በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ሰሞኑን ወደ አሜሪካን በማቅናት በወቅታዊ ክልላዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያውያንና ከክልሉ ተወላጆች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በሰሜን አሜሪካን – ዋሽንግተን ዲሲ የተጀመረው ይህ ውይይት ገንቢ ሃሳቦች የተንጸባረቁበትና የጋራ መግባባትም የታየበት ነው፡፡ በዛሬው ጽሁፋችን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረጉትን ውይይት እንደሚከ ተለው አቅርበነዋል፡፡
የውይይቱ አላማና የመክፈቻ ንግግር
የውይይቱ ዓላማ የተጀመረውን የለውጥና የመነሳሳት መንፈስ ከቃላት በዘለለ ወደ ተግባር ለማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከር ነው፡፡ አቶ ገዱ በመክፈቻ ንግግራቸው በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለረጅም ጊዜ ተፈጥሮ የቆየው ፊት የመዟዟር መንፈስ ተወግዶ በጥላቻ ከመተያየት ይልቅ ወደ መቀራረብ፣ ፍቅርና ይቅር ባይነት በመምጣትና እጅ ለእጅ በመያያዝ የለውጡን ህልውና ማስቀጠል ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡ ‹‹እዚህ የምትኖሩ ወገኖቻችን ፊት ዛሬ እንዲህ በድፍረት እንድንቆም ያደረገን በመካከላችን መፈጠር የጀመረው የሃሳብ አንድነትና መቀራረብ ነው፡፡ በአገራችን አዲስ የለውጥ ማዕበል ተቀስቅሶ በአጭር ጊዜ የማይጠበቅ ውጤት እየተመዘገበ ነው›› ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ድረስ የተነፈጋቸውን ይህን የነጻነት መንፈስና የተፈጠረ ውን የፖለቲካ ምህዳር በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
ዜጎቻችን የመሰላቸውን ሃሳብ የመያዝ ፣ በመሰላቸው አግባብ የመግለጽና የመደራጀት መብቶቻቸውን በተግባር በመጠቀም ከሥጋትና ከፍርሃት ቆፈን ተላቀዋል፤የየድርሻቸውን ለመወጣ ትም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቁርጠኛ አቋም ይዘው መጓዝ ጀምረዋል ሲሉም አመልክተዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ በአገሩ ጉዳይ የማይደራደር ቀናኢ ህዝብ ከመሆኑም ባሻገር ከሌሎች ወንድምና እህቶቹ ጋር ተባብሮ ተቻችሎና በባህል ፣ በሃይማኖትና በኢኮኖሚ ተሳስሮ የመኖር አኩሪ እሴት የገነባ ለአብሮነት መኖር የሚመች ህዝብ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ህዝብ ይህንን መሰል እሴት የገነባ ቢሆንም በሀገራችን ለረጅም ጊዜ ሲሰበክ የኖረው የጥላቻ ፖለቲካ በብዙ መልኩ ሲያጎሳቁለው መኖሩ የማይካድ ነው ሲሉ አቶ ገዱ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም አሁን በአገራችን ህዝቦች ትግል የተገኘው የለውጥ ተስፋ ብዙ ፈተናዎች ያሉበት ቢሆንም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአገራችን ለማስፈን እጅግ የተመቸ ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
አቶ ገዱ እንዳሉት፤ ዛሬ በአማራ ክልልም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ የድል ብሥራት ጮራ መፈንጠቅ ጀምሯል፡፡ አንድ ሆነን ከተንቀሳቀስን ብርሃኑ ከእኛ አልፎ ለሌሎችም ይተርፋል፡፡ የጀመርነው የድል ጉዞ ዳር እንዳይደርስ አንድነታችን እንዲላላና አሸናፊነት እንዲርቀን የሚያደርጉ ፈተናዎችን ለማስወገድ መረባረብ አለብን፡፡ ወቅቱ ትልልቅ ፈተናዎችን ለማለፍ ትንንሽ ልዩነቶችን ወደጎን የምንተውበት ነው፡፡
ችግሮቻችን እንደ ጊዜው እርዝማኔ የተከመሩ በመሆናቸው በተባበረ ክንድ ካልሆነ በቀር ልንፈታቸው አንችልም፡፡ የአማራ ህዝብ ካለፉት ሥርዓቶች የተለየ ጥቅም ያገኘ በማስመሰል እንደ ጨቋኝ፤ ለፍትህና ለዕኩልነት መስዋዕት ሲከፍል የኖረ ህዝብ ሆኖ ሳለ እንደ አፋኝ ተደርጎ ሲዘራ የኖረው የጥላቻ ዘር አበሳውን ሲያበዛበት ኖሯል፡፡ ዛሬ ግን ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመተባበር ባደረገው ትግል የለውጥ ብርሃንን ማየት ችሏል፡፡ ተነጣጥሎ መጓዝ በየምዕራፉ ተንጠባጥቦ መቅረትን ያስከትላል፤ እናም የአማራ ህዝብ እርስ በርሱና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር አንድ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጥያቄዎች
የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ክልሉን እያስተዳደረ ሳለ በርካታ ቁጥር ያላቸው የክልሉ ነዋሪዎች እየታፈኑ ተወስደዋል እስከ አሁን ይኑሩ ይሙቱ አይታወቅም በዚህ ጉዳይ ምላሻችሁ ምንድነው ? አዴፓና ኦዴፓ ያላቸው መተባበር እስከምን ድረስ ነው? በፌዴራል መንግሥት ያለው የስልጣን ክፍፍል የተመጣጠነ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? መጪውን ትውልድ በጥሩ ሥነ- ምግባር ከመቅረጽ አንጻር ለጫትና ለመሰል ሱሶች እንዳይጋለጥ ምን እየሠራችሁ ነው? ስለአዲስ አበባ ከተማ ባለቤትነትስ ምን ትላላችሁ? ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም ወይ? የአማራ ክልል ህዝቦች እያሰሙ ያሉትን የወሰንና የማንነት ይከበርልን ጥያቄ አዴፓ እንዴት ይመለከተዋል? ለውጡን በሁለት እግሩ ለማቆም ከእኛ ምን ትጠብቃላችሁ? የሚሉት በዋሽንግተን ዲሲ ከተነሱት ጥያቄዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላትም ተራ በተራ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የለውጡ ሂደት
ምላሽና ማብራሪያ መስጠት የጀመሩት ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ ‹‹ይህን ድርጅት ስንቀላቀል ሥርዓቱ፣ሀገርና ወገንን ለማገልገል ያስችለናል ብለን በማሰብ ነበር። ነገር ግን የፖለቲካው ዕድገት ወደ አፈና እና ወደ ሙስና እየተሸጋገረ ሲመጣ ከውስጥም ከውጭም ትግሉ እየተፋፋመ መጥቶ ለዛሬው ድል ደርሰናል፡፡ ትግሉን አስቸጋሪ ያደረገውም በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ሆነን አንዱ በእውነት ሌላው በአድርባይነት በመሰለፋችን ነው›› ብለዋል፡፡
ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት እጅግ ፈታኝ የነበሩ የጭቅጭቅና የንትርክ መድረኮችን ነበር ያሳለፍነው ያሉት ዶክተር አምባቸው፣ይህም በድል የተጠናቀቀው ዶክተር አብይን የኢህአዴግ ሊቀመንበር አድርገን የመረጥነው ዕለት ነው ብለዋል፡፤ በለውጡ ነጻ የወጡት የኢህአዴግም አመራሮች ጭምር በመሆናቸው ድርጅታቸው አሁን ህዝብን ማገልገል ወደሚችልበት ደረጃ እንደተሸጋገረና ከሌሎች ተጽዕኖዎችም ነጻ እንደወጣ አስረድተዋል፡፡
የክልላችን ሕዝቦች ስለመልካም አስተዳደርና ስለፍትህ ሲሉ በተለያየ ጊዜ ጥያቄ አቅርበዋል፤ ሥርዓቱን ተቃውመዋል፤ አምጸዋል፤ መንግሥት የህዝቦችን ጥያቄ ባልሆነ መንገድ ለመመለስ ኃይል ተጠቅሞ ብዙዎች ተንገላተዋል፣ ተገርፈዋል ፣ቆስለዋል ፣ አካላቸውን አጥተዋል ፤ሞተዋል ፤ አንዳንዶቹም ታፍነው ተወስደው እስከ አሁን የት እንዳሉ እንኳን አይታወቅም ያሉት ዶክተር አምባቸው፣ እንደ አመራር እኛም ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂዎች ነን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ይህ ለውጥ ከሀገር ውጭ ያሉ ዜጎችም በመሰላቸው ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የታገሉለት እንደመሆኑ ድሉ የሁላችንም ውጤት ነው፡፡ ለውጡ ዛሬ በህዝብ እጅ ስለገባ ከማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ቢሆንም ትናንት ሊያደናቅፉ የሞከሩ ዛሬም የሚያሴሩ ፀረ-ለውጥ ኃይሎች እንዳሉ መረሳት የለበትም ሲሉም ዶክተር አምባቸው አሳስበዋል፡፡
በብሄር መደራጀትና ፌዴራሊዝም
ሌላው የሉኡካን ቡድኑ አባል የሆኑት አቶ ምግባሩ ከበደ፣ በበኩላቸው፣ በብሄር መደራጀትና ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ተጽዕኖ አያሳድሩም ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም አንዳንዶቻችሁ ኢትዮጵያዊነታ ችሁን ፤ አንዳንዶቻችሁ ደግሞ አማራነታችሁን ትቀበላላችሁ ፡፡ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ውብ አማራነትስ እንዳለ አስባችሁ ታውቃላችሁ? አማራ ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር የከፈለውን ዋጋ ቆጥረን አንጨርሰውም ግን ብቻውን አይደለም፡፡ ከሌሎች ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር ተባብሮ ነው፡፡
አንዱ ተደራጅቶ ፤ ትንፋሽ ሰብስቦ በሚጫወ ትበት ኳስ ሜዳ ውስጥ ሌላው ደግሞ እኔ አንድነት እስኪመጣ መደራጀት አያስፈልገኝም ቢል ሜዳው እኩል ተወዳዳሪ ያልሆኑ ሰዎች የሚሰለፉበት ይሆንና የማሸነፍ ሚዛኑ ወደ አንዱ ያደላል፡፡ ወይም ደግሞ በፎርፌ መሸነፍ ይመጣል፡፡ ስለዚህ ይህንን ችግር ለማስወገድ ነው የብሔር መደራጀት ያስፈለገው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
‹‹የምንደራጀው ማንንም ለመጉዳት አይደለም፡፡ ይልቁንም እንደኛው ተደራጅተው ለዕኩልነትና ለሰላም ከሚታገሉ ወንድሞቻችን ጎን ቆመን ሌላ ክንድ ለመሆን ነው፡፡ የአማራው ሕዝብ ዕውቀትና ጥበብ ከሌላው ሕዝብ ዕውቀትና ጥበብ ጋር ሲደመር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል አቅም ይፈጠራል፡፡ ይህ ህዝብ ካልተደራጀና በተናጠል የሚሄድ ከሆነ ችግሮችን የመቋቋምና ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም አይኖረውም፡፡ ስለሆነም አዴፓ ስለመደራጀት ሲያወራ ሕብረ ብሔራዊነትን ወይም ኢትዮጵያ ዊነትን ሊያሳካ ከሚችልበት ግቡ ጋር አያይዞ ነው›› በማለት አብራርተዋል፡፡
አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው የኩርድ ህዝብ በቁጥር ከሰላሳ ሚሊዮን በላይ ነው፡፡ ነገር ግን በአምስት የተለያዩ ሀገሮች ተበታትኖ ስለሚኖር አንድ ሆኖ ድምጹን ማሰማት እንዳይችልና እንዳይታገል ሆኗል፡፡ ይህ ሁኔታ እኛም ላይ እንዳይመጣ ከወዲሁ ጥብቅ ትስስርና አንድነት ሊኖረን ይገባል ሲሉ የመደራጀቱን አስፈላጊነት አስረድተዋል፡፡ አስከትለውም የአማራ ህዝብ አንድ ባለመሆኑ ምክንያት ዛሬ እየጠቀስናቸው ላሉት ችግሮች ተጋልጧል፡፡ አንድነት መተሳሰብን፣ መረዳዳትን ፣መቻቻልን፤ መደማመጥን፣ ባለ ራዕይነትንና ስልጣኔንም ያጎናጽፋል በማለትም አብራርተዋል፡፡
አዴፓና ኦዴፓ
‹‹አዴፓና ኦዴፓ ለለውጡ መምጣት በጋራ ሆናችሁ እንደሠራችሁ ይታወቃል፡፡ በፌዴራል ደረጃ የስልጣን ክፍፍሉ ወደ ኦዴፓ ያመዘነ የመስላል፡፡ እንዴት ነበር ሥምምነታችሁ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ገዱ እንዲህ በማለት መልሰዋል፡፡የተስማማነው ስልጣንን እንዴት እንከፋፈላለን በሚል ሳይሆን የመጀመሪያው እርምጃችን ሁለቱን ሕዝቦች ለማራራቅ የተዘራውን መርዝ በማስወገድ እንዴት ማቀራረብ እንችላለን በሚል ነው፡፡ ምናልባትም በደንብ ቢጠና ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነዚህ ሁለት ህዝቦች የተጋባና የተቀላቀለ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ እናም በባህል፣ በታሪክ ፣ በደም፣ በቋንቋና በመልክዓ ምድር የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ትልቁ ግባችን በተዛባም ይሁን በእውነተኛ ታሪክ ላይ በመንጠልጠል በእነዚህ ህዝቦች መካከል የነበረው መልካም ግንኙነት እንዲሻክር በመደረጉ ይህንን አፍርሰን ሁለቱን ህዝቦች አንድ ማድረግ ነበር፡፡
ጣናን መታደግ
ጣናንና አባይና ከመታደግ አንጻር ለተነሳው ጥያቄም አቶ ገዱ ሲያብራሩ ፣ ጣናን ከአደጋ ለመታደግ በዋናነት እየሠራ ያለው አርሶ አደሩ እንደሆነ ገልጸው፣ ሳይንሳዊ መንገድን ተከትሎ እንቦጭን ለማስወገድና ለመከላከል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ጣና የውሃ አካል ብቻ ሳይሆን ያለፈው ዘመን የክልሉ ታሪክ ተከማችቶ ያለበትና፣ በዓሳ ምርትና በቱሪስት መስህብነትም ትልቅ ጥቅም እየሰጠ ያለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እግረ መንገዳቸውንም ጣናን ለመታደግ በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ከዚህ በፊት ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የአዲስ አበባ ጉዳይ
አቶ ገዱ የአዲስ አበባ ከተማን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ አዲስ አበባ ከተማ ባለ ወግ ፤ ባለማዕረግና ክብር ያላት የኢትዮጵያና የአፍሪካ መዲና ነች፡፡ አዲስ አበባን አዲስ አበባ ያደረጋት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንድትሆን የታጨችው በልጆቿ የተባበረ ክንድ ነጻነቷን በማስከበሯና የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት በመሆኗ ነው፡፡
የወሰንና የማንነት ጥያቄ
ወልቃይት ፣ ራያና መተከልን በተመለከተ ለቀረቡት ጥያቄዎች አቶ ገዱ የሰጡት መልስ ዋናው የአዴፓ አቋም ታሪካዊ ሁኔታውንና የህዝቡን ፍላጎት መሠረት አድርጎ መፈታት እንደሚገባው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት በሀቀኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ መሰራት አለበት የሚል ነው የእኛ አቋም፡፡ የትግራይና የአማራ ህዝቦች ከሥር መሠረታቸው አንድ ህዝቦች ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን ለውጡን ለማደናቀፍ የሚፈልጉ ጥቂት አካላት የትግራይ ህዝብን መደበቂያ ለማድረግ በመፈለግ የሚሰሩት ሴራ ነው፡፡
ትውልድን በተመለከተ
ከሱስ የጸዳ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ከመፍጠር አንጻር ለተነሳው ጥያቄም አቶ ገዱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጫት ራዕይ ያለው ትውልድ ከመገ ንባት አንጻር ጠንቅ እንደሆነና ወጣቱን በሞራል፣ በአካላዊ፣ በኢኮኖሚና በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች እየጎዳው እንደሆነ በመግለጽ ይህን ዕጽ ደረጃ በደረጃ ለማጥፋት እንደታሰበ አስረድተዋል፡፡ አሁን የገቢ ምንጭ አድርገው የሚጠቀሙት አርሶ አደሮችም ከዚህ ጎጂ ተክል ተላቀው በምትኩ ለሰው ልጅ የሚጠቅም ሌላ ተክል ማምረት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡
የጠፉ ሰዎች
ታፍነው ተወስደው እስከ አሁን ደብዛቸው የጠፉ ሰዎችን አስመልክቶ ለተነሳው ጥያቄ አቶ ገዱ ሲመልሱ፣ይህን ጉዳይ የሰሙት ዛሬ እንዳልሆነና ከሰሙ ጊዜ ጀምሮ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመሆን የማፈላለጉን ሥራ እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ለለውጡ መነሻ የሆኑትም እንደዚህ ዓይነቶቹ ግፎችና ሰቆቃዎች በህዝባችን ጫንቃ ላይ መጫናቸው ነው ያሉት አቶ ገዱ፣ በክልላችን ብዙ ወገኖች እንዲህ ዓይነት ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ እንደአመራር መልስ መስጠት ስለሚያስ ፈልግ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመመካከር ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ለለውጡ ምን ይጠበቃል?
በመጨረሻም ‹‹ለውጡን በሁለት እግሮቹ ለማቆም ከእኛ ምን ይጠበቃል›› በሚል የቀረበውን ጥያቄ አስመልክተው አቶ ገዱና ሌሎች የልዑካኑ አባላት የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ ለውጡን ተቋማዊ ለማድረግ ገና ብዙ መሠራት እንዳለበት በመግለጽ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ውያን ምሁራን በሙያቸው በማገዝ፣ ገንዘብ ያላቸው በሀገራቸው ኢንቨስት በማድረግ ፣የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ሀገራችን መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማነቃቃትና ስለኢትዮጵያ የገጽታ ግንባታ ሥራ በመሥራት ፣ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ወዘተ ሀገራቸውን መርዳት እንዲችሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ አቶ ገዱ በንግግራቸው ማሳረጊያም ‹‹እየሸቀላችሁ ወደ ሀገራችሁ ላኩ ›› በማለት መልዕክታቸውን በቀልድ አዋዝተው የዋሺንግተን ዲሲውን ውይይት አጠቃለዋል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ልዑክ በአሜሪካን