“የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ተፈጥሯል” በተባለበት በተያዘው የበጀት ዓመት ካለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ የገቢ ግብር መሰብሰብ ተችሏል።
በአገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች አለመረጋጋቶች በመከሰታቸው በተለያዩ ጊዜያት አስተያየት ሰጪዎች ሁኔታው በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ፈጥሯል ሲሉ ስጋታቸውን ሲያስቀምጡ ተደምጠዋል። ይህን እንጂ በበጀት ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ ግብር ካለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በታሪክ ከፍተኛው መሆኑ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያነጋገራቸው የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ ይርጋ እንዳሉት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በበጀት ዓመቱ በዘረጋቸው አዳዲስ አሰራሮችና የታክስ ንቅናቄዎች ካለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ግብር መሰብሰብ አስችሎታል።
“የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ አለ፤ የለም” የሚለው ጥያቄ ራሱን የቻለ ጥናት ይፈልጋል ያሉት አቶ አዲስ፤ እንደ ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግን ባለፉት አስር ወራት በተከናወኑት የተለያዩ ተግባራት ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።
እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፤ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱ የታክስ ንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብም የተካሄዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ፣ ህብረተሰቡ ለተገበያየበት ደረሰኝ መጠየቅና ነጋዴዎችም ደረሰኝ የመቁረጥ መጀመራቸው ለገቢ መጠኑ ማደግ ምክንያት ሆነዋል።
የኮንትሮባንድ ንግድን የመከላከል ቁርጠኛ አቋም መያዙ፣ ሃሰተኛ ደረሰኞች በሚሰጡነና ገቢያቸውን በሚያንሩ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ መጀመሩም ለገቢው ማደግ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ነው አቶ አዲስ ያብራሩት።
በኢፌዲሪ ፖሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት የፖሊሲ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ግርማ ተሾመ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳብራሩት፣ በአገሪቱ ከዚህ ቀደም መደበኛ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ሴክተሮች በተለይም ከኮንትሮባንድ ንግድ ጋር በተያያዘ ህገወጥ ተግባራት በብዛት ይስተዋሉ ነበር። በዚህ መንገድ የሚገቡ እቃዎች ህጋዊ ነጋዴውን ለኪሳራ ከመዳረጋቸውም ባሻገር በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ይፈጥራሉ ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ በመጀመሩ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየተገቱ በመምጣታቸው የተሻለ ገቢ እንዲሰበስብ እንዳገዘ ተመራማሪው ተናግረዋል።
እንደ ዶክተር ግርማ ገለፃ፤ አሁን ላይ የተወሰነ መልኩ የኢኮኖሚ መገጫገጮች ቢስተዋሉም ህገወጥ የኮንትሮባንድ ንግዶች ወደ ህጋዊነት መመለስ መጀመራቸውና ህብረተሰቡም ስለግብር የተሻለ ግንዛቤ እየፈጠረ መሆኑ እንዲሁም መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ ያረጋጋዋል፡፡
በኃይማኖት ከበደ
“የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ተፈጥሯል” በተባለበት ዓመት የተሻለ የገቢ ግብር መሰብሰብ ተችሏል