ከትናንት ዛሬ ከዛሬ ነገ ሰው እየሆኑ መሄድ የሚቻለው ዛሬ ላይ ቆሞ ትናንትን ቃኝቶ ነገን ማየት ሲችል ነው።ሐገሬ እንደ ሐገር ያለፈችባቸው መንገዶች አለማየት ዛሬን በቅጡ እንዳልገነዘብ ከትናንትም በቅጡ መማር እንዳልችል ያደርገኛልና ከትናንታችን የምንማረው ብዙ ነገር እንዳለን አስባለሁ።ሆኖም ትናንትን የመዋቀሻና የመካሰሻ አጀንዳ አድርጎ የማቅረብ ሃሳቡም፤ ትልሙም ፤ ህልሙም የለኝም፡፡
ይህ ማለት ግን ትናንት ሁሉ በሁሉ ጥሩ ነበረና አትንኩት፤ አትውቀሱት ማለቴ አይደለም።ትውልድ በራሱ ሚዛን የሚወቅሰውም የሚያደንቀውም እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ጉዳታችንን አብዝተን መናገራችን ቁስልን እያከኩ ከማስፋት ያለፈ ፋይዳ ስለሌለው ነው።ወዲህም ደግሞ ትናንት በዘመኑ ልክ እንጂ በዘመናችን ልክ መመዘን የለበትም ፡፡ ዛሬ ዓለም በደረሰበት መለኪያ እንለካቸው ካልን ሁሉ ጨለማ ሁሉ ሀዘን ነው የሚሆነው።ስለዚህ መልካም መልካሙን እያዳበርን ካለፍንበት መንገድ እየተማርን መሄድ ነው፤ ያለብን፡፡
ወደኋላ ዘወር ብለን ያለፍንበትን መንገድ የምናየው ዛሬና ወደፊታችንን ለመስራት እንጂ ያንን አሁንም አሁንም አንስተን ለማቆሻበል አይደለም።እንድያውም እኛ ኢትዮጵያውያን፣ በደመ ነፍስ፣ እየተፍገመገምን ዕለት ዕለቱን እንዲሁ በማንረዳው ድንግዝግዝ ባለ ባልተጨበጠና እንደቦይ ውሃ በሚፈስስ ታሪክ ውስጥ ያለፍን ሕዝቦች አይደለንም።ይልቁንም ነባርና ጥንታዊ የታሪክ መስረታችን ዛሬ ካለንበት ሕይወት ለላቀ ማህበራዊና አጠቃላይ ዕድገት ሊያበቃን አቅም ያለውና የምንኮራበትም ነበር፤ ነውም፡፡
ታሪካዊና አኩሪ የማንነት መሠረት ካላቸው ጥቂት የምድሪቱ ሕዝቦች መሀል ተጠቃሽ መሆናችን እውነት ሆኖ ሳለ ይህን እውነት መቼም እና የትም በኩራት ብንናገረው ታሪክ ስንሰራም ይሁን የነበረውን ታሪክ ስናወሳ እንደመሠረት ብንጠቅሰው፣ እንደ መነሻ ብንጠቀመው ትክክል ነን፡፡ በእኔ በኩል ያለፍንበትን ታሪክ ማወቅ፣ ዛሬን ለማየት ወደፊቴን ከሕዝቤና ከሀገሬ ልጆች ጋር በበጎ ለማሰብ እንደ አንድ ብርቱ ትምህርት ቤት እወስደዋለሁ።ያለፍንበት የታሪክ ት/ቤት ደግሞ ሊጎበኝ ከሞላ ጎደል ዝርዝር ሁኔታው ሊጠናና ለትውልዱ የዕለት ከእለት የሆነ ዘላቂ ሕይወት እንዲሰጥ ያለውን በጎ ነገር መፈተሽ ተገቢም ወቅታዊም ነው፤ ብዬ አምናለሁ፡፡
ያባከንነውና በታሪክ ውስጥ ለቁጭት የሚዳርገንን ዛሬ እንዳንደግመው፣ ዛሬ ያጣነውንና በመረጃ እጦትም ይሁን በታሪካዊ መነሻ ዕጦት የባከንንበትን ጉዳይ ዕልባት እናገኝለት ዘንድ ታሪካችንን መቃኘት የግድ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል በምድሪቱ ላይ አለም አቀፍ ስምምነትን አግኝቶ ከደረጀ ዘመናት የተቆጠሩ ቢሆንም ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ በዘለቀው ያለፈው ፣ የፖለቲካ ሸፍጥና ሽር ምክንያት እየደበዘዘ እየደበዘዘ እንዲሄድ ተደርጓል።ከኢትዮጵያዊነት ታላቅ የአንድነት ግርማ ሞገስ ይልቅ በጎጥ ጎሳና መንደር ትውልዱ ጠብቦ እንዲያስብ፣ በዚህም የነበረ አንድነቱና ወገናዊ ትብብሩ እንዲላላ፣ ከማድረግ በከፋ ልዩነቱን የታከኩ የጠብና የመጠፋፋት ፖለቲካዊ ደባና ሸሮች ሆን ተብለው ተሰርተዋል፡፡
ይህንን ወቅት በመሻገር አገርና ሕዝባችንን ለተሻለ ሕይወት ማብቃት ካለብን ወደ ኋላ ተንደርድረን በብርቱ ኃይልና ፍጥነት ማለፍ ይኖርብናል።ይህ ወቅት ወይም የዚህ ወቅት አጠቃላይ ብሄራዊ ተግዳሮት ያለፉትን ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ የዘለቀውን የእኩልነት የሚመስል ደብተራዊ የፖለቲካ ሸርና ደባ ያስከተለውን ውጤት በጥንቃቄ እየነቀሱ ማውጣትም ግድ ይሆናል፡፡ መለያየትን፣ በመለያየትም የሰላም እጦትን፣ በሰላም ዕጦት ስጋትም፣ ዕድገት ይሁን የጤናማ ትውልድ ተከታታይና ዘላቂ ሕልውና ሊታሰብ አይቻልም።የዚያኑ ያህልም ለታላቅና ታሪካዊት አገር ማንነትም የማይመጥነው የወቅቱ የመለያያ፣ የመነታረኪያና በጠብ የስጋት መንፈስ የተጋረደው ጭጋግም ከአገሪቱ አየር ላይ መነሳት አለበት፡፡
በጎውን የምንመኘው የአንድነት መሠረት ስላለን ነው።የአንድነት መንፈስን ለማስቀደም የሚያበቃ የኋላ ታሪክ እንዳለን ሁሉ ይኸው የምንናገርለት አንድነት በሕዝቦች መከባበርና የጋራ ጥቅም እንዲፀና ለማትጋትና ለመትጋትም ነው፡፡ በታሪክ ውስጥ የተከሰቱ እንከኖች እየታረሙ ለዛሬና ለነገ ይበጀን ዘንድ ይጠቀሱ ይሆናል እንጂ ወቅትና ሁኔታ እየጠበቁ በማንሳት እያናቆሩ የአደጋ መንስኤ እንዲሆኑ መስራት ይጥለናል እንጂ አያነሳንም።ዘመኑ ለሚጠይቀው የላቀ ዕድገት ሲባል ዝግጅታችን ስህተታችንን ከማረም እንዲጀምር መትጋት ይገባል፡፡
በዛሬው ጊዜ አሉ የሚባሉ መልካም ነገሮች ሁሉ ከትላንቱ የወረስናቸው በጎነቶች ናቸውና በዚህም ለታሪካችን ክብር ይገባዋል።በዛሬው ጊዜ አሉ የሚባሉ ጉድለትና ችግሮቻችን ሁሉ ፣ ከትናንት ታሪካዊ መሠረትነት የተነሱ እንጂ እንዲሁ ከባዶ የተነሱ ፤ ድንገቴ ሆነው የተከሰቱ አይደሉምና ታሪካዊ ዕርማት ለማድረግም ነው፤ የኋላ ታሪካችንን የምንቃኘው።ይህ ብቻም አይደለም የወደፊቱን ዘመን በጎ ሕይወትና አንድነት “በማተለቅ መተለቅ” ፅንስ ሃሳብ መሠረት ለማቆምም ነው፡፡
ኢትዮጵያን ታህል ለረጅም ዘመናት ያልተቋረጠ መንግስታዊ ታሪክ ያላት፤ በታሪክና በባህል የደረጀች ሀገር፣ ከ3 ሺህ ዘመን በላይ በዘለቀ የታሪክ መንገዷ ላይ በበርካታ ውጣ ውረድ ውስጥ ማለፏ የሚጠበቅ እውነት ነው።የአስተዳደር ስርዓቷ እንደየጊዜውና ወቅቱ ሁሉ በሕዝቦችም ደምና አጥንት እየተገነባ፣ ወጣ ውረድዋ ከሕዝቦችዋ ሕይወትና ማንነት ውጭ የማትታሰብ ሃገር እንደሆነች ሁሉ፣ የዚህችው ሀገር ሕዝቦችም በየዘመናቱ የሚጣመሩ የሚዋለዱና አንድ የሆኑ ናቸው።በመሃከላቸው ልዩነትን መፈለግ በአገሪቱ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ለደባና የሸር አላማ ካልሆነ በቀር አንዳች አገራዊ ጠቀሜታ፣ አንዳችም ሕዝባዊ ትርፍ አልነበረውም።ኪሳራው ግን ግልፅ ነበር።
በዛሬው ዘመን እንደመንገስ የሚቃጣው የመለያየትና የጎሳ ፖለቲካ፣ ለጥቂት ነጋዴዎች ትርፍ የሚያመጣውን ያህል ለሀገርና ብዙሃን ሕዝብ ያው የተለመደውን ጥፋትና ኪሳራ አከናንቦ ዘወር የሚል ነው።ለቀጣዩ ትውልድ አንዳች በጎ ኃላፊነት የማያወርሰው ይኸው የመለያየትና የጠብ መነሻ የሆነ የዘር ፖለቲካ፣ ዛሬ በአገርና በሕዝቦች ኪሳራ ነጋዴዎችን አበልፅጎ ብቻ የሚያከትም ያንድ ወቅት አገራዊ በሽታ ብቻ አይደለም።
ይልቁንም ስሩን መስደድ የሚወድ ነገን በማበላሸት ስትራቴጂ በዛሬ ትርፍ ላይ የሚንደረደር፣ የሕዝቦች ንቃት እውን እንዳይሆን የማደናቆሪያ ስልቱን በውሸት፣ በመለያየት በቂምና ቁርሾ ላይ ብቻ መስርቶ የሚያዋክብ ኃይል ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም በላይ አይናቸውን ገልጠው በባህል፣ በእምነት ፣ በእርስ በርስ ጋብቻና በዘመናት የአብሮ መኖር ቆይታ ውስጥ አንድ ለመሆን ከመተባበራቸው እንጂ ለጠብ በሚያበቃ ልዩነት እንደማያተርፉ ማስታወስ አለባቸው።
ኢትዮጵያዊያን ለአንድነትና ለሕብረት ይመቻቸው ዘንድ አንድ ያደረጋቸውን ኢትዮጵያዊ የኋላ ታሪክ ማስታወስ አለባቸው።በታሪክ ውጣ ውረዱ ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮች፣ ግጭቶች በውጊያና ጦርነት የደረሱ ጥፋቶች በዚህ ዘመን ሂሳብ ይሰራላቸው ትርፍና ኪሳራውም ተሰልቶ ሂሳቡን ያወራረዱ የሚሉ የፖለቲካ ልሂቃንና ነጋዴዎች በግልፅ እያተረፉ ያሉት ልዩነትን በማስፋት ያንዱ ወገን ጠበቃ መስለው በመታየትና በማስመሰል ነው።እነዚህ የአፍራሽ መንፈስ ልሒቃን የቆምንለት በሚሉት ህዝብና በእነርሱ መካከል ያለውን ልዩነት በቀላሉ ለመገንዘብ ውሎና አዳራቸውን መቃኘት ብቻ ይበቃል፡፡ የአሜሪካን የእርስ በእርስ ጦርነት (1861-65 ዓም.) ሁነት ላይ ተመስርቶ “Gone with the wind “በሚል ርዕስ ተጽፎ በነብይ መኮንን፣ “ነገም ሌላ ቀን ነው፣” ተብሎ በተተረጎመው መጽሐፍ ላይ ካሉት ገጸ ባህሪያት አንዱ፣ “ሚስተር ሬት በትለር” የተባለ ባለታሪክ ነው።በትለር፣ ጦርነቱ እየተካሄደ እያለ ከምንም ወደ አስደናቂ ባለሀብትነት የተሸጋገረ ሰው ሲሆን አንደኛው ገጸባህሪ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል።“ጎበዝ ጦርነቱ እያበቃ እኮ ነው” ፤ሲለው ፣በትለር ተደናግጦ፣ “እንዴትና ለምን?” ሲል ደግሞ ይጠይቀዋል። የበትለር አነጋገር አንድምታ ግልጽ ነው፤ “ጦርነቱ ካበቃ እኮ የምንሸጠው መሳሪያ ሊያበቃ ነው፤ እንግዲህ ጦርነቱ ሲያበቃ ሽያጩ ምን ሊሆን ነው፤” የሚል ነው፡፡ እርሱ ለሰሜኖቹ ፌዴራሊስቶችም ሆነ ለኮንፌ ዴራሊስቶቹ ደቡባውያን መሳሪያውን ይሸጥ የነበረ ሰው ነውና።
ያሳሰበው በንግዱ የሚያተርፈው ገንዘብ እንጂ በጥይቶቹ የሚፈስሰው ደም አልነበረም። አሁንም በእኛ ሐገር ያሉ በትለሮች፣ የሚያሳስባቸው፣ ዋናው ነገር ዓላማ ብለው የሚያላዝኑበት ጉዳይ አይደለም ፤ እኛ ሁሉን ነገር ካልተቆጣጠርነው፣ ሁሉም ነገር በእኛ መሪነት ስር ካልሆነ ሁሉም ነገር ገደል ይግባ ከሚል ስሜት የተነሳ ነው።አሳዛኙ ነገር የሚገዙት ህዝብ የሌለበት ሐገር ምን ያደርግላቸዋል እንዳንል ሌላ ህዝብ ተከራይተን እናሰፍርበታለን፤ ከማለት የማይመለሱ ሐገርን ከኪራይ ቤት አሳንሰው የሚያዩ ግብዞች መሆናቸው ነው፡፡
ትርፍና ኪሳራው ሲሰላ ሂሳቡ የሚወራረደውም በሕዝቦች ተጨማሪ ደም፣ እልቂትና ያልተገባ ረብሻ ሳቢያ መሆኑን አለም እስኪታዘበን ድረስ ያየነው መሆኑንም ያለፍንበት እውነታ ምስክር ነው።ምንጊዜም ቢሆን ያለፍንበት የኋላ ታሪክ ለዛሬና ለነገ ሕይወት እስካልበጀ ድረስ በተቃራኒው ለጥፋትና መለያየት ብቻ እንደመሳሪያ የሚነሳ ከሆነ ይህ ጤናማ ያልሆነ መንፈስ ሊነቃበት ይገባል። በሃገራችን የረጅም ዘመን ታሪክ መንግስት ይቀያየራል።መንግስታት የሚመሩት ሕዝብም በዚያው መጠን ይዋሃዳል።
ኢትዮጵያዊያንን በቋንቋና ቀለም ሳቢያ “እንዲህ ነህ” ብለን ለመለየት የምንቸገርበት ብዙ ስፍራ አለን።ዛሬ አንዱ ክልል የዚያው በሆነ የጎሳ ስም ሲጠራ እናም ያ የዚያ ጎሳ ክልል ነው፤ ሲባል እንሰማለን።ይሁንና በዚያ ክልል “ክልል” ይሉት የመለያያ ቋንቋ ከመቋቋሙ በፊት ለዘመናት የኖረና የተዋሐደው ኢትዮጵያዊ ሕዝብስ? ከ4ቱም አቅጣጫና ማዕዘን መጥቶ “ሸዋ” ላይ ሰፍሮልሃል።ተዋልዷል።ቤተሰብን መስርቶ እስከቅድመ ቅምቅም አያቱ የሚቆጥረው የተሳሰረ ዝምድና መስርቷል።ይህን ህዝብ ምን ስምና ወገን እንሰጠዋለን ? ምን የጎሳ መደብ፣ ከየትኛው የጎጥና የመንደር ማንነት ጋር እናዳብለዋለን? ከዚህ ለአገርና ለትውልድ ምንም ረብ በሌለው መለያየት ሰዎቹ ትርፋማ የመሆናቸውን ያህል፣ ለዚሁ አላማ የሚተባበራቸው ትውልድ መገኘቱም የበለጠ አስገራሚም አስፈሪም ነው።
መለያየት ውጤቱም ጥፋት የሆነውን የኋላውን ክፋት ጠባሳ እያነካኩ ከዚሁ ጥፋትና ኪሳራ ትርፍ የሚያጋብሱትን የፖለቲካ ነጋዴዎችም አገሬ በክብርና በክብካቤ መያዟ ለእኔ የዘመኑ ገራሚ ኮሜዲ ነው።ኮሜዲውም በጥፋት የተሞላ የግብዞች ድራማ እንደሆነም ነው ፤ የማስበው፡፡ እዚህ ላይ ከአበው ይትበሃሎች የዝሆንና ድርጭቷን ጉዳይ አነሳለሁ።ድርጭቱ ጎጆ ሰርታ እንቁላል ጥላ በዚያው ጎጆዋ ዙሪያ እየዘመረችና ሰላሟን እያጣጣመች ሳለ በዚያው ስፍራ ውሃ ለመጠጣት የሚመላለስ ዝሆን እንደዋዛ ጎጆዋን ረግጦ እንቁላልዋን ሰባብሮ ሃዘን ላይ ይጥላታል፡፡
እሷም ከዚህ ሃዘንና መከራ የተነሳ አለቀሰች፤ አልቀሳ አልቀረችም።ዝሆንን ሄዳ ጠየቀችው።“ብርቱው ሆይ፣ እኔ አንተን ተጠግቼ እየኖርኩ ስለምን እንቁላሌን ሰብረህ ሃዘን ላይ ትጥለኛለህ? ይህ እንደዋዛ የሰራኸው ስራ የእኔን አቅም አሳንሰህ፣ የኔን ጉዳይ አቃልለህ፣ እና እኔንም በመናቅ ነውን?” አለችው፡፡ ዝሆኑም “እውነት ነው፤ ነገሩ ሁሉ ልክ አንቺ እንዳልሽው ነው” ሲል በሀዘንዋ ላይ ሃዘን እንዲበዛ ተዛበተባት።ተነስታም ወደ ወፎች ሰራዊት ሄደች።ዝሆን ከታላቅ ትዕቢቱ የተነሳ እንቁላልዋን ሰብሮ ጎጆዋን ደምስሶ ሲያበቃ ምንም አታመጣም፣ በሚል የሰጣትን የንቀት ምላሽም ነገረቻቸው፡፡ እነሱም “ወፎች ነን” ምን እናድርገው ብለሽ ነገርሽን” አሏት።እሷም ፈራ ተባ እያለች በእልህም ጭምር ጭልፋቶችንና ቀሪዎችን “ከእኔ ጋር ሄዳችሁ አይኑን ብትነቁሩልኝ እንድየው ጥፋት ይባልብኝ ይሆን?” አለቻቸው።“የምን ጥፋት” አሉ ቁራና ጭልፊቶች “ዋጋውን ከፈልሽው ነው የሚባልልሽ” ብለው የዝሆኑን አይን ጓጉጠው አጠፉት፡፡ ታላቁ ዝሆን፣ ከዚያ በኋላ ምግብና መጠጡን ለማግኘት አሳዛኝ ድካምና እንግልት ቢገጥመውም ድርጭቱ በዚህ ብቻ ልትፋታው አልወደደችም።
ወደ እንቁራሪቶች ጉባኤ ሄዳ “ከዕብሪቱና ከኃይሉ የተነሳ የተበተብኝን ዝሆን ጉድጓድ ውስጥ መክተት ፈልጋለሁ” አለቻቸው፡፡ “ምን እንርዳሽ ታዲያ?” “ከእኔ ጋር ኑና፤ በጉድጓዱ ዙሪያ ከፍ አድርጋችሁ ጩኸት አሰሙ።ያኔ ውሃ ያገኘ መስሎት ሲመጣ ወደ ጉድጓድ ይወድቃል።ከእነ ትዕቢቱና ጥፋቱም ይቀበራል” አለቻቸው። በእርግጥም ዝሆን የእንቁራሪቶቹን ጩኸት በሰማ ጊዜ እንደተለመደው ውሃ ያገኘ መስሎት ከማይቀርለት ጉድጓድ ወደቀ።በእርግጥም ጥፋትን የሚዘራ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ያንኑ ጥፋት ማጨዱ አይቀርም።በሰዎች የግንዛቤ አናሳነት ላይ ከቶውንም አትተብት፤ የሚጠብቅህ የዝሆኑ ፍፃሜ ነውና ፡፡
በንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የትምህርት ጅማሮ ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከእናታቸው ጓዳ የበለጠ ክብካቤ የሚያገኙበት፣ በራሳቸው በንጉሱ እየተጎበኙ እንደገዛ ልጆቻቸው ፍራፍሬና ጣፋጭ ብስኩት የሚቀበሉበት፣ እንደ አንድ ቤተሰብ ሁሉ ቤተሰባዊ ፍቅርና ሰላም የሚነግስበት ተቋም እንደምን ወደ ተራ የእርስ በእርስ የግጭት ማዕከልነት ወረደ? ለተማሪዎች ምቾት ሲባል እንደ ንጉሱ ዘመን ያለ ክብካቤ ቢያጣውም እንደምን በተራ የመንደርተኝነትና የጎሳ ስሜት ሳቢያ የሰው ልጅ ሕይወት ለሞት በቀላሉ የሚጋለጥበት የሲኦል ቀጠና እንዴት ሊሆን በቃ፤ ብለን መጠየቅ የተገባ ነው፡፡
ይህን ለመሰለ ለብሄራዊ ውድቀት ከሚዳርገን በሽታ መፈወስ የለብንም ወይ? መፈወስስ ካለብን በሽታችንን አንናገረውም ወይ? የዚህኑ በሽታ ስር መሠረትና ምንጭ ለማወቅስ ከብዙ የጊዜና የገንዘብ ብክነት ይልቅ ዘወር ብለን ባለፍንበት መንገድ የተዘራውን ዘር ማየት አይገባንም ወይ? ዛሬ የሚታየው አዝመራስ የዚያ ዘር ውጤት አይደለም ወይ? አሁን ደግሞ በገጠመን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ጾታና እድሜ የማይገድበው ክፉ በሽታ ዙሪያ አንድ ነገር ልበል።ህመሙ፣ ወረርሽኙ በምንም መንገድ ካገኘን ማናችንንም የማይምር፣ ሰው መሆናችን ብቻ በቂው የሆነ መቅሰፍት ነው።
ታላላቆቹን እየገነደሰ ከንፋስ በፈጠነ ፍጥነት ዓለምን ሁሉ አዳርሶና የሚያጭደውን አጫጭዶ አፍሪካን እየዳበሳት ይገኛል።ውድ ወንድሞቼ ወገኖቼ ፣ ይህ መቅሰፍት ቋንቋ የለውም ስም ብቻ ነው፤ ይህ መቅሰፍት ብሔር የለውም መነሻ ስፍራ ነው፤ ይህ መቅሰፍት ጂኦግራፊ የለውም ምድርና ሞላዋን ነው።ስለዚህ መከላከል የምንችለው እንደ ሰው ቆመን እንጂ እንደትውልዳችን አማራ፣ ኦሮሞ፣ ቻይናዊም ሆነ አሜሪካዊ፣ ሲዳማም ሆነ ወላይታ አይቶን አይደለም ፤ እንደ ሰው ብቻ ነው።
ቫይረሱም ያሳየንና አብዝቶ በአውሮፓና አሜሪካ፣ ሰብዓዊ ከተፋውን የቀጠለው በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ነው።ስለዚህ እንደ ሰውና እንደ ሐገር ቆመን እንፋለመው፤ በዚህ ሰዓት እየመጡ የፖለቲካ አጀንዳቸውን በወረርሽኙ ውስጥ ለመሸጎጥ የሚፈልጉ ክፉዎች ካሉ የተወገዙ ናቸው፡፡ ሐገሬ፣ አሁን እግዚኦታ ላይ ነች።ሐገሬ አሁን አምላኳ ተማጽኖዋን እንዲሰማ በእንባ እና በልመና ላይ ነች፤ ይህንን እንባዋን አድርቅ የሆናችሁ “የክፉ ቀን ክፉዎች”፤ እባካችሁ ከክፋታችሁ ታቀቡና በመከላከል ዘመቻና እግዚኦታው ላይ ተሳተፉ።እግዚአብሄር የፈቃድ አምላክ ነውና ፈቃድ አጥታችሁ፣ የአምላክም ልጆች ካልሆናችሁ “በምክንያታዊነት አምልኳችሁ ይዣችኋለሁ፤ እስቲ ይኼ ክፉ ቀን እስኪያልፍ ዝ….ም፣ በሉ!! ይኼ ቀን ሲያልፍ ወደ ወደ ነገራችሁ ትመለሳላችሁ….ሰው ሲኖር ነው፤ ፖለቲካም የሚኖረው፤ ሐገር ስትኖር ነው፤ የአገዛዝ ስልት የሚፈጠረው።ቤተክርስቲያንንና መስጊድን ያስጠረቀመ ወረርሽን በምን እንደሚያቆም መገመት አይቻልምና፣ አስቡበት።ስለዚህ በእውነት ለህዝብና ለሐገር የምታስቡ ከሆነ በዚህ ወቅት ዝም በሉ፤ ኮሮናን በጋራ እንከላከል!! ያለፍንበት መንገድ፣ ምንም ይሁን ምን፣ አሁን ከምናልፍበት መቅሰፍት አይብስብንም፤ ነገ ቆመን ልናወራ የምንችልበት ዕድል ሁሉ ላይኖረን እንደሚችል አስበን በፍቅር እንተሳሰብ ፤ ይሰማል ?
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
ያለፍንበት መንገድ