፈ ሁሉ ወደ ቀበሌ ካለ፤ ኢትዮጵያ ትንሽ ትሆናለች” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይሄ እንዳይሆን ምሁራን መብራቱ ጨለማውን ገፎ መንገድ ማሳየት ሲገባው ራሱ ብርሃኑ በጨለማ ተውጦ መደናቀፍ እንዳይኖር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ምሁራን፣ተነጋግራችሁ፣ ተወያይታችሁ፣ የማያስፈልገውን ትታችሁ፣ የሚያ ስፈልገውን የሚጠቅመንን የጋራ ታሪክ ማውጣት፣ የጋራ ራዕይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ ብለዋል ።
የዛሬዎቹ ምሁራን ትልቅ ውለታ አለባችህ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም የወላጆች፣ የመምህራን፣ የቀዳሚዎቹና የሀገር ባለውለተኛዎች መሆናችሁን አውቃችው ውለታውን በየፈርጁ መመለስ የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ኢትዮጵያ ትልቁን በጀት ያስቀመጠችው ለትምህርት ነው። ይሄንን ሁሉ ሀብት የምታፈሰው ተምረው ድህነትን፣ ችግርን፣ ረሀብን፣ እርዛትንና አለመደማመጥን አለመሰልጠንን አስቀርተው ስልጡን ኢትዮጵያን ይፈጥሩልኛል የሚል እምነት ስላላት ነው።እስካሁን ላስተማረች ኢንቨስት ላደረገች አገር በመስራት ውለታዋን እንድትከፍሉ ሲሉ ተማጽነዋል።
ሀገር በፈተና ወቅት፣ በመከራ ጊዜ በስቃይ ጊዜ ችግሯን የሚያበዛና ስቃይዋን የሚያገዝፈው የማያውቁ ሰዎች ጩኸት ሳይሆን የሚያውቁ ሰዎች ዝምታ ነው ብለው የምናውቅ ሰዎች ዝም ካልንና አይተን እንዳላየን ከሆንን ዮፍታሄ ንጉሴ እንዳሉት “ሀገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ የእንቧይ ካብ“ ይሆናል ብለዋል ።
አዲስ ዘመን ሀምሌ 7/2011
በጋዜጣው ሪፖርተር