ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው ዓመታዊው የበጎ ሰው ሽልማት የ2011 እጩዎች ጥቆማ ተጀምሯል። ይህም የእጩዎች ጥቆማ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
እንደወትሮው ሁሉ በሽልማቱ እጩዎች የሚጠቆሙባቸው አስር ዘርፎች የተካተቱ ሲሆን፤ እነዚህም መምህርነት፣ ሳይንስ (ህክምና ፣ቴክኖሎጂ፣ፊዚክስ፣ምህንድስና፣ኬሚስትሪ፣አር ክቴክቸር….ወዘተ)፣ ኪነ ጥበብ (ፎቶግራፍ)፣ በጎ አድራጎት፣ ቢዝነስና ሥራ ፈጠራ፣ መንግስታዊ የሥራ ፈጠራ፣ ቅርስና ባህል፣ ማህበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ እድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ዳያስፖራዎች የሚሉ ናቸው።
በእነዚህ ዘርፎችም እጩዎችን ለመጠቆም የሚፈልጉ ሁሉ በስልክ ቁጥር 0940-14 0813 በመደወል አልያም በዚሁ ስልክ የቫይበር፣ ቴሌግራም እና ኋትስ አፕን መጠቀም ይችላሉ ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በኢሜይል: begosewprize@gmail.com እንዲሁም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 150035፤ በአካል ጥቆማ ለመስጠት ለሚፈልጉ ጠቋሚዎች ደግሞ አግዮስ አሳታሚ ቢሮ ለም ሆቴል ማቴዎስ ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ላይ ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉም ተገልጿል። የበጎ ሰው ሽልማት ኮሚቴ ባሳለፍነው ሐሙስ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ የዘንድሮው የሽልማት መርሃ ግብር ነሐሴ 26 ቀን 2011ዓ.ም እንደሚውል ተገልጿል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2011