በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እንዲያድር፣ ጸብ እንዲፈጠር እና መቃቃር እንዲኖር ከሚያደርጉ ምክንያቶቹ አንዱ ሀሜት ነው፡፡ ያላደረገውን አደረገ በሚል ለሌሎች የሚደርስ ወሬ ከግለሰቦችም አልፎ ቤተሰብን ችግር ውስጥ ሊከት ይችላል፡፡
በሀገራችን ሀሜት ውግዝ ቢሆንም ከማግለል ያለፈ ያስቀጣበት ሁኔታ ግን የለም፡፡ ከወደ ፊሊፒንስ የወጣ ዘገባ ግን ሀሜተኛ ቅጣት እንዲጣልበት ህግ ወጥቶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ ከፊሊፒንስ ዋና ከተማ ማኒላ ቢናሎናን መንደር ሀሜትን የሚከለክል ህግ በቅርቡ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በዚህም ተጠራጣሪነት በህብረተሰቡ ዘንድ ስር እንዳይሰድ ለማድረግ ታስቧል፡፡
ሀሜትን ለመከላከል ሲባል ህግ መውጣቱ በ አ ን ዳ ን ዶ ች ዘንድ ጥሩ ስሜትን ያላሳደረ ቢሆንም፣ ሰዎች ለ ሚ ና ገ ሩ ት ሁሉ ኃላፊነት እ ን ዲ ወ ስ ዱ የሚረዳ መሆኑን የ ሚ ያ ም ኑ ት ቁጥርም በርካታ ሆኗል።
በህጉ መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሜት የፈጸመ ሰው 200 ቤሶ / የፊሊፒንስ ብር/ ወይም 3 ነጥብ8 ዶላር ቅጣት የሚጣልበት ሲሆን፣ በዚህ ላይም ለሶስት ሰዓታት በጎዳና ላይ እየተንቀሳቀሰ ቆሻሻ እንዲሰበስብ ይደረጋል፡፡ በተደጋጋሚ ሀሜት የፈጸሙ ደግሞ እስከ 20 ዶላር የገንዘብ ቅጣት መክፈል እና 8 ሰአት የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
አንዳንድ ወገኖች ታዲያ ህጉን ማስፈጸም እንደሚከብድና የቱ ሀሜት እንደሆነ የቱ ደግሞ እንዳልሆነ ለማወቅ እንደሚቸግር በመጥቀስ ነው ህጉ ግልጽ እንዳልሆነ እየገለጹ ናቸው፡ የከተማዋ ከንቲባ ራማን ጉይኮ ባንፃሩ በህጉ አማካኝነት በሀሜት ላይ የተመሰረተውን የማህበረሰቡን ግንኙነትና የገንዘብ እንቅስቃሴ ማስቆም ዋነኛ ግባቸው ስለመሆኑ አስረድተዋል።
ይህ አነጋጋሪ ህግ ቀደም ሲልም የቢናሎናን ጎረቤት በሆነችው ሞሬኖ እአአ በ2017 ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፤ በርካታ ነዋሪዎች በፈጸሙት ሀሜት 500 ፔሶ ወይም 10 ዶላር እንዲሁም ግማሽ ቀን ቆሻሻ እንዲሰበስቡ የተደረገበት ሁኔታም ታይቷል፡፡
ይሁንና በዚህ አይነቱ ቅጣት ለሁለተኛ ጊዜ ቅጣት የተደረገ አንድም ሰው አለመኖሩም የታወቀ ሲሆን ይህም ማንም ሀሜተኛ ተብሎ መፈረጅ የማይፈለግ ሆኖ በመገኘቱ የተከሰተ መሆኑን መረጃ አመላክቷል።
የጥርጣሬ እና ሀሜት ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር በበጋ ወራት ላይ እንደሚጠናከር ዘገባው ጠቁሞ፣ይህ ወቅት በሀገሪቱ እንደ ሀሜትና ጥርጣሬ ያሉ ተግባሮች በእጅጉ የሚስፋፋበት ወቅት መሆኑን አመልክቷል፡፡ ሙቀት እየጨመረ ሲመጣ ሰዎች በጥላ ስር በስፋት እየተሰባሰቡ ስለሁሉም ነገር በስፋት የሚያወሩበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ያ መ ለ ክ ታ ል ፡ ፡ በዚህ ወቅት በትዳር ጓደኛው ላይ ማን እ ን ደ ሚ ማ ግ ጥ ፣ ማን ከፍተኛ እዳ ውስጥ እንደገባ እና የመሳሰሉት በስፋት እንደሚነሱም ይነሳል ይጣላል።
ከንቲባ ጉይኮ ሀሜትና ጥርጣሬ ጊዜ ማባከኛ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ክልከላ መደረጉ የከተማችን ህይወት ለማሻሻያ ሁነኛ መንገዳችን ነው ›ብለዋል። የ44 አመቱ ከንቲባ ለሀገር ውስጥ መገናኝ ብዙሃን እንዳሉት አዲሱ ህግ የመናገር ነጻነትን እንደማይጋፋ ጠቅሰው፣ ማህበረሰቡን ከስም ማጥፋት፣ ስድብና የመሳሰሉት እንደሚጠበቅም ነው የሚናገሩት፡፡
ከንቲባው ‹‹ ይህ ህግ ስለምንናገረው ሁሉ የከተማዋ ህዝብ እንደ ግለሰብም እንደ ማህበረሰብም ኃላፊነት እንዳለበት ለማስገንዘብ ይጠቅማል›› ሲሉ ገልጸው፣ የከተማችን ህዝብ ኃላፊነት የሚሰማው መሆኑን ለሌሎች ከተሞች ህዝቦች ለማሳየትም እንደሚጠቀም ተናግረዋል፡፡ ከተማዋ ሊቆዩባት የምትገባ ምቹና እና ጥሩ ከተማ መሆኗን እንደሚጠቁምም ነው ያብራሩት፡፡
በሀገራችን በሀሜተኛነት ሳቢያ በህብረተሰቡ የጎሪጥ ከመታየትና ከመገለል የዘለለ የሚያስቀጣበት ሁኔታ ባይኖርም ነገን ማን ያውቃል፡ ቢያንስ መጠንቀቁን መለማመድ ይገባል፡፡
አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2011
በዘካርያስ