ቬንዝዌላ በአሁኑ ወቅት ከባድ የሆነ የኢኮኖሚና የሰብኣዊ ቀውስ ውስጥ ምትገኝ አገር ነች፡፡ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ኢኮኖሚዋ በዋጋ ንረት የወደቀ ሲሆን እአአ 2018 መጨረሻ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እንዳጋጠማትም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በተከሰተው ቀውስ ምክንያት ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በአገሪቱ ባለው ቀውስ ረሀብ የተከሰተ ሲሆን በየቀኑ ከሰባት ህፃናት ውስጥ አንዱ በአልሚ ምግብ እጥረት ይሞታል፡፡ በተያያዘም በሚፈጠሩ ግጭቶች በየቀኑ 80 ሰዎች የሚገደሉ ሲሆን ይህ ሁኔታ ቬንዚዌላን በደቡብ አሜሪካ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ቀዳሚ ያደርጋታል፡ ፡ የመብራት ሀይል መቋረጥ ለዓመት የዘለቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መፈታት የማይቻልበት ደረጃ ደርሷል፡ ፡ የተፈጠረው ሁኔታ አስጨናቂ እና አሳዛኝ ሲሆን በአገሪቱ ያለው ሁኔታ በቀጣይ እየተባባሰ እንደሚሄድ ምልክቶች ይታያሉ፡፡
በአገሪቱ የተከሰተው ችግር ይበልጥ እንዲባባስ መነሻ የነበረው የአገሪቱ ብሄራዊ ምክርቤት ሸንጎ የተቃዋሚ መሪ የሆነው ጁአን ጓኢዶ በእአአ 2019 ጥር ላይ ፕሬዚዳንት ተደርጎ መሾሙ ሲሆን ይህ ሹመት ደግሞ አገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው የኒኮላስ ማዱሮ መንግስት ላይ ችግር በመፍጠሩ ነው፡፡ ጓኢዶ በምዕራባዊያን አገራት፣ በደቡብ አሜሪካ አንዳንድ አገራት እና በአለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ ይደረግለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ህዝቡንና መከላከያ ሀይሉን የማዱሮን መንግስት ለማውረድ ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ እያቀረበ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የማዱሮን መንግስት ለማውረድ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ ሩሲያ በበኩሏ ወደ ካራሳስ ወታደሮቿን በማሰማራት የማዱሮን መንግስት ለመርዳት ዝግጅት አድርጋለች፡፡
ማንኛውም የውጭ አገር ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ካለ አገሪቱ ወደ ማትወጣው ብጥብጥ ውስጥ የሚከታት ሲሆን እአአ 2001 አሜሪካ በአፍጋኒስታን ውስጥ ጣልቃ ገብታ የተፈጠረው አይነት ክስተት ቬንዚዌላን ሊያጋጥማት ይችላል፡፡ የቻቪስ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም የህዝቡን ድጋፍ እያጣ ሲመጣ ማዱሮ ተቀባይነት 20 በመቶ እየጨመረ መጣ፡፡ የነዳጅ ሀብቱ እየቀነሰ ሲመጣ የቻቪዝሞ አስተዳደር የተዳከመ ሲሆን በስልጣን ላይ ለመቆየት የተለያዩ የፖለቲካ ፖሊሲዎችን መከተል ጀመረ፡፡ ከዚህ ውስጥ እታችኛው ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን መደገፍ ይጠቀሳል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ሀይሎች ግፊት ቻቬዝ በሚያስገርም ሁኔታ እንዲወርድ ተደረገ፡፡ ይህ ሁኔታ በአገሪቱ የተወሳሰበ የፖለቲካ ሁኔታ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሁጎ ቻቬዝ እና ተከታያቸው ማዱሮ ኢንስትቲዩሽን ግንባታን ችላ በማለታቸው አስተዳደራቸው በሙስና እንዲጨማለቅ በር ከፍተዋል፡፡ እንዲሁም እራሳቸው የአገሪቱን በጀት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የቦሎቮሪያን ብሄራዊ ወታደራዊ ሀይል በመባል የሚታወቅ ቡድን ማደራጀታቸው ሊጠቀስ ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ማሳያው ከአስር ዓመታት በፊት ቻቬዝ የቦሎቮሪያን ብሄራዊ ወታደራዊ ሀይል አዛዥ የአገሪቱን ወሳኝ የተባሉ ሀብቶች የማዕድን ቦታዎችን ጨምሮ እንዲቆጣጠር ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት አብዛኛዎቹ የማዕድን ማውጫዎች የተዘጉ ሲሆን የወታደራዊ ሀይሉ አባላት በህገወጥ መንገድ ከማዕድናቱ ትርፍ ያገኙ ነበር፡፡ ወታደራዊ ሀይሉ አባላት እንደሚሉት፤ ከማዕድን ሽያጭ ውጭ በአደንዛዥ እፅ እና በህገወጥ ነዳጅ ንግድ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡
ቻቬዝ ከስልጣን ሲወርድ የወታደራዊ ሀይሉ አመራሮች የማዱሮን መንግስት በመደገፍ ቀድሞ የነበራቸውን ህገወጥ እንቅስቃሴ ቀጠሉ፡፡ የማዱሮን መንግስት ከመውደቅ የሚታደጉት የቦሎቮሪያን ብሄራዊ ወታደራዊ ሀይል ብቻ አደለም። ቀደም ብሎ አንዳንድ ወታደራዊ አመራሮች የቻቬዝን መንግስት ይቃወሙ ስለነበር መፈንቅለ መንግስት አስበው ነበር፡፡ በዚህም ቻቬዝ ለታማኝ ደጋፊዎቹ መሳሪያ እደላ አድርጎ ነበር፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የተመራው የቦሊቮሪያን ወታደራዊ ሀይል ነበር፡ ፡ በማዱሮ አስተዳደር ጊዜ ስማቸውን በመቀየር ‹‹ኮሌክቲቭ›› በሚል እንደ አዲስ ተደራጅተ ዋል፡ ፡ የዚህ ወታደራዊ ቡድን ዋነኛ ዓላማ የሶሻሊዝምን ርዕዮት አለም እንዲቀጥል ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ቡድኑ ወታደራዊ ወንጀሎች ውስጥ የተዘፈቀ ነው፡፡ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ በጎረቤት አገራት አካባቢ የሚደረገውን ህገወጥ እንቅስቃሴ እየመራም ይገኛል፡፡
እነዚህ ወታደራዊ ሀይሎች ከፍተኛ ስልጣን በማግኘታቸው ባለፉት ሀያ አመታት ያሻቸውን በማድረጋቸው የቻቬዝን ውድቀት አፋጥነውት ነበር፡ ፡ በተመሳሳይ የማዱሮን መንግስት መደገፍ የቀጠሉ ሲሆን ቀደም ብሎ ሲያደርጉት የነበረውን ሙስናና ቅጥ ያጣ ህገወጥ ንግዳቸውን አጧጡፈው ቀጠሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከጓኢዶ ተቃውሞውን እንዲቀ ላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ አሁን በቬንዝዌላ ያለው ሁኔታ አፍጋኒስታን በአሜሪካ መሪነት የተደረገው ወረራና ችግሩን ለመፍታት የተደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም አሁን ያለውን የአፍጋኒስታን ቀውስ ጋር የመመሳሰል ነገር አለው፡፡ የአፍጋኒስታ ሁኔታ ለቬንዝዌላ እንደ ማስጠንቀቂያ መቀመጥ ያለበት ሲሆን፤ ምክንያቱም አሜሪካ የማዱሮን መንግስት ለማውረድ ወረራ ብትፈፅም ተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ የቬንዝዌላ ተቃዋሚዎችና የውጭ ሀይሎች የማዱሮን መንግስት በጉልበት ለመንጠቅ ሙከራ ቢያደርጉ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆነው የአገሪቱ ወታደራዊ ሀይል እና ከኮሌክቲቮች ጋር ከፍተኛ የሆነ ጦርነት ይካሄዳል፡፡ ይህ ደግሞ በአገሪቱ ያለውን ቀውስ በማባባስ ወደ ርስበርስ ጦርነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
በግጭት ወቅት የቦሎቮሪያን ብሄራዊ ወታደራዊ ሀይል ለሁለት ሊሰነጠቅ ቢችል የተወሰኑት የማዱሮ ተቃዋሚዎችን ደግፈው ሊዋጉ እንደሚችሉ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ ሩሲያ ግጭት ቢፈጠር በቀጥታ ተሳታፊነትን አትፈልግም፡፡ ግጭት ቢቀሰቀስ ለኮሌክቲቮችና ለአዳዲስ ወታደራዊ ሀይሎች መሳሪያና ሌሎች ግብዓቶችን በማቅረብ ድጋፍ የማድረግ እቅድ አላት፡፡ ወታደራዊ ግጭቶች ሲፈጠሩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢንስትቲዩሽን ግንባታ ላይ እንቅፋት ይፈጥራል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ወንጀለኝነትና ዝርፊያ እንዲስፋፋ በማድረግ የኮሌክቲቮ ጎረቤት አገራትን ጨምሮ እንዲቆጣጠር እድል ይከፍትለታል፡ ፡ በቬንዝዌላ ጠፍቶ የነበረው የደፈጣ ውጊያ ከብዙ ዓመታት በኋላ ተመልሶ እየታየ ይገኛል፡ ፡ በአገሪቱ ሰላም ለማምጣት የአለም አቀፍ ማህበረሰብና የቬንዝዌላ ተቃዋሚዎች ቅድሚያ የችግሩን ውስብስብነት መረዳት አለባቸው፡፡
ነገር ግን ለተፈጠረው ሁኔታ የተጠናና ለውጥ አምጪ ሰትራቴጂ መጠቀም ካልቻሉ ቀውሱ ማይቆምበት ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀርም፡፡ የቬንዝዌላ ተቃዋሚዎች ትክክለኛው ስልጣን ማን ጋር እንዳለ ማወቅና መቀበል አለባቸው፡፡ በአገሪቱ ያለው ተቃውሞ አገሪቱን እየመራ ያለው መንግስት ማውረድና ሌላ መንግስት ለመመስረት ያለውን ፍላጎት መረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሁን ዋነኛ ጥያቄ መሆን ያለበት በምን አይነት መንገድ የማዱሮን መንግስት ማስወገድ ይቻላል የሚለው ነው፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ደም መፋሰስ ሳይኖር ሽግግር ማምጣት እንደሚቻል ዝግጅት ይጠይቃል።
በቬንዝዌላ የሚታየው ችግር ትክክለኛ አማራጭ ለመምረጥ አንዱን መንገድ እንጂ ሁሉንም አማራጭ መንገድ እየተከተለ አይደለም፡፡ ይህን ጉዳይ ለማስረዳት በቅርቡ የተከሰተ ሁነት ማንሳት ይቻላል፡ ፡ በአሜሪካና በማዱሮ መንግስት ላይ የተነሱ ትችቶች የቬንዝዌላን ተቃዋሚዎች ከጨዋታ ውጭ አድርጎት ነበር፡፡ በቬንዝዌላ መሀል ሰፋሪ የሚባሉ ፖለቲከኞች ሲኖሩ በዚህ ውስጥ ስመጥር ሰዎች ተካተውበታል፡፡ በዚህ የቀድሞ የመንግስት ባለስልጣናት የህገመንግስቱ ጠበቂዎች ነን የሚል ስም ለራሳቸው ሰጥተዋል፡ ፡
ለአገሪቱ ደህንነትም ንግግር ሳይሆን የማዱሮን መንግስት መቀየርና ህዝበ ውሳኔ መደረግ አለበት የሚል ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡ ይህ አካሄድ አገሪቱን የሚበታትን መሆኑ የፖለቲካ ተንታኞቸች ይናገራሉ፡ ፡ በምን አይነት መንገድ አሁን ያለውን የቬንዝዌላ መንግስት መተካት እንደሚቻል የተቀመጠ ነገር የለም፡፡ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ 10 በመቶ የህዝቡን የድጋፍ ፊርማ የሚሰበስበው ማን እንደሆነ አልተወሰነም፡፡ በሌላ በኩል ማዱሮ ስልጣን ላይ እንዳይቆይ ድምፅ የሚሰጡ ዜጎች የሚመርጡት ሌላ ፓርቲ አላዘጋጁም፡፡ በነዚህ ሁኔታዎች የአገሪቱ ችግር እየተባባሰ ይገኛል፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2011
መርድ ክፍሉ