ከ«ጎልደን ፎር» እስከ «ዳይመንድ ሊግ»

ከሳምንታት በፊት በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሜዳሊያዎችን ካጠለቁ አትሌቶች መካከል አብዛኛዎቹ ትናንት እና ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የዳመንድ ሊግ የፍጻሜ ውድድሮች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። መነሻውን በኳታር ዶሃ አድርጎ በአራት አህጉራት በ14 ከተሞች ሲከናወን የቆየው የዳይመንድ ሊግ የዓመቱን ውድድር አሜሪካ ዩጂን ኦሬጎን ላይ ይጠቃለላል። በዚህ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ይጠበቃሉ። በእያንዳንዱ ርቀት በድምር የነጥብ ውጤት የሚያሸነፉ አትሌቶች በነፍስ ወከፍ የአልማዝ (ዳይመንድ) ዋንጫ እና 30 ሺህ ዶላር ሽልማት የሚያገኙም ይሆናል።

የዓለም ምርጥ አትሌቶች የሚካፈሉበት ይህ ዓመታዊ ውድድር እዚህ ለመድረስ በርካታ ደረጃዎችን አልፏል። ይህ ውድድር ጥንታዊ ሊያሰኘው በሚችል መልኩ መነሻውን ያደረገው እአአ በ1978 ነው። በወቅቱ ምርጥ የሚባሉ አትሌቶችን እርስ በእርስ ለማፎካከር በማቀድም በአውሮፓ ከተሞች ማለትም በዙሪክ፣ ኦስሎ እና ብራስልስ ውድድሮች ይካሄዱ ነበር። የቻምፒዮና ቅርጽ ያልነበረው ውድድሩ እአአ ከ1993 አንስቶ በርሊንን ሌላኛዋ የውድድሩ መዳረሻ ከተማ በማድረግ ‹‹ጎልደን ፎር›› በሚል ስያሜ አዲስ ቅርጽ በመያዝ ይደረግ ነበር። በሜዳ እና በመም አትሌቲክስ ላይ የሚያተኩረው ውድድሩ የራሱን አስተዳደር በማዋቀርም በአራቱ ከተሞች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶቹ ልዩ ሽልማት ያበረክታል። ይኸውም 20 ኪሎ ግራም ወርቅ ሲሆን በተከታታይ አሸናፊ የሚሆኑት አትሌቶች በቁጥራቸው ልክ የሚከፋፈሉትም ይሆናል። በ1993 አምስት አትሌቶች የወርቁ ተካፋዮች ሲሆኑ፣ በቀጣዩ ሁለት አትሌቶች፣ ከዚያም አራት በቀጣዮቹ ደግሞ አምስት እና ሶስት አትሌቶች ወርቁን ተቀራምተዋል።

braveness is definitely the emotional meaning related to best swiss site web.best wp-affiliatebuilder.net moved by way of latter part of the 24th century western european enormous railway rail station through the region of one’s salmon dome.choose news and events our online store.

በዚህ መልክ ለአምስት ዓመታት የተካሄደው ውድድሩ እአአ ከ1998 ጀምሮ ግን በዓለም አትሌቲክስ ባለቤትነት ‹‹ጎልደን ሊግ›› የሚል ስያሜን አገኘ። የሮም፣ ሞናኮ እና ሞስኮ ከተሞችንም ውድድሩን ወደ ማስተናገድ እንዲቀላቀሉ በማድረግ መዳረሻዎቹን አስፍቶ ለዓመታት ሲያወዳድር ቆይቷል። በሁሉም ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሚሆነው አትሌትም እንደቀድሞው ባይሆንም ሽልማቱን በጥፍጥፍ ወርቅ አሊያም በገንዘብ እንዲወስድ ይደረግ ነበር። አትሌቶችም እጅግ አጓጊ ከሆነው ሽልማት ባለፈ በዓለም አትሌቲክስ ለሚመሩ ሌሎች ሶስት ውድድሮች ተሳታፊ ለመሆን እንደ ማጣሪያ የሚያገለግል በመሆኑ በሰባቱ ከተሞች በሚኖራቸው ተሳትፎ ነጥብ ለመጨመር ይፎካከሩ ነበር።

እአአ ከ2010 አንስቶ ግን ለሶስተኛ ጊዜ ስያሜውን ወደ ‹‹ዳይመንድ ሊግ›› በመቀየርና ለአራተኛ ጊዜ የውድድር ቅርጹን በመከለስ እስካሁን ድረስ እየተካሄደ ይገኛል። በወቅቱ የተጨመረችው ከተማ ፓሪስ ብቻ ስትሆን፤ የአንድ ቀን ውሎው ውድድር ረቡዕ ዕለት ብቻ ይከናወን ነበር። ይኸውም የሆነው የመገናኛ ብዙሃንን ሽፋን ለማግኘት ነው። በሂደትም የ‹‹ጎልደን ሊግ›› ዋነኛ ዓላማ የነበረውን የአውሮፓውያን አትሌቶችን ብቃትና በከተሞቻቸው ማሳደግን በመቀየር በመላው ዓለም ያሉ ከተሞችን ማጠቃለልና ሁሉንም አትሌቶች ማሳተፍ የሚል ሆነ። በዚህም የመዳረሻ ከተሞቹንም ቁጥር በመጨመር ወደ 14 ሲያሳድግ፤ ዓመቱን ሙሉም ውድድሩ የሚካሄድ ይሆናል። በተለያዩ ጊዜያት የውድድሩ አዘጋጅ ከተሞች ቢለያዩም አሁን ላይ ከአውሮፓ ባለፈ ከአሜሪካ አህጉር (ዩጂን)፣ ከአፍሪካ (ራባት) እንዲሁም ከእስያ አህጉር (ዶሃ እና ዚመን) ከተሞችን ላይ ይከናወናል። ዳይመንድ ሊግ በሚል ስያሜ ውድድሩ በተጀመረበት ወቅት ከመዶሻ ውርወራ በቀር ባሉት የሜዳ ተግባራት እንዲሁም የመም የሩጫ ውድድሮች ይካሄዱበት የነበረው ዳይመንድ ሊግ፤ እአአ ከ2020 አንስቶ ውድድር የሚካሄድባቸውን ተግባራትና ርቀቶች ከ32 ወደ 24 እንዲቀነሱ መወሰኑን በፕሬዚዳንቱ ሰባስቲያን ኮ በኩል አሳውቋል። ከተቀነሱት ውድድሮች መካከል አንዱ በተለይ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ውጤታማ የሚሆኑበት የ10ሺ ሜትር አንዱ ሲሆን፤ በጊዜው ሃገራቱ ቅሬታ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ሰሚ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የሚታወስ ነው።

ይሁንና በዚያው ዓመት ተከስቶ በነበረው ዓለም አቀፉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩን ማካሄድ ባለመቻሉ ተሰርዞ ነበር። በቀጣዩ ዓመት ዳይመንድ ሊጉ ወደ ውድድሩ ሲመለስም ፉክክር የሚደረግባቸውን ሁነቶች በድጋሚ ወደ 32 ያሳደገ ቢሆንም ኢትዮጵያውያንን ያስከፋው የ10ሺ ሜትር ውድድር ግን እንደተሰረዘ ነው። ትላንትና እና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች እአአ የ2023 ዳይመንድ ሊግ ፍጻሜ ላይም በአጠቃላይ የዙር ውድድሩ የተሻለ ነጥብ መሰብሰብ የቻሉ አትሌቶች አሸናፊዎች ይሆናሉ።

ብርሃን ፈይሳ

አዲስ ዘመን እሁድ መስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You