የኮቪድ ወርሽኝ ያመጣው ተፅዕኖ ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ሰዎች እንደልብ እዳይገናኙ ንግድ ድርጅቶች በሀገር ውስጥና በውጪ ገበያቸውን በማሳጣት ለኪሳራ ዳርጓል፤ ተመልካችው ሰው የሚያሻቸው እንደ ስታዲየም ዓይነት ቦታዎች ተመልካች በሌለበት እንዲጫወቱ ተገደዋል፡፡ ቲያትርና ሲኒማ ቤቶች ሰው እንዳያይገባባቸው ማዕቀብ የተጣለባቸው ነበሩ፡፡ ይህም በመላው ዓለም የኮቪድ ወረርሽኝ መራራቅን ስለሚያስገድድ ነው፡፡ ሰሞኑን በኮረና ወረርሽኝ ጥቂት ተጠቂዎች ያላት አውስትራሊያ የገባ ሰው በሆቴል ተገልሎ እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር፡፡ ግለሰቡ ግን አንሶላ ቀጣጥሎ ከ4ኛ ፎቅ ወረደ ፡-
ሲድኒ (ሬውተርስ) – በአውስትራሊያ ፔርዝ በምትባል ከተማ የሚኖር አንድ ግለሰብ በሚያድርበት ሆቴል የሚደረገውን የኮቪድ ኳረንታይን (ለብቻ መለየትን ) ለመሸሽ ከአራተኛው ወለል መስኮት አንሶላዎችን በመቀጣጠል ማምለጡን ባለፈው ማክሰኞ ፖሊስ ገለጠ፡፡
በከተማው ምዕራብ ጠረፋማ አካባቢ interstate flight በሀገር ውስጥ በረራ ከብሪስባን የደረሰው ግለሰቡ ለመግባት ያቀረበው ማመልከቻ በግዛቱ ተቀባይነት ያጣው የድንበር መግቢያ መመሪያዎች ቫይረሱን ለመግታት በማሰብ ከየትኛውም ሥፍራ ወደ ሀገሪቱ እንዳይገባ በማሰብ ግለሰቡ በ48 ሰዓታት ውስጥ ግዛቱን እንዲለቅ ተነግሮት እንደነበርና ወደ ሆቴልም ተወስዶ በጊዚያዊነት ተነጥሎ እንዲቆይ መደረጉን ፤ ግን ማክሰኞ ከምሽቱ ሰባት ሰዓት በኋላ ‹‹ የአራተኛውን ፎቅ መስኮቱ በመንጠላጠል አንሶላዎችን እንደ ገመድ በመገመድ (በመሥራት) ቀጣጥሎ ወደ መሬት በመውረድ አካባቢውን ለቋል፡፡ ›› ሲል የምዕራባዊት አውስትራሊያ ፖሊስ መገለጹን የሬውተርስ ዘገባ ያስረዳል፡፡ ክስተቱንም የሚያሳዩ ፎቶዎች በፌስ ቡክ መለጠፋቸውንና ለዚሁ የተሠራው ጊዚያዊ ገመድ ከአራተኛው ፎቅ ወለል እስከ መንገዱ ይደርስ እንደነበር ነው የተገለጠው፡፡
ከስምንት ሰዓታት አሰሳ በኋላ ሰውየው በከተማውን አካባቢ በፖሊስ ተይዞ ክስ እንደመሠረተበት ይህም የወጣን መመሪያ በመፃረር እና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት መሆኑ ታውቋል፡፡ ፖሊስ ይህን ይበል እንጂ ሰውየውን 39 ዓመት እንደሚሞላው ከቫይረሱምበተደረገለት ምርመራ ነፃ መሆኑን ጠቁሞ ማንነቱንም ሆነ ለምን ይህን ድርጊት እንደፈጸመ ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡
አውስትራሊያ ጥቂት የሆኑ የኮረና ቫይረስ ሪከርድ ያስመዘገበች ስትሆን ከለሙት አገሮች ጋር ሲነፃፀር የሟቾች ቁጥር ጥቂት ሊሆን የቻለው ብሔራዊ ድንበር እና የውስጥ ግዛት ወሰኖቿን በመዝጋት፤ ከውጪ የሚመጣ ሆነ በውስጥ ድንበሮች የሚገቡ ሰዎችን በሆቴል ኳራንታይ ማድረግ እንደ ገደብ በማስቀመጥ ቢሆንም ፖሊስ ያመለጡ ሰዎችን ትኩረት እንዲሰጥ እንዳስገደደውና በያዝነው የፈረንጆቹ ወር አንዲት ሴት ኳራንታይ ለመሸሽ ባልኮኒዎች ዘላ በር ሰብራ በሰሜን ምሥራቅ የአገሪቱ ክልል ሙከራ አድርጋ አንደነበር መረጃው ያስረዳል፡፡
አዲስ ዘመን መስከረም 3/2014