አዲስ አበባ፡- በአማራና በደቡብ ክልል በተለያዩ ግጭቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ የማቋቋም ሥራ እየተሠራ ነው። በመጠለያ የሚገኙት ደግሞ እስከ ሰኔ አስራ አምስት ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንደሚመለሱ የየክልሉ ኮሚሽነሮች አስታወቁ።
የአማራ ክልል የአደጋ መከላከል ዋስትና ማስተባበሪያ እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ እታገኘው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በተለያየ ምክንያት በተፈጠሩ ግጭቶች የማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደርን ጨምሮ ወደ መቶ ሰባት ሺ የሚጠጉ ተፈናቃዮች የተለያዩ ድጋፎች ሲደረግ
ቆይቷል፤ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ በመመለስ እና መልሶ ለማቋቋም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ግብረሃይል ተቋቁሞ ሥራ እየተሰራ ነው። እስከ ሰኔ አስራ አምስት ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ቦታቸው ይመለሳሉ።
በአሁን ወቅት ከግማሽ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቦታቸው መመለሳቸውን ያነሱት ምክትል ኮሚሽነሯ ተመላሾችን መልሶ የማቋቋሙ ሥራ የቤት ግንባታን ጨምሮ መሆኑን ገልጸው ክልሉ ለቀሪዎችም ቤት በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ወይዘሮ እታገኘው ገለፃ፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው ከኦሮሚያ፣ ከቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ከሱማሌ አካባቢ ተፈናቅለው የመጡ የክልሉ ተወላጆች አሉ። ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ ቆይቷል፤ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ በመመለስ እና መልሶ ለማቋቋም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ግብረሃይል ተቋቁሞ ሥራ እየተሰራ ነው። እስከ ሰኔ አስራ አምስት ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ቦታቸው ይመለሳሉ።
በአሁን ወቅት ከግማሽ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቦታቸው መመለሳቸውን ያነሱት ምክትል ኮሚሽነሯ ተመላሾችን መልሶ የማቋቋሙ ሥራ የቤት ግንባታን ጨምሮ መሆኑን ገልጸው ክልሉ ለቀሪዎችም ቤት በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ወይዘሮ እታገኘው ገለፃ፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው ከኦሮሚያ፣ ከቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ከሱማሌ አካባቢ ተፈናቅለው የመጡ የክልሉ ተወላጆች አሉ። ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ
አዲስ ዘመን ሰኔ 9/2011
ሞገስ ፀጋዬ