መነሻው ምን እንደሆነ በውል ሳያውቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል? የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል። የአቀማመጥ ሁኔታ፣ የሚጠቀሙት ጫማ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛውና የታችኛው ጀርባ ህመም ያስከትላል።
የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶች
1. የቢሮ ወንበር
የቢሮ ወንበር ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ሲቀመጡ ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ይፈጥሩበታል። አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል። ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል።
2. የሚያደርጉት ጫማ
ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የማይገባ/ትክክል ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል። ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል።
3. የሚተኙበት ፍራሽ
የሳሳ (ስስ) ፍራሽ መጠቀም የታችኛውን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል። በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ በጡንቻዎች እና የአከር ካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ውጥረት ይፈጥራል።
4. የጀርባ ቦርሳ
የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል ይኖርዎታል። ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርባ ህመም ምክንያት ነው።
በአንድ በኩል ያለው የሰውነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርባና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።
5. በሆድ በኩል መተኛት
በሆድ በኩል ተደፍተው ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል። በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰውነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል። ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው።
6. ትከሻ ወይም አንገት ለረጂም ሰዓት ማዘንበል
አንገትን አዘንብሎ (ደፍቶ) መቆየት ወይም መጓዝ በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል።
7. ላፕቶፕና ስማርት ስልኮች
በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎ ቻቸው ፍቅር ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው።
በስራ በተጠመዱበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል በመያዝ ለረጅም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል።
8. ከመጠን ያለፈ ውፍረት
ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣ መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል።
አብዛኛዎቹ በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ያጋጥማቸዋል።
9. እግርን አጣምሮ መቀመጥ
እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት ይሳነዋል። ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል።
በተጨማሪም የደም ዝውውር በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን (Varicose vein) ለተባለ በሽታ ያጋልጣል።
10. ሲጋራ ማጨስ
በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ (Disc) የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጐን አጥንት ችግር ያስከትላል።
በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል። በመሆኑም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር ያጋጥማቸዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 16/2013