አዲስ አበባ፡– የሰው ህይወት ሳይጠፋ፣ አካል ሳይጎድል፣ ንብረቶች ሳይወድሙ እና መፈናቀሎች ሳይከሰቱ በአገር በቀል የችግር መፍቻ መንገዶች፤ እንዲሁም የጸጥታ እና የደህንነት መዋቅሩ ቀድሞ በመከላከል ላይ እንዲያተኩር ምሁራን አሳሰቡ።
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አቶ ጋሻው አይፈራም፤ የጸጥታና የደህንነት መዋቅሩ ግጭቶች ታቅደውና ተቀነባ ብረው እስከሚፈጸሙ ድረስ ከመረጃ ውጪ የሚሆንበት ሁኔታ መኖር የለበትም ብለዋል፡፡
በአንድ አገር ውስጥ የጸጥታና የደህንነት መዋቅሩ ዋና ዓላማ ችግር ከተከሰተ በኋላ መድረስ ሳይሆን፤ አደጋ ከመከሰቱ አስቀድሞ የሰው ህይወት ሳይጠፋ፣ ንብረት ሳይወድም እና መፈናቀሎች ሳይከሰቱ የሚያከሽፍበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለ በትም አመልክተዋል፡፡ ለውጡ ያመጣው በጎ ነገር ቢኖርም የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች ጉድለት መስተካከል እንዳለባቸውም መክረዋል፡፡
አቶ ጋሻው፤ የመንግሥት አካላት የደህንነት ስጋት መኖሩ መረጃ ሲደርሳቸው ቅድመ መከላከል ላይ በፍጥነት ሊሰሩ ይገባቸዋል ብለ ዋል፡፡ ግጭቶች እንዳይከሰቱ፣ የሚስተዋሉትም እንዲከስሙ ሁሉም አካላት ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል፡፡ በተለይም የአደጋ ጊዜ ቀድሞ የመከላከል የመንግሥት አሰራር የተሻለ እንዲሆንም መክረዋል፡፡
የደህንነት ስጋት አለ ተብሎ ሲታሰብ በተለይም ከአካባቢው ማህበረሰብና በአካባቢው ካሉ አገር በቀል ተቋማት፣ ሽማግሌዎችና የሃይማኖት ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት መከላከል የሚቻልበት መንገድ መዘርጋት በዘላቂነት መተግበር የሚገባው መሆኑንም አቶ ጋሻው አብራርተዋል፡፡
በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በልማት ጥናት (development studies) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት አቶ ዘሪሁን ጋሻው፤በማንኛውም አገር፣ ማህበረሰብና በቤተሰብ ግንኙነት ውስጥ ግጭት ይጠፋል ተብሎ የማይታሰብ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ግጭት መኖሩ ጤነኛ ተብሎ የሚታሰብ መሆኑን በመጥቀስም፤ ዋናው ጉዳይ ግጭትን ለመልካም ነገር መጠቀሙ ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል፡፡ ግጭቶች የከፋ ውጤት ሳይኖራቸው መከላከል ላይ ማተኮር ይገባልም ብለዋል፡፡
የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ለግጭት መንስኤ ዋናው ምክንያት ተብሎ ይታሰባል የሚሉት አቶ ዘሪሁን፤ በፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉ ተዋንያን በመካከላቸው ያለው ግንኙነት አገር ውስጥ ላለው የሰላም ሁኔታ ወሳኝ ሁኔታ ተደርጎ እንደሚታይም አመልክተዋል፡፡
ፖለቲከኞች ልዩነታቸውን ለመፍ ታት የሚከተሉት መንገድ የሰለጠነ ካልሆነ ወደ ግጭት ያመራል ያሉት አቶ ዘሪሁን፤ ልዩነታ ቸውን ተነጋግረው በማጥበብ፣ በሚያግባቧቸው ጉዳዮች በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ መክረዋል፡፡
እንደ እርሳቸው ማብራሪያ፤ መንግ ሥት በጉያው አቅፎአቸው የሚገኙ አንዳንድ አመራ ሮችና ሌሎች አካላት ያላቸውን ስልጣን እና ተሰሚነት በመ ጠቀም ለግጭት መንስኤ እና አቀጣጣይ እየሆኑ ናቸው፡፡
በመሆኑም መንግሥት በጉያው ውስጥ ያሉ አካላትን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ማስ ተካከል ካልተቻለ ለወደፊትም አሳሳቢ መሆኑን እና ግጭት ሊነሳ የሚችልበትን ጊዜ ለማወቅ አዳጋች እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2011
በዘላለም ግዛው