ናይትረስ ኦክሳይድ ጋዝን ያሸተተ ሁሉ ከዚህ በፊት ተሰምቶት የማያውቅ ልዩ የደስታ ስሜት ስለሚሰማው ከመሬት ተነስቶ የኮረኮሩት ያህል ሊስቅ ይችላል። ወይም ደግሞ በአካባቢው ያገኘውን ሰው ሁሉ ሙሃመድ አሊንም ይሁን ማይክ ታይሰንን ካልደበደብኩ ብሎ ሊገለገል ይችላል፣ ያለ ምንም ሙዚቃና ጭብጨባ እስክስታ ሊወርድ ይችላል።
ብቻ በአጠቃላይ ይህን ጋዝ ያሸተቱ ሰዎች ሁሉ ከአንድ ጤናማ ሰው የማይጠበቁ አስቂኝ ድርጊቶችን ስለሚፈጽሙ ጋዙ “አስቂኝ ጋዝ” የሚል ቅጽል ስምን ሊያገኝ ችሏል። ከዚህ የተነሳ ዋናው ጥቅሙ እስኪታወቅ ድረስ ናይትረስ ኦክሳይድ እንደተገኘ መጀመሪያ አካባቢ በመዝናኛ ድግሶች ላይ ሰዎችን ለማሳቅ አገልግሎት ነበር የሚውለው።
በዘመኑ በየከተማው ሕዝብ በተሰበሰበ ባቸው የመዝናኛ ማዕከላት እየዞሩ ስለ ናይትረስ ኦክሳይድ መግለጫ በመስጠትና ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ጋዙን እያስሸተቱ ታዳሚዎቹን የሚያዝናኑ ሰዎችም ነበሩ።
አንድ ቀን በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1844 ዓ.ም ሃርትፎርድ ኮኔክቲከት አሜሪካ ውስጥ በአንድ የመዝናኛ ትር ዒት ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ተፈጠረ። እንደተለመደው በየመዝናኛ ትርዒቶች እየዞረ ናይትረስ ኦክሳይድን የሚያስተዋውቅና ፈቃደኛ ሰዎችን እያሸተተ ታዳሚዎችን በማዝናናት ሥራ ላይ የተሰማራ ኮልተን የተባለ ግለሰብ መድረክ ላይ ወጥቶ ንግግሩን አድርጎ ከጨረሰ በኋላ “በፈቃደኝነት ጋዙን ማሽተትና የሚፈጥረውን ስሜት ሞክሮ ማየት የሚፈልግ ሰው ካለ?” በማለት ታዳሚውን ይጠይቃል።
ሳሙኤል ኩሊ የተባለ ሰው እጁን ያወጣል። ከዚያም ኮልተን የያዘውን ናይ ትረስ ኦክሳይድ ጋዝ እንዲያሸት ለኩሊ ይጋ ብዘዋል። ሚስተር ኩሊም ጋዙን ተቀብሎ ማሽተት ይጀምራል። ወዲያው ወተት እንደጠገበች የሰኔ እንቦሳ በታዳሚው መሃል እንጣጥ፣ እንጣጥ ማለት ይጀምራል።
ሰውየው ደስታ አይሉት ስካር በሚመስል ስሜት ውስጥ ሰምጦ እየተወራጨ ሲዘል ያደናቅፈውና ክፉኛ ይወድቃል። ሰዎች ተረባርበው ከወደቀበት ሲያነሱትም ሁለት ጥርሶቹ ወልቀው ድዱ በደም እየታጠበ ነበር። ሆራስ ዌልስ የተባለ በዘመኑ ታዋቂ የጥርስ ሃኪምም በመዝናኛ ትርዒቱ ላይ ታድሞ ስለነበር ኩሊ ላይ የደረሰውን አደጋ ከታዳሚው ጋር አብሮ ይመለከት ነበር።
ታዲያ አስገራሚው ነገር ሃኪሙ ዌልስ ቀርቦ የኩሊን ሁኔታ በሚመለከትበት ጊዜ ተጎጂው ላይ ምንም ዓይነት የህመም ስሜት አለማየቱ ነበር። ይህንን የተመለከተው ዶክተር ዌልስም ጋዙ ሌሎች በሽተኞች ላይም ቢሞከር የህመም ስሜታቸውን በመግደል ሳይሰቃዩ እንዲታከሙ ማድረግ እንደሚቻል አሰበ። በመሆኑም ዌልስ ጋዙን መሞከሩን ቀጠለ። ፍቱንነቱን የበለጠ ለማረጋገጥ በራሱ ላይ ሞክሮ ለማየት ወሰነ።
ከዚያም ዌልስ ናይትረስ ኦክሳይድ ጋዙን ራሱ አሽትቶ ጓደኛው ጥርሱን እንዲነቅ ለው አደረገ። እንዳሰበውም ሙከራው ስኬታማና ውጤቱም አስደሳች ነበር። በራሱ ላይ ባደረገው የሙከራ ውጤት በጣም የተበረታታው ዶክተር ዌልስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ግኝቱን ለማሳየት አሰበ።
በዚህም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አንዱን የጥርስ በሽተኛ ጋዙን እንዲያሸተው ካደረገ በኋላ ጥርሱን ለመንቀል ሲሞክር ጋዙ ገና ሥራውን አልጀመረ ኖሮ ታካሚው ጩኸቱን አቀለጠው። የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተማሪዎችም በዌልስ ድርጊት ተናደው አዋርደውና ሰድበው አባረሩት።
ስህተቱ የተፈጠረው በትክክል ባለመጠ ቀሙ ምክንያት እንጂ ጋዙ ይሰራ እንደነበር እርግጠኛ የነበረው ዌልስ ግን ናይትረስ ኦክሳይድን በመጠቀም ደንበኞቹን ማከም ጀመረ። ብዙም ሳይቆዩ ሌሎች የጥርስ ሃኪሞች ናይትረስ ኦክሳይድ ጋዝን ለማደንዘ ዣነት ይጠቀሙበት ጀመር። ከዌልስ በፊት ናይትረስ ኦክሳይድ ጋዝ ለማደንዘዣነት ይጠ ቅም እንደነበር የሚያውቁ ሌሎች ሃኪሞችም የነበሩ ቢሆንም ግኝታቸውን ግን ለማንም አልተናገሩም ነበር።
ሆኖም የዌልስ ከናይትረስ ኦክሳይድ ማደንዘዣን የመፍጠር ዝና በናኘ ጊዜ “ማደንዘዣን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀምን እኛ ነን” በሚል አራት የሚሆኑ ዶክተሮች ጭቅጭቅ አስነስተው ነበር። በመጨረሻም የአሜሪካው የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር የፈጠራ ባለቤትነት ዕውቅናውን ለሆራስ ዌልስ ሰጥቶታል።
ከሁለት ምዕተ ዓመታት በፊት እጅግ አስቸጋሪ ከነበሩ ሥራዎች መካከል ዋነኛው የነበረው የቀዶ ጥገና ህክምና ዕድሜ ለናይትረስ ኦክሳይድ አሁን በቀላሉ ይከናወናል። በጊዜው በአደጋም ይሁን በሌላ በሽታ ምክንያት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ቁስል መስፋት፣ እንደ ትርፍ አንጀትና የመሳሰሉ የውስጥ ደዌ በሽታዎችን ለመፈወስ ቀዶ ጥገና ማድረግ ሌላው ይቅርና የታመመ ጥርስን መንቀል ለታካሚው መራር ስቃይ ነበር።
ለአካሚውም እንደዚሁ በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ሥራ ነበር። ናይትረስ ኦክሳይድ የተባለ ጋዝ በመገኘቱና ጥቅም ላይ በመዋሉ ግን ከ1980ዎቹ ወዲህሁኔታዎች እየተቀየሩ መጡ። ምክንያቱም ከላይ ባየነው መንገድ በድንገት ከአስቂኝነት ወደ ማደንዘዣነት የተቀየረው ናይትረስ ኦክሳይድ የተባለ ጋዝ በሚሸተትበት ጊዜ ሰዎችን የማሳቅና ልዩ የደስታ ስሜት የመፍጠር ባህሪ ስላለው ቀዶ ጥገና ለሚደረግላቸው ሰዎች በማሽተት ህመማቸውንና ስቃያቸውን እንዲረሱና ህክም ናቸውን በአግባቡ እንዲያደርጉስላስቻለ ነው።
እናም በድንገት የሚፈጠሩ ችግሮችና አጋጣሚዎች ከስህተት መማሪያ ብቻ ሳይሆኑ አዲስ ነገር መፍጠሪያም ሊሆኑ ይችላሉና በማማረር ፈንታ ማስተዋል ይበጃል። በርግ ጥም የአብዛኞቹ ፈጠራዎች መነሻ ችግሮች ለመሆናቸውታሪክ የመዘገበው የዓለማችን እውነታ ነው። መረጃውን ለማጠናቀር ዊኪፒ ዲያን፣ ጆርናል ኦፍ አንስቴዥያ ሂስትሪና ክዊንስ ኦርቻርድ ዴን ታል ኬር የተባሉ ድረ ገጾችን ተጠቅመናል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17/2011
በይበል ካሳ