አዲስ አበባ፡- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬተ ሮች የማኅበረሰብን ችግር የሚቀርፉ ወሳኝ መፍትሄዎችን የማፍለቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዘጠነኛውን ዓመታዊ ብሄራዊ የሳ ይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የሽልማት የእው ቅና ሥነሥርዓት በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን መሰብሰቢያ
አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት እንደገለፁት፣ የእ ውቀት ዋነኛ ስኬት አዎንታዊ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የማኅበረሰብን ችግር ማቃለል ነው።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ጠቅላይ ሚኒስ ትሩ ተሸላሚዎቹ የመደመር ፍልስፍናን እንዲ ጠቀሙበትና በትብብር የወደፊቷን ኢትዮጵያ እንዲገነቡ ያበረታቱ ሲሆን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የጀመሩትን የፈጠራ ሥራ ጨርሰው የጀግንነት ሥራ እንዲ ሰሩም ጠይቀዋል፡፡
በሥነ ሥርዓቱ 194 ተመራማሪዎችና ኢኖ ቬተሮች እውቅናና ሽልማታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እጅ የተቀበሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 38 ወርቅ፣ 81 ብር፣ 66 ነሃስ፣ 4 የፈጠራ ሥራ የምርምር እና 5 ልዩ ተሸላሚዎች መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የህዝብ ተወ ካዮች ምክር ቤት አባላት፤ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የተሸላሚ ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ከግንቦት 29 – ሰኔ 3 በተካሄደው ‘’የኢኖቬት ኢትዮጵያ’’ ሳምንት የዲጂታል ውድድር፣ የአ ይሲቲ ኤክስፖ፣ ኢትዮጵያን እናነሳሳት (ስታርት አፕ ኢትዮጵያ)፤ የኢኖቬት ዲጂታል አፍሪካ ስብሰባ እና ሀገር አቀፍ የሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሽልማት የተከናወነ ሲሆን በኢኮሜርስ /የኤሌክትሮኒክ ግብይት/፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ የስራ ፈጠራ፣ በዲጂታል የመንግሥት አሰራር እና ሌሎች ርዕሶች ዙሪያም ውይይቶች ተደርጓል፡፡
የኢኖቬት ሳምንቱ የኢፌዴሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ግንቦት 29/2011 በሚሊኒየም አዳራሽ መከፈቱ ይታወሳል፡፡
አዲስ ዘመን ሰኔ 6/2011
ድልነሳ ምንውየለት