መቼም በዚች ምድር አይሰማ የለ፡፡ የምንነግራችሁ በቢቢሲ የተተ ነፈሰ ነው፡፡ እኛ መዥገሮችን ሥናውቃቸው በምግብም ሆነ በኑሮ ጥገኝነታቸው በጋማና በቀንድ ከብቶች ላይ የተመሰረተ ሆነው ነው፡፡ በነገራችን ላይ በእኛ ሀገር የሰው መዥገሮችም እየተበራከቱ መጥተዋል የሚል የሹክሹክታ ነፋስ ይነፍ ሳል፡፡ በእውነት ነፋስ ሆኖ ነፋስ በወሰደው ያሰኛል ወሬውን፡፡ በእኛ ሀገር ቢሆን ኖሮ ወሬው መዥገሮች መዥገሩን አጠቁት ይባልለት ነበር፡፡
የሆነው ከወደ አውስትራሊያ ሲሆን የተሰማው አስገራሚ ወሬ ደግሞ 511 መዥገሮች ከሰውነቱ ላይ የተነሳለት እባብ የቀይ ደም ህዋሳት እጥረት አጋጥሞት የአውስትራሊያ የእንስሳት ሃኪሞች ህክምና እያደረጉለት ነው የሚል ነበር፡፡ አጃኢብ እኮ ነው፡፡ እዚህ ለእኛ እናቶች የተቀመጠ ደም ይጠፋል፡፡ እባቡ ኢንፌክሽን አጋጥሞት እንቅስ ቃሴው ተገድቦ የነበረ ሲሆን፤ ይህም መዥገሮች በቀላሉ እንዲይዙት እድል ፈጥሮላ ቸዋል ብሏል ከረምቢን የተሰኘ የዱር እንስሳት ሆስፒታል።
የእኛው ሀገር እባብ ግን ቀን ካልጣለው በስተቀር አይሞከርም፡፡ እባብ ነዋ! መዥገሮች ደም በመምጠጥ ቀይ የደም ህዋስ እጥረትን ያስከትላሉ። እባቡ የገጠ መውም ይህ ነበር ሲሉም ሀኪሙ የሆነውን ተናግረዋል። የእንስሳቱ የህክምና ተቋም እንዳስታወቀው፤ ከወራት በኋላ እባቡ ሲያገግም ተመልሶ ወደ መኖሪያ ስፍራው የሚለቀቅ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞት ለነበረ ‹‹ኮአላ›› ለተሰኘ እንስሳ ተመሳሳይ ህክምና ተደርጎ እንደነበረ አስታውሰዋል።
‘ኮአላ’ የአውስትራሊያ ብርቅዬ እንስሳ ሲሆን፤ በመዥገር ተወሮ ወደ ህክምና ተቋሙ ከተወሰደ በኋላ አስፈላጊው ህክምና ተደርጎለት ወደ ዱር ተመልሷል። የእንስሳት ሃኪሞች እንደሚሉት፤ የዱር እንስሳት ከሌሎች እንስሳት በተሻለ በመዥገርና በሌሎች ጥገኛ ተውሳክ (ፓራሳይቶች) የመያዝ እድላቸው ዝቅተኛ ነው።
ሆኖም አያድርገውና እንስሳቱ በበሽታ ከተጠቁና እንቅስቃሴያቸው ከተገደበ ደግሞ በቀላሉ በመዥገር ሊያዙ ይችላሉ። መዥ ገሮቹም ‹‹ሠርግና ምላሽ ይሆንላቸዋል›› በፍጥነት ቁጥራቸውን በመጨመር የእንስሳቱን በሽታ የመከላከል አቅም ያዳክማሉ። በቀላሉም በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው የሚፈልጉትን ያህል ደም ይመጣሉ፡፡ የእነሱን ሕይወት ለማፍካት የእሱን ሕይወት እስከወዲያኛው ሊያጨልሙት ይችላል፡፡ በእኛም አገር የሰው ልጆች ሕይወት እንዲህ ናት አያሠኝም ትላላችሁ?
አዲስ ዘመን ግንቦት 1/2011
በሙሐመድ ሁሴን