በአገሪቱ ስምንት አካባቢዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው የመድኃኒቶችንና የህክምና ተረፈ ምርቶችን የሚያስወግድ የዘመኑን ቴክኖሎጂን የሚጠቀም መሳሪያ ወይም ኢንሲኒሬተር እየገንባ መሆኑን የመደሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ገለጸ።
በአዳማ፣ ሃዋሳ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ነቀምት፣ ደሴና ድሬዳዋ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችንና የህክምና ተረፈ ምርቶችን ማስወገጃ ኢንሲኒሬተር በመገንባት ላይ መሆኑን የገለጹት የኤጀነሲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ አድና በሬ አሁን ላይ የአዳማና ሃዋሳና የህንጻ ግንባታውና የማሽን ተከላው ሂደት ተጠናቆ ስራ ጀምረዋል።
በተመሳሳይ የባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ነቀምትነና ደሴ ደግሞ የህንጻ ግንባታቸውና የማሽን ተከላ ተጠናቆ የሙከራ ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይናቸው ያሉት ሃላፊዋ የቀሩት ደግሞ የህንጻ ግንባታቸው እየተካሄደ ነው ብለዋል።
ኢንሲኔሬተሮቹ ከራዲዮ አክቲቭ ውጪ የሆኑ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው የመድኃኒቶችንና የህክምና ተረፈ ምርቶችን ለአብነት ግላቭ፣ ሰሪንጅ፣ ዲዲቲ፣ ኬሚካሎች ሌሎች ክኒሊካልና አናቶሚክ ተረፈምርቶችን 99.9 በመቶ ያለጭስ የማቃጠል አቅም ያለው ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጆዎችን የሚጠቀም ነው ያሉት ሃላፊዋ ኢንሲኔሬተሮቹ ከመተከላቸው በፊት የሚከተሉት ሂደቱ ከአካባቢ ብክለት ነጻ መሆኑ በየአካባቢው ባሉ ዩንቨረሲቲዎችና በአካባቢ ጥበቃ ሃላፊዎች ተረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡
በአዳማ የተገነባው ኢንሲኒሬተር በአገሪቱ እየተገነቡ ካሉት ስምንት ኢንሲኔሬተሮች መካከል በአቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ወ/ሮ አድና አዲስ አበባን ጨምሮ ለአካባቢው ከተሞች አገልግሎት ይሰጣል።
ሃላፊዋ አያይዘውም ኤጀንሲው ኢንስኔሬተሮች ግንባታ 16 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን የአዳማው ኢንሲኔሬተር ግንባታ ብቻ 100 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ብለዋል።
ተ.ተ