ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እ ኤ አ በግንቦት 2 ቀን 2019 ባወጣው ትንበያ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት በአማካኝ የ3. 3 በመቶ ዕድገት ሲያስመዘግቡ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የ7.7 በመቶ ዕድገት እንደምታስመዘግብ ድርጅቱ ገልጿል።
ድርጅቱ አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2018 3 በመቶ ያስመዘገበችው ዕድገት በ2019 ወደ 3.5 በመቶ እንዲሁም 2020 ደግሞ የ3.7 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ በትንበያውን አስቀምጧል።
ድርጅቱ በተፈጥሮ ሃብት ላይ ላይ ያልተመሰረተ ኢኮኖሚ ያላቸው የአፍሪካ አገራት በ2019-20 በአማካኝ የ6.3 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባሉ ብሏል።
እንደሪፖርቱ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአካባቢው አገራት በተፈጥሮ ሃብት ላይ ያልተመሰረተ ኢኮኖሚ ያላቸው አገራት በመሆናቸው አምስት በመቶና ከዚያም በላይ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ገቢያያቸውም ከሌላው አካባቢ በአንጻራዊ ፈጣን ዕድገት ያሳያል።
በአካባቢው ሶስተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ ባልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም እንኳን የ7.7 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ፤ መንግስትም የግሉን ዘርፍ እንዲጠናከር የጀመረውን ሪፎርም እንደሚቀጥልበት አስታውቋል ሲል የአይ ኤም ኤፍ በሪፖርቱ ጠቅሷል። የድርጅቱ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት የጥናት ዲፓርትመንት ሃላፊ ፓፓ ኒዲአዬ የአፍሪካ የዕድገት ምጣኔ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ገልጸው በተለይ ኢኮኖሚያቸው በተፈጥሮ ሃብት ላይ ጥገኛ ያልሆነ የአፍሪካ አገራት በ2019 ከ5 በመቶና ከዚያም በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ተናግረዋል። ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ሴኒጋል፣ ከትዲቯር በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው ያሉ ሲሆን የነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም ዕድገት እንደሚያሳይ ሃላፊው ተናግረዋል።
ተ ተ