አዲስ አበባ፡- በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በአዲሱ የመብራት ፈረቃ አሠራር ምክንያት እየተቸገሩ መሆናቸውን አመለከቱ።
ነዋሪዎቹ ችግሩን አስመልክተው ሰሞኑን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በግድቦች ላይ ያጋጠመውን የውሃ እጥረት ተከትሎ ከመንግሥት የተላለፈውን የመብራት ፈረቃ ከተመደበው ሰዓትና ቀናት በላይ መብራት እየጠፋ በመሆኑ በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮባቸዋል፡፡
በቱሉዲምቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በፕሮጀክት አስራ ሁለት ከሚገኙ ነዋሪዎች መሀል ወይዘሮ ሙሉ አመንሲሳ ከቀናት በፊት መብራት በፈረቃ ይሆናል መባሉን ሰምተው የራሳቸውን ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ይናገራሉ።
የፈረቃው ሂደት በአግባቡ ተግባራዊ ባለመሆኑ ግን ለሦስት ቀናትና ከዚያም በላይ ያለመብራት ለመቆየት መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡
የመብራት መጥፋቱ ችግር መደጋገም የቀደመ ህይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት እየቸገራቸው መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ ሙሉ ስለፈረቃው ለአካባቢው ግልጽ መረጃ ያለመሰጠቱም በኤሌክትሪክ ከመጠቀም ሌላ አማራጭ ለሌለው ነዋሪ ችግር እያስከተለ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ሌላው የፕሮጀክቱ ነዋሪ አቶ ሳሙኤል በቀለ በበኩላቸው በተከታታይ እየጠፋ ካለው መብራት ጋር ታያይዞ የአካባቢው ነጋዴዎች በእንጀራና በሌሎች ምግቦች ዋጋ ላይ ጭማሪ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በአሁኑ ጊዜም በአካባቢው ሱቆች የአስር ዳቦ ዋጋ ከ35 እስከ 40 ብር መድረሱን በመጠቆም የመብራት መጥፋቱ ሰበብ ለህገወጦች ጭምር በር እየከፈተ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለምዶ ኃይሌ ጋርመንት በሚባለው አካባቢ የሚኖሩት ወይዘሮ ዓለም ገብሩ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ቀደም ሲል በአካባቢው ተደጋጋሚ የመብራት መቆራረጥ ችግር ነበር። ከቅርብ ቀናት ወዲህ የፈረቃ ሂደት መጀመሩን ቢሰሙም አሠራሩ በአግባቡ እየተተገበረ ባለመሆኑ እሳቸውን ጨምሮ በርካቶቹ ለችግር ተዳርገዋል፡፡
ለበርካታ ቀናትን በጨለማ እያሳለፍን ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ይህ ችግር በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የከፋ መሆኑንና ከዝናብና ጨለማ ጋር ተያይዞም ለዝርፊያና መሰል ወንጀሎች እየተጋለጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ አሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ በሰጡት ምላሽ ቀደም ሲል የነበረው የመብራት መቆራረጥ እንዳለ ሆኖ አሁን የተጀመረው የፈረቃ ሂደት በኑሮ ልማድ ላይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።
በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎችም ከትራንስፎርመር ብልሽት ጋር ተያይዞ ለቀናት መብራት የመጥፋት ችግር እያጋጠመ መሆኑን አስረድተዋል። ይሁን እንጂ አብዛኛው ነዋሪ ጉዳዩን ከመብራት ፈረቃ ጋር በማያያዝ በወቅቱ ጥቆማ ስለማይሰጥ ችግሩ ያለመፍትሔ እንዲቀጥል ምክንያት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ተደራራቢ የብልሽት ችግሮች እንደሚስተዋሉ የሚናገሩት አቶ ብዙወርቅ፤ ሰሞኑን ከሚጥለው ዝናብ ጋር ተያይዞም በአንዳንድ መስመሮች ላይ ችግር እያጋጠመ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በንፋስ ኃይል የዛፎችና ምሰሶዎች መውደቅና መሰል ችግሮች በአገልግሎቱ ላይ ተጨማሪ ፈተና እየጋረጡ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ሰሞኑን በተጀመረው የፈረቃ ሂደት አብዛኞቹ ደንበኞች መብራት ሲለቀቅ በተመሳሳይ ጊዜ የመጠቀማቸው እውነታ ትራንስፎርመሮቹ ከአቅም በላይ ኃይል እንዲሸከሙና ችግሩ እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
የፈረቃ ሂደቱን አስመልክቶ ለየአካባቢዎቹ ተራቸውን የማሳወቅ ክፍተት እንዳለ የሚያምኑት አቶ ብዙወርቅ፣ ለዚህም ምክንያቱ የሰፈሮቹን መገኛ ለይቶ ለማስቀመጥ የአቀማመጣቸው አቅጣጫ አመቺ አለመሆኑ የፈጠረው ችግር ስለመሆኑ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ብዙነህ ገለጻ፤ ከጥቂት አካባቢዎች በቀር የሰሞኑን ችግር አስመልክቶ ለተቋሙ መረጃ የሰጠ አካል የለም። ይህ ሁኔታ በሌለበት አጋጣሚም አስቸኳይ መፍትሔ ለመስጠት አልተቻለም። ይሁን እንጂ ማንኛውም ደንበኛ ከተገለጸው የፈረቃ ቆይታ በላይ መብራት መጥፋት ሲያጋጥመው በወቅቱ በማሳወቅ ምላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡
ሰሞኑን ተከታትሎ የሚጥለው ዝናብ ለግድቡ ኃይል ግብአት እንደሚሆን ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው፤ ሁኔታዎች በታሰበው መልኩ ከተሳኩም እስከ ሰኔ 30 የታቀደው የፈረቃ ሂደት እንደሚቀንስና ከወዲሁ እንደሚቋረጥ ገልጸዋል። እስከዚያው ግን ከሌሊቱ 11 ሰዓት እስከቀኑ 8 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ያለው የፈረቃ ሂደት በነበረው መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 17/2011በመልካምሥራ አፈወርቅ
በመብራት ፈረቃ ምክንያት ነዋሪዎች መቸገራቸውን አመለከቱ