በስፖርቱ ዓለም በተለይም በእግር ኳስና አትሌቲክስ ብዙም የማትታወቀው ህንድ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተለያዩ የአትሌቲክስ የጎዳና ላይ ውድድሮችን እያስተናገደች ትገኛለች። በዚህም በመዲናዋ በየዓመቱ ከምታዘጋጀው የዴልሂ ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድር አንስቶ በሌሎች የጎዳና ላይ ውድድሮችም ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ደረጃ የተሰጣቸው ፉክክሮችን ለማስተናገድ ችላለች። የፊታችን እሁድም የነሐስ ደረጃ የተሰጠውን የካልካታ ሃያ አምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ታካሂዳለች።
በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአሸናፊነት ግምት ያገኙ ሲሆን፤ በተለይም በሴቶች መካከል በሚካሄደው ውድድር የአምናዋ አሸናፊ አትሌት ደጊቱ አዝመራው ዳግም ለአሸናፊነት ታጭታለች። ባለፈው ዓመት ይህች የአስራ ስምንት ዓመት ኢትዮጵያዊት አትሌት በመጀመሪያ ዓለም አቀፍ ውድድሯ የቦታውን ክብረወሰን 1፡26፡01 በሆነ ሰዓት በማሻሻል ጭምር አሸንፋ በርካቶችን እንዳስደ መመች አይ ኤኤ ኤፍ በድረ ገፁ አስፍሮታል።
አትሌት ደጊቱ በ2018 የውድድር ዓመት በጎዳና ላይ ሌሎች ውድድሮችን አድርጋም ውጤታማ ነበረች። ባለፈው የካቲት ወር በራክ ግማሽ ማራቶን ተወዳድራ የራሷን ምርጥ ሰዓት ወደ 1፡06፡47 አውርዳለች። ከዚህም በኋላ በጃፓን ጊፉ ግማሽ ማራቶን ማሸነፍ ችላለች። ይህም በዘንድሮው ውድድር ለአሸናፊነት እንድትጠበቅ አድርጓታል። ይሁን እንጂ ከኬንያዊቷ ጠንካራ አትሌት ፍሎሬንስ ኪፕላጋት የሚገጥማት ፈተና ቀላል እንደ ማይሆን ይታመናል።
እኤአ 2009 ላይ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና እንዲሁም 2010 ላይ በዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማጥለቅ የቻለችው ኪፕላጋት በጎዳና ላይ ውድድሮች በርካታ ልምዶችን ከማካበቷ ባሻገር የቀድሞ የዓለም የግማሽ ማራቶን ባለ ክብረወሰን እንደነበረች ይታወሳል። ኪፕላጋት አሁን ሰላሳ አንደኛ ዓመቷ ላይ የምትገኝ ቢሆንም፤ ከወጣቷ ኢትዮጵያዊት ጋር ለመፎካከርና አሸናፊ ለመሆን የተሻለ እንጂ ያነሰ እድል የላትም።
ኪፕላጋት ባለፈው ዓመት በዚሁ በካልካታ ሃያ አምስት ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ ትሳተፋለች ተብሎ ቢጠበቅም ቀደም ብሎ ቺካጎ ማራቶን ላይ በገጠማት ጉዳት ሳቢያ ለውድድሩ ብቁ ሆና መገኘት አልቻለችም። ዘንድሮ ግን ያለፈውንም ቁጭቷን ለመወጣት ወደ ህንዷ የኢንዱስትሪ ከተማ እንደምታቀና ታውቋል። በእርግጥ ኪፕላጋት ከዚሁ ከጉዳት ጋር በተያያዘ ከወር በፊት በቺካጎ ማራቶን አራተኛ ደረጃን ይዛ እስካጠናቀቀችበት ውድድር ለዓመት ያህል ከፉክክር ርቃ ቆይታለች። ኪፕላጋት በካልካታ ውድድር ላይ ስትሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያዋ ቢሆንም ህንድ አገር በሚካሄዱ ውድድሮች እንግዳ አይደለችም። ከዚህ ቀደም በዴልሂ ግማሽ ማራቶን ሁለት ጊዜ ማሸነፏ ይታወሳል። በውድድሩ ሱቱሜ አሰፋ የተባለች ኢትዮጵያ ዊት እንዲሁም ፌሉና ማታንጋ የተባለች ታንዛኒያዊት አትሌት ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ ውድድር በወንዶች መካከል የቦታው ብቻም ሳይሆን በህንድ አገር ከተሮጡ ፈጣን ሰዓቶች ሁሉ ክብረወሰን ሊሆን የሚችል ሰዓት ይመዘገባል ተብሎ ይጠበቃል። የቦታው ክብረወሰን ባለፈው ዓመት በጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 1፡13፡48 ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። ያለፈው ዓመት ውድድር ቀነኒሳን ጨምሮ በሴቶችም ውድድር ጠንካራና ስመ ጥር አትሌቶች ሲሳተፉ የመጀመሪያው እንደነበር ይታወቃል።
ዘንድሮ በወንዶች መካከል በሚካሄደው ውድድር ለህንድ አትሌቲክስ አፍቃሪዎች አዲስ ያልሆነው ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ለገሰ ለአሸናፊነት ይጠበቃል። ብርሃኑ ሁለት ጊዜ በዴልሂ ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮን ከመሆኑ ባሻገር በባንግሎር አስር ኪሎ ሜትርና ሌሎች ውድድሮች ላይ በመሳተፍ በህንድ ታዋቂ ነው።
ብርሃኑ በውድድሩ ከኬንያዊው ኤሪክ ኪፕቱናይ ብርቱ ፉክክር የሚጠብቀው ሲሆን፤ የኤርትራ፣ ታንዛኒያ እንዲሁም ሌሎች የኢትዮጵያና ኬንያ አትሌቶች ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተለይም ኬንያዊው ኪፕቱናይ በ2018 የውድድር ዓመት ባለፈው የበርሊን ግማሽ ማራቶን ያሰመዘገበው 58፡42 ሰዓት በውድድር ዓመቱ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት መሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል። የታንዛኒያ ባለክብረወሰን ኦገስቲኖ ሱሌ ባለፈው ዓመት በዚህ ውድድር ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ኢትዮጵያውያን በካልካታ ለድል ይጠበቃሉ