ጋምቤላ፡-የጋምቤላና ኦሮሚያ ክልል ህዝቦ ችን አንድነት የሚያጠናክር ግንኙነት ለመፍ ጠር እንደሚሰራ ተገለጸ። የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በጋምቤላ ተካሂደ።
መድረኩ ትናንት በተካሄደበት ወቅት የጋም ቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኡመድ ኡጁሉ እንደ ገለፁት፤ ሁለቱ ክልሎች በመከባበርና በመቻቻል እስካሁን እየኖሩ ሲሆን፣ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚፈልጉ ሀይሎችን ሴራ ለማክሸፍ አንድነት ለመፍጠር ይሰራል። በክልሎቹ የጋራ ተጠቃ ሚነት ላይ መሰረት ያደረገ ግንኙነትን ለማሳደግ የህዝቦች አንድነት መጠናከር ይኖርበታል።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ቦታዎች በወሰን ፣ በብሄር፣ በቋንቋ እና በባህል ልዩነት የሚመጡ ግጭ ቶችን ለመከ ላከል ውይይቱ ማስፈለጉን ያመላከቱት ፕሬዚ ዳንቱ፤ ለእርስ በእርስ ግጭት መባባስ መሳሪያ ላለመሆን የሁለቱ ክልል ህዝቦች በመቻቻል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማሳደግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። «በቀጣ ይም ያላቸውን አንድነት በተግባር ማሳየት ይገባቸ ዋል» ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያና ጋምቤላ ክልል ህዝቦች ብዙ መስ ዋትነት በጋራ የከፈሉ መሆናቸውን በመጠቆም፤ ህዝቦቹ ለአንድነታቸውዘብ መቆም እንዳለባቸውም አስገንዝበ ዋል።
‹‹የሁለቱን ክልል ህዝቦች አንድነት ለመበጣጠስ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቆራኙበት ገመድ ጠንካራ በመሆኑ አልተበ ጠሰም›› ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንት ፤የኦሮሚያ ክልል ይህን አንድነት ለማ ጠናከር እንደ ሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡
አገሪቱን ወደ እድገት ለመውሰድ የህዝቦች አንድነት ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም በኦሮሚያ ክልል ከዚህ በኋላ መፈናቀል እንደማይኖርና የተፈናቀሉ ህዝቦችን ወደ ቀዬቻው የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። በጋምቤላ ክልል የሚ ገኙ የኦሮሞ ነዋሪዎች በአፍ መፍቻቸው እንዲማሩ መደረጉን አድንቀዋል።
የመድረኩ ተሳታፉዎችም በሁለቱ ክልሎች መካ ከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በንግድና በባህል ልውውጥ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል። ሁለቱ ህዝቦች በጋብቻ ጭምር የተሳሰሩ መሆናቸውን በመጥቀስም፣ አንድነታቸው እንዳይ ፈርስ የክልሉ አመ ራሮች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 13/2011
መርድ ክፍሉ