አዲስ አበባ፡- ተመራቂዎች ያገኙትን ዕውቀት በሥራ ላይ በማዋል ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለአገራቸው ጠቃሚ እንዲሆኑና የአገር ልማትን በማጠናከር ረገድም አርአያ መሆን እንደሚገባቸው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አስገነዘበ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቡራዩ ገፈርሳ ካምፓስ በልዩ ልዩ የትምህርት ዓይነት ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ትናንት ባስመረቀበት ወቅት የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ተሾመ እንደተናገሩት፣ ተመራቂዎች
ያገኙትን ዕውቀት በሥራ ላይ በማዋል የአገር ልማትን በማጠናከር ረገድ አርአያ እንዲሆኑ አደራ ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አክለው እንዳሉት ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር ማካሄድ እና የኅብረተሰብ አገልግሎት መስጠት ዩኒቨርሲቲ የሚያ ስብሉት ዓቢይ ተግባራት ናቸው፡፡
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲም እንደ አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመማር ማስተማር ሂደቱን በጥራት ለማከናወን ላለፉት ዓመታት የሚቻለውን ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ መቆየቱን ገልጸው ዩኒቨርሲቲው የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትና የጥራቱም ሂደት ቀጣይ እና አስተማማኝ እንዲሆን ሳያሰልስ እንደሚሠራ አብራርተዋል፡፡
የቡራዩ ገፈርሳ ካምፓስ ዲን ዶክተር ሙሉጌታ ታየ በበኩላቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎች የዕድሜ ዘመን የቡራዩ ገፈርሳ ካምፓስ አምባሳደር እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
በካምፓሱ የሚማሩ የተማሪዎች ቁጥርንም ለማሳደግ በማሰብ ከዩኒቨርሲው ጋር ተመጋጋቢ የሆነ ከኬጂ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሚለውን የትምህርት ስልት ተግባራዊ ለማድረግ መሠረት እየተጣለ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
«ካምፓሱን ለማሳደግ የተለያዩ የማስ ፋፊያ እና የማጠናከሪያ ሥራ መስራት አለብን» ያሉት ዶክተር ሙሉጌታ ይህ ንንም ለመተግበር የአካባቢውን ሕዝብ በማስ ተባበርና ከሚመ ለከታቸው ቢሮዎች ጋር በመሆን እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡
ከነፃ የትምህርት ዕድል ጋር በተያያዘ የአካባቢውን ሕዝብ ለማበረታታት በዩኒቨ ርሲቲው ፕሬዚዳንት በዶክተር አረጋ ይርዳው ለአምስት ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት እንዲማሩ የነፃ ዕድል እንደተሰጠም በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
አዲስ ዘመን ሰኔ 30/2011
አብርሃም ተወልደ