የኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ምርምር ላደረገችው ጥረት በሳይንሳዊ መጠሪያቸው “HD16175 ና HD16 175b ተብለው ለሚታወቁት ኮኮብና ፕላኔት” የሚገኙበትን ስርዓት ስያሜ እንድትሰጥ ዕድል እንደተሰጣት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።
ኢትዮጵያ እያደረገች ባለችው ጥረትና ተሳትፈዋ እውቅና በመስጠት የህዋው አለም አቀፉ ህብረት (International Astronomical Union –IAU) በኢትዮጵያ ጋላክሲ ውስጥ የሚገኙትን በሳይንሳዊ መለያው HD16175 ተብሎ የሚታወቅ ኮኮብና HD16 175b ተብላ የምትታወቀዋን ፕላኔት የሚገኙበትን ስርአት ኢትዮጵያ እንድትሰይም ዕድል ዕድል ተሰጥቷታል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰሎሞን በላይ ፤ ኢትዮጵያ እንድትሰይም የተሰጣት ኮኮብና ፕላኔት በ196 የብርሀን አመት አካባቢ ከእኛ ፀሀይ ርቀው በእኛው ጋላክሲ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ብለዋል።
ኮከቧ ከጸሐይ 1.34 ጊዜ የምትገዝፍ ߹ ስፋተዋ ደግሞ ከፀሐይ 1.66 ጊዜ ያህል የምትበልጥ እና ከሶስት እጥፍ በላይ ከፀሐይ የበለጠ የምታበራ መሆኗ እንደታወቀ ገልፀዋል ። ፕላኔትዋ በግዙፈነት ጁፒተር ከሚባለው ፕላኔተ ከ 4.8 ግዜ በላይ ትበለጣለች ።
በዚህ የህዋ አካል ስርአት ውስጥ ለሚገኙት የምንሰጠው ስያሜ ዝንተ አለም መጠርያቸው ሆኖ ኢትዮጵያ የምትታወስበት ና ትውልድ የሚያነሳሳ ታላቅ ክብርና ኩራት ነው ያሉት ደሞ በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ዋና ስራ አስካያጅ ወ/ሮ ቤዛ ተስፋየ ናቸው። አሰያየሙ በተቻለ መጠን ሰፊና ህዝባዊ ተሳትፎ ማገኘት ስላለበት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ߹ ዩኒቨርስቲዎችና ሌሎች ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ምሁራን ߹የምርምር ተቋማት ߹ እድሮች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለያዩ መንገዶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በማዕረግ ገ/እግዚአብሄር