የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሳምንት (ኢኖቬት ኢትዮጵያ) ከግንቦት 29 – ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚከበር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩርያ (ዶ/ር. ኢንጂ.) ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀዋል።
በእነዚህ ቀናት ውስጥ አራት ታላላቅ ኩነቶች የሚካሄዱ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ ከግንቦት 29 – ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የ ICT ኤክስፖ በሚሌኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በኤክስፖው ላይ በዓለምና በአገር ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ በአይሲቲ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል። በተመሳሳይ ሰኔ 1 ና 2 ኢትዮጵያን እናነሳሳት ወይም “Start up Ethiopia” ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አገር ትሁን የሚል አዲስ ራዕይ መኖሩን የሚያሳይ ኩነትም በሚሌኒያም አደዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል ብለዋል ሚኒስትሩ።
እንደሚኒስትሩ ገለጻ ሰኔ 3ና 4 ደግሞ “ ኢኖቬት አፍሪካ” የተሰኘው በርካታ የዘርፉ ምሁራንና ባለሙያዎች በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በዲጂታል ገቨርንመንት፣ በኢ-ኮመርስ፣ በስራ ፈጠራና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሸራተን አዲስ የሚመክሩበት የፓናል ውይይት የሚካሄድ ይሆናል። በማጠቃለያም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሰኔ 5 ላይ የሚከናውነው ሽልማት ስነስርአት ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የፈጠራ እና የምርምር አሸናፊዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሽልማት የሰጣቸዋል ብለዋል ሚኒስትሩ።
እንደ ዶ/ር. ኢንጂ. ጌታሁን መኩርያ ገለጻ የዘንድሮው የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴልኖሎጂ ሳምንት ዓላማዎች መካከል አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች ማበረታታት፣ በዘርፉ በአገሪቱን ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ማሳየ እንዲሁም ከውጭ የሚመጡ የቴክኖሎጂ ፈጣራዎችን ከአገር ውስጥ ጋር ትስስትር መፍጠር፣ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችና በርካታ ሰዎች የሚሳተፉበት ጉባዔ በመሆኑ የቴክኖሎጂ ቱሪዝምንም ማስተዋወቅም ይሆናል።
ተ.ተ