አዲስ አበባ፡– በግማሽ ቢሊዮን ብር የተቋ ቋመው የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፍት ሃዊነት በጎደለው አወሳሰን እስከ 20 በመቶ የሚደ ርስ ግብር እንዲከፍል በመደረጉ በገበያ ለመ ወዳደር መቸገሩን ገለጸ።
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አደም ዳውድ እንደገለጹት፣ የፕላስቲክና የግሪን ሀውስ ሽት ተጠቃሚ ገበሬዎች ዘርፉን ለማበረታታት በሚል ከውጭ ሲያስገቡ ያለቀረጥ እንዲያስገቡ ፈቅዷል። የፕላስቲክና የግሪን ሀውስ ሽት በማምረት በአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነው ፋብሪካው ግብዓቶችን ከውጭ ሲያስገባ ቀረጥ እንዲከፍል ይደረጋል። ከተመረተ በኋላም ሽያጭ ሲፈፀም ከደንበኞች በሚከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ዋጋው ከ20 በመቶ በላይ ይጨምራል።
ለእኛ ፋብሪካ ተጠቃሚዎች ከውጭ በነፃ እንዲያስገቡ ፈቅዶ የእኛ ፋብሪካ ከፍተኛ ግብር ስለሚጠየቅ ፍትሃዊ ባልሆነው ገበያ ለመወዳደር ተቸግረናል ብለዋል።ፋብሪካው የተቋቋመበት ዓላማ ከውጭ የሚገቡ የፓይፕ ምርቶችን በማምረት ለአገር ውስጥ ተጠቃሚዎች በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ማስቀረትና ለአፍሪካ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
አቶ አደም እንደገለጹት፣ ፋብሪካው ዘመናዊ ማሽን አስገብቷል። በዓመት ስምንት ሺህ 600 ሜትሪክ ቶን ፓይፕ የማምረት አቅም አለው። ነገር ግን፤ ፍትሐዊ ባልሆነው የግብር አከፋፋል መቸገሩን ጠቁመው፤ ፋብሪካው ማምረት የሚችለው 25 በመቶ ብቻ ነው።
በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው የሚያመርተው በዓለም ታዋቂ የሆኑ የግብዓት አምራቾችን ጥሬ ዕቃ ተጠቅሞ ሲሆን፤ ወደፊት ጥሬ እቃዎችን በአገር ውስጥ በማምረት በዘርፉ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የመሆን ዓላማ አለው። ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ጥራት ያለው ምርት እያመረተ መሆኑንም ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል።
የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እንደሚገ ልጸው፤ በግብርናው ዘርፍ ጥራት ያለው ምርት ለማምረት የግሪን ሀወስ ምርት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።
ፋብሪካው ለግሪን ሀውስ የሚሆኑ ምርቶችን ለአገራችንና ለአፍሪካ የማቅረብ አቅም አለው። ሆኖም መንግሥት ከውጭ ለሚያስገቡ ድርጅቶች ለማበረታታት ቀደም ሲል ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ቢፈቅድም ፋብሪካው የእሴት ታክስና የቀረጥ ዋጋ ስላለበት ዋጋው ጭማሪ ስላለው ምርቱን ተጠቃሚዎች የመግዛት ፍላጎት እንደሌላቸው አምኗል።
ወደፊት የተፈጥሮ ጋዝ በሱማሌ ክልል መመረት ስለሚጀምር ግብዓቱን በአገር ውስጥ በቀላሉ ማግኘት እንደሚቻልና ፋብሪካው ከውጭ የሚያስገባቸውን ግብዓ ቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ለማድረግ እንደሚሰራ አመልክቷል።
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ የተቋቋመው በአሜሪካ፣ በግብፅና በአማራ ክልል መንግሥ ታት ሽርክና ሲሆን፤ የተለያዩ ዓይነት የፕላስ ቲክና የግሪን ሀውስ ውጤቶችን ያመርታል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2011
በአጎናፍር ገዛኸኝ