አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ እርጥባማ መሬቶችን በዘላቂነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን የራምሳር ስምምነት /ኮንቬንሽን/ለመፈረም ጥናት እየተካሄደ መሆኑን የአካባቢ፣ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
የአካባቢ፣ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደተ ናገሩት፤ እርጥባማ መሬት በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈረመ የራምሳር ኮንቬንሽን የሚባል በቅርቡ ፀድቋል፡፡ ኮንቬንሽኑ እርጥባማ መሬት እንዴት በዘላ ቂነት መጠቀም እንደሚቻል ያስቀምጣል። ኮንቬንሽኑ ሲፈረም ቴክኖሎጂ፣ የምሁራን ልውውጥንና ሀብት ያስገኛል፡፡ ይህን ኮንቬንሽን ኢትዮጵያ እስካሁን አልፈ ረመችም፡፡ ኮንቬንሽኑን ተቀብሎ ለመፈረም ጥናቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያ ማንኛውንም ዓለምአቀፍ ድርድር ቅድሚያ አጥንታ ነው የምትፈርመው ያሉት ፕሮፌሰር ፈቃዱ፤ በድርድር የሚገኙ ስምምነቶች አገራዊ ፋይ ዳቸው ታይቶ እንደሚፈረሙ አመልክተዋል። የራ ምሳር ኮንቬንሽንንም በባለሙያዎች እንዲጠና ተደርጎ የጥናት ውጤቱ ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ ጠቅሰ ዋል፡፡
እንደ ኮሚሽነሩ አባባል፤ እርጥባማ መሬቶች በጣም ጠቃሚ የአገር ሀብት ናቸው፡፡ እርጥባማ መሬቶች ሲባል ብዝሀሕይወትና የውሃ አካላትን የሚያካትት ሲሆን በበለፀጉት አገሮች አካባቢ እርጥ ባማ ቦታዎችን ከማድረቅ ይልቅ ተንከባክቦ በውስጡ የሚገኙትን ነገሮች የመጠቀም አሰራር አሉት፡፡ የኮንቬሽኑ ጥቅም የመጀ መሪያው በዘላቂነት ይሄን ሀብት መጠቀምና መጠበቅ ማስቻል ነው፡፡ ይሄም ኢኮኖሚያዊና ስነ ምህዳራዊ ጠቀሜታ አለው። ስነ ምህዳር ጠቀሜታ ሲባል ለምሳሌ የበካይ ጋዞችን የመምጠጥ ሚና አለው፡፡ ይህን ለመጠቀም ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶች ያስፈልጋሉ፡፡
አዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011
መርድ ክፍሉ