ዳንኤል ዘነበ
ጀርመን ውስጥ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች በላይ የአልዛይመር በሽታ ተጎጂ ናቸው። የአንጎል የነርቭ ሴሎች ሲሞቱ ሰዎች መርሳት ይጀምራሉ፤ የመናገር እና የማስታወስ ችሎታቸውም ይዳክማል። እንደ የጀርመን የአልዛይመር ማህበረሰብ መረጃ የታማሚው ቁጥር እስከ 2050 ዓ.ም በእጥፍ ሊጨምር ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ስለበሽታው በቂ ግንዛቤም ስለሌላቸው አንድ ሰው በበሽታው መያዙ የሚረጋገጠው ጉዳቱ ሥር ከሰደደ በኋላ ነው። እስካሁን የተደረጉ የህክምና ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ በሽታውን ማዳን አይቻልም። እስካሁን ያለው ተሞክሮ እንደሚያሳየው፤ አብዛኞቹ የአልዛይመር ታማሚዎች ከ80 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች ሲሆኑ፤ 70 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው። ይሁንና በሽታው በጎልማሳ እድሜም ሊይዝ ይችላል።
የበሽታው ምንነት
የማስታወስ ችሎታ ህይወታችን ይበልጥ ጣዕም ያለው እንዲሆን ያደርጋል። በህይወት ዘመናችን ስንኖር ያለፍናቸውን ህይወቶች በትውስታ መመለስ የተለመደ ነው። ትውስታዎቻችንም የሚያሳዝኑ፣ የሚያስቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በተለያዩ የህመም አይነቶች እና በእድሜ መግፋት ምክንያት ይህንን ትውስታ ልናጣ እንችላለን። በየቀኑ ወደ አዕምሯችን የሚመጡትን መረጃዎችን አዕምሯችን መዝግቦ የትውስታ ማህደር ክፍላችን ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርበታል። ነገር ግን አዕምሯችን ይህንን ተግባር በትክክል ማከናወን ካቃተው፣ አንድ ገለሰብ የተለመደ ሥራውን ማከናወን ይቸገራል። ይህ ችግር ያለበት ግለሰብ የመርሳት ችግር እንዳለበት በማሰብ አስፈላጊውን ምርመራና ህክምና ሊደረግለት ይገባል። የመርሳት ችግር ብዙ ጊዜ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ቢሆንም አሁን ላይ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየትኛውም እድሜ ክልል ሊከሰት እንደሚችል ነው። ይሁንና እድሜያቸው ከ65 ዓመት በታች የሆኑት ላይ ግን አነስተኛ ነው።
መነሻ ምክንያቶች
- አልዛይመር
- የደም ግፊት ወይም መርጋት ህመም
- የኤች አይቪ ኤድስ ህመም
- አንጎላችን ተደጋጋሚ አካላዊ ጥቃት ሲደርስበት ለምሳሌ ጭንቅላታቸው በተደጋጋሚ የተመቱ ሰዎች
- የተለያዩ ሌሎች የአዕምሮ ህመሞች በተለይ የድብርት ህመም
- አካላዊ የህመም አይነቶች ምሳሌ የቫይታሚን ምግብ እጥረቶች፣ የእንቅርት ህመም፣ የተለያዩ የአንጎል እጢዎች
- ለረጅም ጊዜ ማጨስና የአልኮል መጠጥ ማዘውተር
- እንዲሁም በዘር የመጋለጥ ሁኔታ እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች የመርሳት ችግር ሊያመጡ ይችላሉ።
ምልክቶቹ
³ ያስቀመጡትን ዕቃ መርሳት
³ በሂደት ቀጠሮ መርሳት፣ ዕቃ ገዝተው መልስ
አለመቀበል፣ የሚሰሩትን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት መቸገር፣
³ የመርሳት ችግሩ እየባሰ ሲመጣ የሚያውቋቸውን ሰዎች ስም መቀላቀል፣ ሁኔታው እየበረታ ሲሄድ እድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ ሲሆን የልጆቻቸውን ስም እስከ መርሳት፣ አንድ ወሬ ደጋግመው ማውራት፣ ቤታቸው ቁጭ ብለው ቤቴ ውሰዱኝ ማለት
³ የቅርብ ጊዜ ክንውኖችን አለማስታወስ ወይም አዲስ መረጃ መያዝ አለመቻል፣ እየቆየ ሲሄድ ራቅ ባለጊዜ የተከናወነውን ጭምር መርሳት ይመጣል
³ ኑራቸውን በዕቅድና በማስተዋል ለመምራት መቸገር
³ ዘዋሪ መሆን ወይም አላማ የሌለው እንቅስቃሴ ቤት አካባቢ ወይም ከቤት ውጭ ሲያደርጉ ማስተዋል
³ በቀላሉ ቁጡ መሆን፣ መነጫነጭ
³ ዝምታን መምረጥ፣ የመከፋት ወይም የመጨነቅ ስሜት ማሳየት
³ ተጠራጣሪ መሆን
³ በህይወት የሌሉ ሰዎችን አብረው እንዳሉ ማሰብ
³ እንቅልፍ በአግባቡ አለመተኛት ወይንም የእንቅልፍ ሰዓት መዛባት
ሕክምናው እና ጠቃሚ ምክሮች
አንድ የቤተሰብ አባል በመርሳት ህመም ሲጠቃ ግለሰቡን ለመርዳት ወይንም ራሳቸውን ካላስፈላጊ ጫና ለመጠበቅ የሚከተሉትን ነጥቦች መሞከር ያስፈልጋል። ምክንያቱም ጫናው እየበዛ ሲመጣ ጤናማ የነበሩትን የቤተሰብ አባላት ለድብርት ወይንም ለጭንቀት ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ።
³ እንዲህ አይነት ችግር የተስተዋለበት ሰው ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መውሰድ
³ እንዲሁም ግለሰቡን የሚንከባከቡ ሰዎች ቶሎ ቶሎ ባይቀያየሩ፣የሚኖሩበት ክፍል የበዛ ብርሃን ባይኖረው እንዲሁም ጫጫታ የማይበዛበት ቢሆን ይመረጣል።
³ የማታ እንቅልፋቸውን ለማሻሻል ቀን ላይ እንዳይተኙ፣ የሚያነቃቁ ነገሮችን እንዳይወስዱ፣ ሞቅ ባለ ውሃ ገላቸውን እንዲታጠቡ ማድረግ።
³ በተጨማሪም የተዛባ የእንቅልፍ ሁኔታ፣ አግባብነት የሌለው የበዛ ጥርጣሬ፣ ብስጩነት፣ እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩት መሰል የባህሪይ ለውጦችን በመድሃኒት ማሻሻል ስለሚቻል ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መሄድ ያስፈልጋል።ምክንያቱም የመርሳት
ችግር ችላ ከተባለ ጫናው እየበዛ እንደሚመጣና ያልታሰቡ ችግሮችን ያስከትላልና።
ምንጭ ፦ የዶክተር 8809