በዓለም ታሪክ በጭካኔ በግንባር ቀደምትነቱ የሚጠቀሰው ከጥንቱ ዓለም አሲሪያን ኢምፓየር ሲሆን፤ በዘመናዊ ዓለም ደግሞ እነ ናዚን ፣ ኤዲያሚን ዳዳ ፣ ሞቡቱ ሴሴሴኮ፣ ሳሙኤል ዶ ወዘተ እንደሆኑ የዓለም ማህበረብ የሚስማማበት ሐቅ ነው። በዓለም ብሎም በኢትዮጵያ እንደ ልዩ ፍጥረት የተከሰተውን አሸባሪው ጁንታ ከሳጥናኤል በዕድሜ ያንሰ ይሆን አንደሆን እንጂ በተግባር ግን ሳጥናኤልን እንደሚያስንቀው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአንክሮ ቢመለከት ከላይ የጠቀስናቸውን እንደ አውሬ የሚነሱ አካላትን ይቅር በሉን፤ ማሩን እንደ ወያኔ ያለ አረመኔ አይተን ስለማናውቅ ነው እናንተን አረመኔ ያልናችሁ ተሳስተናል ብለው ይቅርታ እንደሚጠየቁ አልጠራጠርም።
የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም ራሱን አደራጅቶ ጫካ በማስገባት ትህነግ ብሎ መጥራት ከጀመረ በኋላ የቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ የጥፋት ሰለባ የሆኑት የትግራይ ሰዎች ናቸው። ለዚህም ዋናው ምክንያት ደግሞ ወያኔ በየቦታው ያደርገው የነበረውን ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅስቀሳ የሚቀበለው የትግራይ ህዝብ ሊያገኝ አለመቻሉ ነበር።በዚህ የተበሳጨው ትህነግ የትግል እቅዱን ለትግራይ ተወላጆች ለመጋት በማሰብ የትግራይ ተወላጆችን ያስገድድ ያዘ።
የትግል እቅዱን አንቀበልም ባሉ ሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ ዘግናኝ ዕርምጃዎችን ወሰደ። በዚህም አሸባሪው ትህነግ የተፈጠረበት የካቲት አስራ አንድ ቀን በትግራይ ሲከበር መላው የትግራይ ተወላጆች ለቀኑ መጥሪያ ስም ሰጡት።ለምሳሌ በተምቤን የካቲት 11ን “የተረገመች ቀን” ሲሏት፤ በዓድዋና አክሱም ደግሞ “የጨለማ ቀን” የሚሉት ሲሆን፤ በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” እያሉ አንደሚጠሩት ማንም የትግሬ ተወላጅ እና ከህወሓት ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የሚያውቁት ሐቅ ነው።
ይሁን እና ቀስ በቀስ እነሙሴን የመሰሉ በትግራይ አርሶ አደር የሚወደዱ ታጋዮች በፈጠሩት ቅስቀሳ የገጠሩ የትግራይ ተወላጅን በማሳመን ወደ ትጥቅ ትግሉ ያጓጉዙ ያዙ።መግደል ሱሱ የሆነው ትህነግ ይህ አርሶአደሩን አነቃንቆ ወደ በርሐ ያስገባላቸውን ታጋይ ሙሴን ወደፊት ለስልጣናችን ያሰጋናል በማለት በጦርሜዳ በተቀነባበረ ሴራ መገደሉን ተስፋዬ ገብረ አብ የጋዜጠኛው ማስታወሻ በሚለው መፅሐፉ በግልጽ አስቀምጦታል።
ትህነግ የሽብር ድርጊቱ ጫፍ የወጣ በመሆኑ ቤተክርስቲያን እና መስጅድም ከትህነግ ጥፋት ሊያመልጡ አልቻሉም።የዋልድባ ገዳም እና መነኮሳቱ ላይ የደረሰውን ግፍ ማንም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ሐቅ ነው።ሌላው የአሸባሪው ትህነግ ዘግናኝ ተግባር ገፈት ቀማሹ ደግሞ የኢትዮጵያ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ነው።ወያኔ በ2005 ዓ.ም በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሆኖ የማያውቅ እና ከእስልምና አስተምሮ በተጻራሪ በሆነ መልኩ መጅሊስ በቀበሌ አስመረጠ።ለምን መጅሊስ በቀበሌ ይመረጣል ብለው የተቃወሙ የሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን በሽብር ወንጀል እየከሰሰ በማሰር በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ አረመኔአዊ ድርጊት ፈጸመባቸው። የስልምና አባቶችን አሰረ፤ ገደለ።ከዚህ ጋር ተያይዞ በ2005 ነሐሴ ወር ላይ በደሴ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉትን ሼህ ኑሩ ይማምን የሚረሳ ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም።
የአሸባሪው ትህነግ ሰዎች ባድሜን እንደ ትልቅ ነገር በማንሳት እና ከኤርትራ ጋር በመፋለም እስከአሁን አላማው ምን እንደሆነ የማይታቀውን ጦርነት እንዲደረግ ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊን እንዲፈጁ አድርገዋል።
በ2008 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በመላ አገሪቱ በተለይም ደግሞ በኦሮሞ ፣ በአማራ ፣ በሶማሊያ ፣ በአፈር፣ በደቡብ በነበረው አመፅ ሕወሓት ከ5ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን በወቅቱ ይፋ ያደረገው ሒዩውማን ራይትስ ዎች ከእነዚህ ከተገደሉት ውስጥም የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥራቸው እንደሚበዛም ድርጅቱ ገልፆ እንደነበር አይዘነጋም።
በጋንቤላ በአኛዋክ ህዝብ ላይ በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በገፍ ለመዝረፍ በማሰብ ጁንታው በሦስት ቀናት ውስጥ 424 የአኙዋክ ብሄረሰቦች መገደላቸውን እና 16ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎረቤት ሱዳን መሰደዳቸውም በህውሓት የግፍ ድርጊት ዘመን በጉልህ ሊጠቀስ የሚችል ጭፍጨፋ ነው።
በተመሳሳይም የሶማሌ ህዝብ በአሸባሪው ህውሓት ምክንያት በርካታ ግፎች ተፈጽመውበታል። በክልሉ ያለውን ሀብት ተቆጣጥሮ ያለማንም ከልካይ ለመመዝበር በራሱ አምሳል ገዳይ ቡድን በማደራጀት በጠራራ ፀሐይ ንጹሐን ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል። ቤተ ክርስቲያኖችን በማቃጠል የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ በብዙ ሠርቷል። ሰዎች ብሄራቸው እየተለየ ከቤታቸው ተጎትተው እንዲገደሉ አድርጓል። ሰዎችን ከአራዊት ጋር በማሰር በዚህ ዘመን ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት ግፍ ተፈጽሟል።
ከዚህ አልፎ የለውጡ መንግሥት መምጣት ሲቆረቁረው ቆይቶ አሁን ደግሞ መከላከያን በመተንኮስ አልፎ ተርፎ ለትግራይ ህዝብ ሲባል በመንግሥት በኩል የተሰጠውን የተኩስ አቁም አዋጅ ሽሮ ህዝብ እንዲያልቅ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ አንዲሞቱ ጠንክሮ እየሠራ ይገኛል።
ይህም አልበቃ ብሎት በንጹሐን ላይ ዘር ማጥፋት መፈጸሙን ከመጀመር አልፎ ቀጥሎታል።ለምሳሌ በ2013 ዓ.ም የሆነውን ብቻ ብንመለከት መጀመሪያ በአማራ ክልል በማይካድራ በጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በተፈፀመ ጥቃት አንድ ሺህ አምስት መቶ ንፁሐን ሰዎች ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ተፈፅሟል።
ከዚያም በነሐሴ በአፋር ክልል በጋሊኮማ 270 አካባቢ ከእነዚህ መካከል 107 የሚሆኑ ሕፃናትም በዚሁ በአሸባሪው ብድን ተጨፍጭፈዋል።ቀጥሎም በአማራ ክልል ተመሳሳይ ድርጊት የተፈፀመ ሲሆን፤ እስከ አሁን ባለው መረጃ ከባድ መሳሪያን ጭምር በመጠቀም በተፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት በአንድ መንደር ከመቶ ያላነሱ ሰዎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ አድርገዋል።እነዚህ የተረጋገጡ ቢሆንም የህውሓት አሸባሪ ቡድን በተለያዩ አካባቢዎችም የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨርሶ የመግደል፤ ከነቤታቸው የማቃጠል እና ሕፃናትና ሴቶች ሳይል ሁሉም ላይ በጅምላ ተኩስ በመክፈት እየገደለ መሆኑን የዓይን እማኞች ምስክርነት በመስጠት ላይ ናቸው።
የለውጡ መንግሥት ከመጣ ጀምሮ አሸባሪው ትህነግ በተለያዩ አካባቢዎች እና ክልሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዘረጋው የሴራ መስመር እንዲገደሉ አመቻችቷል።ይህን ታሪክ የማይዘነጋው ከመሆኑም በተጨማሪ አሁን ደግሞ መከላከያን በመተንኮስ አልፎ ተርፎ ለትግራይ ህዝብ ሲባል በመንግሥት በኩል የተሰጠውን የተኩስ አቁም አዋጅ ሽሮ ህዝብ እንዲያልቅ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ አንዲሞቱ ጠንክሮ እየሠራ ይገኛል።ይህም አልበቃ ብሎት በንጹሐን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ከመጀመር አልፎ ቀጥሎታል።ለምሳሌ በ2013 ዓ.ም የሆነውን ብቻ ብንመለከት መጀመሪያ በአማራ ክልል በማይካድራ ፣ ከዚያም በአፈር ክልል በጋሊኮማ ፣ ቀጥሎም በአማራ ክልል በአጋመሳ በከባድ መሳሪያ ጨምሮ በመጠቀም አሰቃቂ የሆነ የዘር ጭፍጨፋ አደረገ።
አሸብር ኃይሉ
አዲስ ዘመን ነሐሴ 18/2013